Home » Entries posted by Zehabesha (Page 3)
Entries posted by Henok Degfu
“የኃይለማርያም ከሥልጣን መልቀቅ የወታደሩን መምጣት የሚያመጣ ከሆነ፤ የጦር ኃይሉ በታላቅ ኃላፊነት ነገሩን እንዲዘው ለማሳሰብ እወዳለሁ” ታምራት ላይኔ

SBS Australia | የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ፤ የወቅቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን የሥልጣን ስንብት ፋይዳ፣ አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖች አስመልክተው ይናገራሉ። “የጠ/ሚ ኃይለማርያም ከሥልጣን መልቀቅ የወታደሩን መምጣት የሚያመጣ ከሆነ፤ የጦር ኃይሉ በታላቅ ኃላፊነት ነገሩን እንዲዘው ለማሳሰብ እወዳለሁ። ቀጥሎ የሚመጣው ጠ/ሚኒስትር ቀውሱን ሊፈታ የሚችል፣ ከብሔሮችና ብሔረሰቦች በላይ አገር ብሎ፤ ኢትዮጵያን ብሎ ለውጥ የሚያመጣ ሰው […]

Continue reading …
ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ

የሕወሓት መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ማምሻውን ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል:: ይህን አዋጅም በመንግስታዊ ሚዲያዎች እንዲተላለፍ አድርጓል;: በኢቢሲ የተላለፈውን መግለጫ ለግንዛቤ እንዲረዳዎ ይመልከቱት::

Continue reading …
ኃይለማርያም ደሳለኝ  ለምን ለቀቁ?

ክንፉ አሰፋ ኢ.ቢ.ሲ. በሰበር ያስተናግደውን የኃይለማርያም ደሳለኝ መግለጫ፤ ዞምቢዎቹ ተሯሩጠው ለማጽደቅ ግዜ አልወሰደባቸውም። እሳቸውም ልክ ስልጣን እንደነበረው ጠቅላይ ሚኒስቴር “ስልጣን አስረክቢያለሁ” ሲሉ እፍረት የሚባል ነገር ፊታቸው ላይ አይታይባቸውም ነበር። ሹመት እንጂ ሕገ-መንግስቱ የሚፈቅደው ስልጣን እጃቸው ላይ እንዳልነበር ሕጻናትም ያውቁታል። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መልቀቅያቸውን በብርሃን ፍጥነት ሲያጸድቀው፤ ድርጊትዋን ከደቡብ አፍሪካው ጃኮብ ዙማ ክስተት ጋር ለማመሳሰል […]

Continue reading …
የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አስከፊ የስደት ዕጣ በመጨረሻው የየትኛውን አሳዳጅ ፖሊሲ ይመርጣሉ? (ልዩ ጥንቅር ) በታምሩ ገዳ

የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አስከፊ የስደት ዕጣ በመጨረሻው የየትኛውን አሳዳጅ ፖሊሲ ይመርጣሉ? (ልዩ ጥንቅር ) በታምሩ ገዳ

Continue reading …
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ሳይቀር በተነሳበት የብአዴኑ ጉባዔ የመጪው የኢህአዴግ ጉልበት ላይ ሚዛኑን ይወስናል | መሳይ መኮንን

ነገሮች በፍጥነት እየተለዋወጡ ነው (መሳይ መኮንን) ነገሮች በፍጥነት እየተለዋወጡ ነው። ይህ ሳምንት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁነኛ ለውጦች የምናይበት ሊሆን እንደሚችል በባለፈው ጽሁፌ አንስቼ ነበር። ቄሮዎች ኦሮሚያ ክልልን ለሶስት ቀናት በአድማ ቀጥ አድርገው አቆሟት። እነበቀለ ገርባ ተፈቱ። እነእስክንድር ከማጎሪያ እስር ቤት ወጡ። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣኑን ለቀቀ። የአስቸኳይ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ ለ3ወራት ታወጀ። አሜሪካን አደጋ አለ እያለች […]

Continue reading …
ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ እንዲፈታ ውሳኔ ተላለፈ

ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው; የወልቃይት ዐማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪና የዐማራ ተጋድሎ መሪው የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ክስ ተቋርጦ ከእስር ሊፈታ መሆኑን ዛሬ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል ሲል ዘግቧል፡፡ ኮ/ል ደመቀ በጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ለየካቲት 22 ቀን 2010 ዓም ቀጠሮ የተሰጠ ቢሆን ክሱ ተቋርጦ እንዲፈታ ተወስኗል ብሏል ሙሉቀን:: የአማራ ተጋድሎ በወልቃይት ማንነት ምክንያት የታሰሩ ወገኖችና ሌሎችም […]

Continue reading …
የኮ/ል ደመቀ ዘውዱ መዝገብ ላይ የካቲት 22 ብይን ይሰጣል ተባለ

(በጌታቸው ሺፈራው_ ጎንደር) የአማራ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጎንደር ምድብ ችሎት በኮ/ል ደመቀ ዘውዱ መዝገብ ላይ የካቲት 22/2010 ዓም ብይን ለመስጠት የመጨረሻ ቀጠሮ ይዟል። ፍርድ ቤቱ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ መዝገብ ላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ መርምሮ “ይከላከሉ፣ አይከላከሉ” የሚለውን ለመበየን ለዛሬ የካቲት 9/2010 ዓም ቀጠሮ ይዞ የነበር ቢሆንም “ከጉዳዩ ስፋት አንፃር እያንዳንዱ ዳኛ ማየት […]

Continue reading …
የህወሓት እና ኦህዴድ ፍልሚያ ያስከተለው የማቃት ስቅታ ወይስ የኃይል ጨዋታ?

ስዩም ተሾመ በተለይ ባለፉት ሦስት አመታት ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ የነበሩበትን ሁኔታ በትውስታ ስመለከት ሁለት የተለያየ ስሜት ይፈጥርብኛል። አቶ ኃይለማሪያም እንደ ሰው በራሳቸው አስበው የተናገሩትንና ያደረጉትን ነገር ሳስብ ያሳዝኑኛል፣ አንዳንዴ ደግሞ ያስቁኛል። ለምሳሌ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጠ/ሚኒስትር እንደሆኑ ከኬኒያው ፕረዜዳንት እሁሩ ኬኒያታ ጋር “ሰለሜ፥ ሰለሜ፥…” ሲጨፍሩ፣ ባለፈው ዓመት ደግሞ “ጥሬ ስጋ እንደሚወዱ”፣ በተለይ ደግሞ “ስለ ታጋሹ […]

Continue reading …
የሃይለማርያም ደሳለኝ መልቀቅና ፋይዳው: (ልዩ ውይይት) ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ገብሩ አስራትና አቶ ልደቱ አያሌው | ሊያዩት የሚገባ

የሃይለማርያም ደሳለኝ መልቀቅና ፋይዳው: (ልዩ ውይይት) ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ገብሩ አስራትና አቶ ልደቱ አያሌው | ሊያዩት የሚገባ

Continue reading …
ኢትዮጵያ ለዘላለም እንድትኖር! –  በተክሉ አባተ (ዶ/ር)

መግቢያ ኢትዮጵያዊያን እጅግ የተቀናጀ፣ ያመረረና ቀጣይነትም ያለው ተቃውሞ በመንግስት ላይ እያካሄዱ ይገኛሉ። ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሏል። መሠረታዊ የሆኑ የመብትና የነጻነት እንዲሁም የፍትህ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ይህንም ተከትሎ ቁጥራቸው በግልጽ ያልታወቀ ኢትዮጵያውያኖች በመንግስት ታጣቂዎች ተገለዋል፣ ቆስለዋል፣ ታስረዋል። ይህም ሁሉ መከራ ወርዶ ሕዝቡ ለበለጠ ትግል ተነሳስቷል። እስካሁን የተከናወኑት ክስተቶች እንዲሁም ሕዝቡ […]

Continue reading …
ኢህአዴግ የአቶ ኃይለማርያምን የስራ መልቀቂያ ጥያቄ መቀበሉ ተገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ተናገሩ፡፡ የመልቀቂያ ጥያቄውም በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተቀባይነት እንዳገኘ፣ የፓርቲው ጽ/ቤት ከመሸ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ አቶ ኃይለማርያም ዛሬ በመንግስት መገናኛ ብዙኃን ቀርበው እንደተናገሩት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸውም ሆነ ከኢህአዴግ ሊቀ-መንበርነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀርበዋል፤ ወይም የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለፓርላማ ማስገባታውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፓርላማውም መልቀቂያቸውን ተቀብሎ እንደሚያሰናብታቸው ተስፋ […]

Continue reading …
በገዥው ፓርቲ ውስጥ የተፈጠረው ውጥረት መባባሱ ታወቀ

  (BBN News) በስልጣን ላይ የሚገኘው ገዥው ፓርቲ የገጠመው ፖለቲካዊ ውጥረት ተባብሶ መቀጠሉን መረጃዎች አመለከቱ፡፡ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ጠንካራ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ፣ ቀደም ሲል በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረው ውጥረት አሁን ላይ ተባብሶ መቀጠሉን ከምንጮች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ የመረጃ ምንጮቹ እንደጠቆሙት ከሆነ፣ የፓርቲው ባለስልጣናት የስርዓት ለውጥ እየጠየቀ በሚገኘው ህዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ ከባድ መደናገጥ ውስጥ ወድቀዋል፡፡ በዚህ […]

Continue reading …
በወልቂጤ ከተማ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ

(BBN News) በወልቂጤ ከተማ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ፡፡ በዛሬው ዕለት በከተማዋ በተካሄደው የአደባባይ ተቃውሞ፣ በርካታ ሰዎች ተገኝተው በስርዓቱ ላይ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት አንድ አካል የሆነው የወልቂጤ ተቃውሞ፣ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ስልጣን እንዲለቅ የተጠየቀበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዛሬ ሐሙስ የካቲት 8 ቀን 2010 በወልቂጤ ከተማ ሲካሄድ የዋለው ይኸው ህዝባዊ […]

Continue reading …
እምየ አንዳርጋቸው ፅጌ የማን “ዕዳ” ነው?!!! – መስከረም አበራ

  የሃገራችን ፖለቲካ ዕድለ-ቢስ የሚባል አይነት ነው፡፡የፖለቲካችን ሰፌድ እንጉላዩን ወደ ፊት ምርቱን ወደ ታች የሚቀብር ክፉ ልክፍት አለበት፡፡ ፖለቲካችን ፈውስ የራቀውም በዚሁ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም! እንደ እኛ ባለው ተቋማዊነት በራቀው ኋላቀር ፖለቲካ ቀርቶ ተቋማዊነት በበረታበት ስልጡን ፖለቲካዊ ከባቢም ቢሆን የፖለቲካውን ልጓም የያዙ የግለሰቦች ስብዕና ለፖለቲካዊ ፈውስ ሁነኛ ግብዓት ነው፡፡ የሃገራችን ፖለቲካ ብዙም ባይሆኑ የእውነት ለህዝብ […]

Continue reading …
የሃይለማርያም ደሳለኝ መልቀቅና የሽግግር ፖለቲካ በኢትዮጵያ: ሊታይ የሚገባው የጀዋር መሐመድ፣ ፕ/ር እዝቅኤል ጋቢሳና ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ ትንታኔ

የሃይለማርያም ደሳለኝ መልቀቅና የሽግግር ፖለቲካ በኢትዮጵያ: ሊታይ የሚገባው የጀዋር መሐመድ፣ ፕ/ር እዝቅኤል ጋቢሳና ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ ትንታኔ (ውይይቱ የተካሄደው በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ነው::)

Continue reading …
የመልቀቂያው እና የመለቀቅ ጉዳይ

ከጌታቸው ሽፈራው ~ነገ የካተቲት 9/2010 ዓም ለብይን የተቀጠረውን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ፍርድ ቤት ለመከታተል መልቀቂያ ደብዳቤ ሳላስገባ አዲስ አበባን ለቅቄ ስለነበር ከኢንተርኔት ጋር ተቆራርጬ ነው የዋልኩት ~ የስምንት ሰዓት መንገድ ከተጓዝን በኋላ፣ ባህርዳር ስንደርስ አንድ ወዳጄ ደውሎ አቶ ሐይለማርያም መልቀቂያ እንዳስገቡ አጫወተኝ፣ ሌላኛው ወዳጄ ደወለልኝ፣ ብዙ ሰው ደወለ። ስለ ኃይለማርያም መልቀቂያ! እኔ ብቻ ሳልሆን የአውቶቡሳችን […]

Continue reading …
የእነ እስክንድር፣ አንዷለምና ማሙሸት ፈተና! – ከሙሉቀን ተስፋው

የአገራችን ፖለቲካ እንደ ልብ አንጠልጣይ ሙቪ በየቀኑ በርካታ አዳዲስ ነገሮችን እያፈራረቀ ነው፤ ካለፈው ይልቅ ደግሞ መጪው ጊዜ የበለጠ አዳዲስ ክስተቶች የሚከናወኑበት ነው፡፡ ምናልባትም መፈንቅለ መንግሥት፣ እንደ አገር መውደቅ፣ የባለሥልጣናት መቀያየር፣ ብዙ ሞትና ብዙ ስደት ብዙ… ነገር ብዙ ሳንቆይ የምናስተናግዳቸው ኩነቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ባጪሩ 1983 ዓ.ም ወደ ኋላ ተጉዘነው እንደገና የደረሰንበት ይመስላል፡፡ ሕወሓት ለመፈንቅለ መንግሥት የሚያግዛትን […]

Continue reading …
ሰበር ዜና: ሃይለማሪያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ አስገቡ | ስለመልቀቂያቸው የተናገሩበትን ቪዲዮ ይዘናል

የሕወሓት መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኢሕአዴግ ሊቀመንበርነትና ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ይፋ አደረጉ:: ዘ-ሐበሻን ጨምሮ የተለያዩ ሚዲያዎች የሕወሓት መንግስት ሃይለማርያም ደሳለኝን ለማንሳት እየሰራ መሆኑን በተደጋጋሚ ምንጮችን እየጠቀሱ ሲዘግቡ የነበረ ሲሆን “ሳልቀደም ልቅደም” በሚል በሚመስል መልኩ ጠ/ሚ/ሩ መልቀቂያ አስገብተዋል:: ጠቅላይ ሚኒስተሩ ለመንግስት ቅርብ ለሆኑ ሚዲያዎች እንደተናገሩት ያቀረቡት መልቀቂያ በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና በደኢሕዴን ሥራ […]

Continue reading …
ቢቢኤን ዜና: ከእስር የተፈቱትን የጀግኖቹን ኡዝታዞቻችንን ድምጽ ይስሙ

ቢቢኤን ዜና: ከእስር የተፈቱትን የጀግኖቹን ኡዝታዞቻችንን ድምጽ ይስሙ

Continue reading …
በጠራራው ፀሐይ ጧፍ አብርቼ እንደ ዲዮጋን ለፈለግኋቸው አባቶቼ | ሰላሞቻችንን ፍቱልን – ዲ/ን አባይነህ ካሴ

እልፍ ደስታ በልቡናየ የደም ሥሮች ሁሉ ይወጣሉ ይወርዳሉ፡፡ ብዙ የሀገር ልጆች በአጥር ከተዘጋው እስር ቤት ወደ ክፍቱ እስር ቤት ስለወጡ፡፡ ይህም አንድ ጋት ነፃነት ነውና፡፡ በመገደድም ይሁን በመፍቀድ ይህን ያደረጉትን ሁሉ ማመስገን ይገባናል፡፡ በቂም ቋጠሮ የትም አንደርስምና ልቦናችን ሁሉ በይቅርታ ደም ይገንባ! ከተፈቱት መኻል ዐይኖቼ አሁንም ይንከራተታሉ፣ ማረፊያቸውን ግን አላገኙም፡፡ እነ አባ ገብረ ኢየሱስ የታሉ? […]

Continue reading …
በርና መስኮትህን ዘግተህ ድመትህን አትቅጣ | መስፍን ጌታቸው  (የሰው ለሰው  የዘመን ድራማ ደራሲ )

ድሮ በህፃንነቴ ዘመን እናቴ ትነግረኝ ከነበሩት ጣፋጭ ወጎች መሀል አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ በድሮ ጊዜ አንድ በትልቅ በትንሹ ዱላ መምዘዝና ያገኘውን ሁሉ መቀጥቀጥ የሚቀናው ሞገደኛ ሰው ነበረ፡፡ ታዲያ ይሄ ሰው በአንድ ወቅት በአለቆቹ ክፉኛ ተበሳጭቶ ቤቱ ሲገባ ለፆም መያዥያ የገዛትን ቅንጣቢ ስጋ ያስቀመጠበት ቦታ ላይ ያጣት ይመስለውና በጣም ይናደዳል፡፡ ንዴቱ ከቁጥጥረ ውጪ ሲሆንበት ግዜ ስጋዬን ቅርጥፍ […]

Continue reading …
ምስጋና ይደረሳችሁ! እስክንድር ነጋ፥ አዲስ አበባ

ክብር ለኃያሉ እግዚአብሔር፣ ለሕዝብ፣ ለቤተሰቦቼ፣ ለወዳጆቼ፣ የሙያ አጋሮቼ ለሆኑት ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች፣ እንዲሁም፣ ለዓለማቀፍ ማኅበረሰብ (በተለይ ለምዕራባውያን) ይሁንና፣ በዛሬዋ ዕለት ከትንሿ እስር ቤት ወጥቼ ትልቁን እስር ቤት ተቀላቅያለሁ። ልቦናቸውን በጭቆና ያደነደኑ አምባገነኖች እጄን ለ18 ዓመታት እንዲጠፍር ያዘጋጁት የግፍ ሰንሰለት፣ ይኸው በ6ኛው ዓመት በሕያው እግዚአብሔር ፍቃድና ፍትሕ በተራበው ሕዝባችን ትግል ተበጣጥሶ ወድቋል። ይህ የተበጣጠሰ ሰንሰለት […]

Continue reading …
ለአቶ በቀለ ገርባ በአዳማ አቀባበል አድርገው ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱ በመቶዎች ወጣቶችን ፌደራል ፖሊስ አሰረ

(ዘ-ሐበሻ) በአዳማ ከተማ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በመውጣት ትናንት ከ እስር ለተለቀቁት አቶ በቀለ ገርባ በስታዲየም ውስጥ አቀባበል አደረጉ:: የኦህዴድ ማ ዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የአዳማ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበበ በስታዲየሙ አቶ በቀለን ለመቀበል ለወጣው ሕዝብ ንግግር አድርገዋል:: ይህ ለአቶ በቀለ አቀባበል በሰላም ከተጠናቀቀ በኋካ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በፌደራል ፖሊስ […]

Continue reading …
‘የአግ 7 በብዙ አካባቢዎች በሚደረጉ የህዝብ ትግሎች ውስጥ አለ… ትግሉ ግን በቀዳሚነት የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ነው” አቶ ነአምን ዘለቀ  (አዲስ ቃለመጠይቅ)

ከቃለምልልሱ ውስጥ የተቀነጨቡትን ያንብቡና ከታች ያድምጡት:: –ሁሉንም ባለድርሻዎች ያካተተ -የፓለቲካ ሃይሎች ፡ የሲቪክ ማህበረሰቡን፡ ታዋቂ ምሁራን ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ወዘተ የሚገኙበት ማንንም ያላገለለ የብሔራዊ ዉይይትና ከዚህም የሚወጣ የሽግግር መንግስት ምስረታ ሂደት ብቻ ነው ተቀባይነት የሚኖረው፡፡  ሰፊው የኢትዮጵያው ህዝብ  ይህ ነው የማይባል የህይወት መስዋእትነት በመክፈል ከፋሽታዊው የህወሓት ስርአት ጋር እየታገለ፣ እየተጋተረ የሚገኘው ወደ ሀቀኛ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የሚያደርስ ፡ […]

Continue reading …
እንቁላል በውጪ ኃይል ከተሰበረ ህይወት ይጠፋል (ይፈጸማል)  | ሁጂን መንጉዱማ ኢጪቲን ሆጀተምት  | ኩሎም ዓበይቲ ጉዳያት  ዝውገኑ ካብ ውሽጢ እዩ!!

እንቁላል በውጪ ኃይል ከተሰበረ ህይወት ይጠፋል (ይፈጸማል) ሁጂን መንጉዱማ ኢጪቲን ሆጀተምት ኩሎም ዓበይቲ ጉዳያት ዝውገኑ ካብ ውሽጢ እዩ!! ከታምራት ይገዙ   ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጽሁፌ ባጭሩ ለማስቀመጥ የሞከርኩት የዘመኑ እርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ያቀጣጠሉት የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በአብዛኛው ኢትዮጵያ ክልል ስር ሰዶ ህወሀት/ኢህኣዴግ  በወገኖቻችን ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍ ከልክ ያለፈና መደረግ ያልነበረበት ወንጀል መሆኑን ሌሎችም ተረድተው በሰላማዊ መንገድ […]

Continue reading …
የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ – “መፈታቴ ደስተኛ የሚያደርገኝ አጠቃላይ ኢትዮጵያ ስትፈታ ነዉ”

ሸንቁጥ አየለ ——————— ልክ ከእስር ቤት እየወጣ ሳለ የመኢአድ ፕሬዝዳንትን አቶ ማሙሸት አማረን እንኳን ደስ አለህ ልለዉ ስልክ ደዉዬ ነበር:: የመለሰልኝ መልስ በጣም አስደመመኝ:: አሁንም ለትግል ያለዉ ወኔ አለመብረዱም ገረመኝ::ከአስራ ሶስት አመታት በላይ ሲታሰር ሲፈታ የኖረ ሰዉ አለወንጀሉ ታስሮ ሲፈታ ምን ሊሰማው እንደሚችል እኔ ማወቅ አልችልም:: ሆኖም እንኳን አብሮ ደስ ያለን ይለኛል ብዬ ነበር የጠበቅሁት::ሆኖም […]

Continue reading …
እስክንድር ነጋና አንዷለም አራጌን ጨምሮ ጥቂት የሕሊና እስረኞች ከ እስር ቤት ወጡ

(ዘ-ሐበሻ) ብርቱው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እና አንዷለም አራጌን ጨምሮ ጥቂት የሕሊና እስረኞች ዛሬ ከ እስር ቤት ተለቀቁ:: አሁንም በርካታ እስረኞች በግፍ እስር በተለያዩ እስር ቤቶች እየማቀቁ ይገኛሉ:: በዛሬው ዕለት ከ እስር ከተለቀቁት መካከል የህዝበ መስሊሙን ዉክልና በመቀበል ለዓመታት በእስር ቤት ሰሰቃዩ የነበሩት ጀግና የህዝብ ወኪሎች ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ፣ኡስታዝ መሐመድ አባተ ኻሊድ ኢብራሂም የሚገኙበት […]

Continue reading …
ጀግናው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከእስር ቤት ሲወጣ የሚያሳዩ ፎቶዎች

አይበገሬው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከደቂቃዎች በፊት ከ እስር ቤት ተለቋል:: የተደረገለት አቀባበል ይህን ይመስላል::

Continue reading …
የቄሮ አስደሳች መልዕክት – “የአማራ ደም ደማችን ነው… የሶማሌ ደም ደማችን ነው” | “አላማችን ኢትዮጵያ ለማቋቋም እንጂ ለመገንጠል አይደለም”

“የአማራ ደም ደማችን ነው… የሶማሌ ደም ደማችን ነው…የደቡብ ደም ደማችን ነው…የአፋር ደም ደማችን ነው…አላማችን ኢትዮጵያ ለማቋቋም እንጂ ለመገንጠል አይደለም” ቄሮ

Continue reading …
ጀግናው አንዷለም አያሌው ከእስር ቤት ወጣ

  አንዷለም አያሌው በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት አንዱ ነው:: አንዷለም በነ አንዷለም አራጌ ክስ 8ተኛ ተከሳሽ ሆኖ ተከሶ የነበረ ሲሆን በአንድ ወቅት በፍርድ ቤት “ለጊዜው ሥራ የለኝም፣ ከምኖርበት ካርቱም የስደተኛ ጣቢያ ነው ተይዤ የመጣሁት፤ ስለዚህ አድራሻ የለኝም፣ ቀደም ሲል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላ ሳለሁ የተሰጠኝን ቤት ባለቤቴንና […]

Continue reading …