በሐረርጌ ደደር ከተማ የሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ወጣ | “መገደል በቃን! ኦህዴድ እያስገደለን ነው! ለማ መገርሳ ለፍርድ ይቅረብ” (አጭር ቪዲዮ ተያይዟል)

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

(ዘ-ሐበሻ) በሕወሓት የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ እየደረሰ ያለውን የሰው ሕይወት ማጥፋት ዘመቻን በመቃወም ይህ ዜና እየተጠናቀረበት ባለበት በዚህ ሰዓት ላይ በሐረርጌ ደደር ከተማ የሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ወጣ::

በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን በሕወሓት የሶማሌ ክልል የአጋዚ ወታደሮች በኦሮሞዎች ላይ የሚያደርሱትን ጭፍጨፋ እንዲያቆሙ እየጠየቁ ነው:: በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልልን አስተዳድራለው የሚለው የኦህዴድ አመራር ከሕወሓት ጎን በመሰለፍ ኦሮሞዎችን እያስገደለ ነው በሚል በተቃውሞው ስሙ ሲጠራ ውሏል:: ለማ መገርሳ ለፍርድ ይቅረብ፣ መንግስት ስልጣኑን ለሕዝብ ያስረክብ፣ መገደል በቃን፣ ኦህዴድ እያስገደለን ነው፣ ዳውን ዳውን ወያኔ እና ሌሎችም መፈክሮች ከሕዝቡ እየተሰሙ ነው::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *