News Feature

የሕወሓቱ ጆሴፍ ጎብልስ፤ የኢሕአፓው አንበርብርና የሻዕብያው በረከት ሰምዖን | ከአቻምየለህ ታምሩ


ጊዜው በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1973 ዓ.ም. ነው። ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሱ ባዕዳን ኃይሎች ቀዳሚ ሀገር በቀል ወኪል የሆነው ኢሕአፓ በሻዕብያ መሪነት ከወያኔ ጋር መረብን ተሻግሮ አሲምባ ከመሸገ በኋላ በወያኔ ተመትቶ ከትግራይ እንደለቀቀ የከተማ የትጥቅ ትግሉም ሳይሳካለት ቀርቶ እንደገና ጫካ በመግባት የትጥቅ ትግሉን ለመቀጠል የተከዘ ማዶዎቹ እነ ቢንያም አዳነ ኢሕአሰ [የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ሰራዊት] በሚል ስያሜ የመሰረቱትን ወታደራዊ ክንፍ ይዞ በድጋሚ አሲምባ ቢከትም፤በጫካ ትግሉ ብዙም ሳይገፋ ድርጅቱ በውስጥ ክፍፍል መታመስ ጀመረ።

አቻምየለህ ታምሩ

ድርጅቱ የተተራመሰው አፈ ጮሌ የድርጅቱ ታጋዮች ከድርጅቱ መርህ ውጭ የሆነ ጽሁፍ በመበተናቸው ነው ተብሎ አራት ፋኖዎች ለጊዜው በቁጥጥር ስር ዋሉ። የነዚህ አራት ፋኖ ጽሁፍ በታኞች ቡድን አስተባባሪ በበረሀ ስሙ «አንበርብር» እየተባለ ይታወቅ የነበረው የመረብ ማዶው ሰው የድርጅቱ አስኳድ ነበር። «አንበርብር» ከኢሕአፓ ስነስርዓት ውጪ ድርጅቱን የሚጎዳ ጽሁፍ የበተነው ከወያኔና ከሻብያ በተሰጠው ድርጅቱን የማፍረስ ተልዕኮ እንደሆነ የትግል አጋር ፋኖዎቹ ይናገራሉ። በመጨረሻም የአንበርብር ቡድን ከህዳር 7 ቀን እስከ ህዳር አስራ አንድ ቀን 1973 ዓመተ ምህረት በትግራይ ውስጥ በተምቤን አውራጃ አምበራ ወረዳ ሽልም እምኒ ቀበሌ ተክራርዋ በተባለች መንደር ከኢሕአፓ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የአፈነገጡ ተጨማሪ ፋኖዎችን በመያዝ ቀደም ብሎ ወያኔ ወዳዘጋጀላቸው ቦታ ተወስደው በወያኔና ሻዕብያ አጋፋሪነት «ጉባኤ» ዘርግተው አዲስ ፓርቲ ለመመስረት «መከሩ»።
በነአንበርበር ስብሰባ ላይ የነበሩ የወያኔ ሰዎች እነአንበርብርን በነፍስ አባታቸው በሻዕብያ ሕግ መሰረት አግባብተው በስብሰባው መጨረሻ በህዳር 11 ቀን 1973 ዓመተ ምህረት ከኢሕአፓ አፈንግጦ የወጣውን የነአንበርብርን ቡድን በሕወሓት አዋላጀት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ [ኢሕዴን] የሚባል ፓርቲ ተመሰረተ። ሕወሓት ከኢሕአፓ የውስጥ ደንብ ውጭ ኢሕአፓን የሚያፈርስ ጽሁፍ እንዲጽፍና እንዲያሰራጭ በኋላም በሕወሓት ፕሮግራም ኢሕዴንን እንዲቋቋም በማድረግ ትልቅ ሚና የነበረውና «ድርጅቴን አዳክሞ አባላቶቼን አስከዳብኝ» ብሎ በወቅቱ ኢሕአፓ መጀመሪያ ያሰረውና ከእስር ካመለጠ በኋላ በይፋ ያወገዘው ከሀዲው ግለሰብ፤ በበረሀ ስሙ አንበርብር ተብሎ ሲታወቅ የኖረው የወያኔና የሻዕብያ ተላላኪ ዛሬ በሚንስትር የማዕረግ ስሙ በረከት ስምዖን ተብሎ የሚጠራው ግለሰብ ነው።

ኢሕዴን እዚያው ትግራይ ውስጥ የሕወሓት «የጡት ልጅ» ሆኖ እንደተመሰረተ ለነአንበርብር ቡድን በመጀመሪያ ወታደራዊ ስልጠና የሰጣቸው የወያኔው የቀድሞው የመከላከያ ሚንስትር የነበረው ስዬ አብርሀ ነበር። የስዬን ስልጠና እንደጨረሱ ኢሕዴኖች መሳሪያ ታደላቸውና ወያኔ «በአማራ አገር» በሚለው ምድር ለሚደረገው የሕወሓት ትግል በመንገድ መሪነትና በአማርኛ አስተርጓሚነት ተመደቡ።

ኢሕዴን ከተመሰረተ ዘጠኝ አመት ከአምስት ወር ሲሆነው ወያኔ ኢሕዴንን አማርኛ እያስተረጎመ ጎጃምና ጎንደር፤ ወሎና ሸዋን ተሻግሮ አዲስ አበባ ገባ። ወያኔ አዲስ አበባ እንደገባ የዐማራ ጥላቻ የወለደው ኦነግ የሚባለው ድርጀት የወያኔ የሽግግር መንግሥት አካል ሆኖ ያገኘውን ስልጣን በመጠቀም በወለጋ፣ በአርሲ፣ በሐረርጌ፣ በባሌና በሎሎች ከተሞች ሁሉ ለዘመናት አገር ሰላም ብለው ይኖሩ የነበሩ ዐማሮችን ያለርህራሄ ማረድና መጨፍጨፍ ጀመረ። ዐማራው በያለበት ደሙ ደመ-ከልብ መሆኑ እንቅልፍ ያሳጣቸው እጀ መድሐኒቱ ሐኪም ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በየተገኘበት ይታረድ የነበረውን የዐማራ ሕይወት ለመታደግ «መአሕድ» [የመላው አማራ ሕዝብ ድርጀት] የሚባል ሕይወት አድን ድርጅት አቋቋሙ።

መአሕድ እንደተቋቋመ ባጭር ጊዜ ውስጥ እልፍ አእላፍ አባላትና ደጋፊዎችን ከጎኑ አሰለፈ። በኢትዮጵያ ሕዝብ ባጠቃላይና በተለይም በዐማራው ዘንድ የመአሕድ ተሰሚነትና የፕሮፌሰር አስራት ቅቡልነት እንቅልፍ የነሳው ወያኔ ኢሕአዴግ ውስጥ በዐማራ ስም የሚጠራ ድርጅት ስለሌለው [የኢሕአዴግ አካል የሆነው የነ አንበርብሩ ኢሕዴን የስም ሕብረ ብሔራዊ ድርጅት እንደነበር ልብ ይሏል] መአሕድ ዐማራውን ከጎኑ አሰልፎ ሳይጨርሰው ከመአሕድ የዐማራውን ውክልና ለመጫረት ሲባል የስም ሕብረ ብሔራዊው ድርጀት የነበረውን ኢሕዴን ወደ ብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ [ብአዴን] ተለውጦ የፕሮፌሰሩን መአሕድ እንዲውጥ ትዕዛዝ ሰጠ።
ኢሕዴኖች እነ አንበርብርም እነ አባዱላን፣ እነ ካሱ ኢላላን ይዞ ከነበረው ከሕብረ ብሔራዊው ኢሕዴን ወደ ብአዴን እንዲያንሱ የተሰጣቸውን የወያኔ ትዕዛዝ ሰጥ ለጥ ብለው በመስገድ በይሁንታ አስተናግደው የሕብረ-ብሔራዊውን የኢሕዴን ድርጅት የፖለቲካ ፕሮግራም ሳይቀይሩ «ወደ ብሔረሰብ ድርጅትነት» ተለወጡ። በ1973 ዓ.ም. ኢሕአፓን ከድቶ ለወያኔ ያደረው ኢሕዴን በ1985 ዓ.ም. ደግሞ ራሱን ኢሕዴንን ከድቶ ብአዴን ሆነ። ዛሬ «ብአዴን ነን» ከሚሉን የድርጅቱ እንደራሴዎች ይልቅ የብአዴንን እውነተኛ ታሪክ ከስር መሰረቱና ለምን አላማ ድርጅቱ እንደመሰረተው የሚያውቁት ድርጅቱን የመሰረቱት ወያኔና ሻዕብያ ብቻ ናቸው። ይህንን ለማየት ድርጅቱን ወያኔ እየሾማቸው ይመሩት የነበሩት ሰዎች ስለብአዴን የተናገሩትን መውሰድ በቂ ነው።

ለምሳሌ ኢሕዴን ወደ ብአዴን ከመቀየሩ በፊት የነእያሱ አለማየሁ ኢሕአፓ «ለወያኔ ያደሩ ከዳተኞች» ብሎ ክስ ባቀረበባቸው ሰዓት የወቅቱ የደርጅቱ መሪ የነበረው የዛሬው ፓስተር ታምራት ላይኔ ኢሕአፓ በኢሕዴን ላይ ላቀረበው ነቀፌታ በድርጅቱ ልሳን በማለዳ መጽሔት አስተያየት ሲሰጥ «እኛ ከኢሕአፓ ተለይተን የወጣን ትክክለኛ ኢሕአፓዎች ነን» ብሎ ነበር። ይህ የፓስተር ታምራት አባባል ተስፋየ መኮንን «ይድረስ ለባለታሪኩ» በሚለው መጽሐፉ ከፋጸው ታሪክ አኳያ ውሃ የሚቋጥር ነው። በተስፋየ መኮነን ትንተና የነ አንበርብር ኢሕአፓ ከብርሀነመስቀል ረዳ ኢሕአፓ የቀጠለ ይመስላል።

በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላው የኢሕዴን ታጋይ ነኝ የሚለውና የድርጅት መሪ የነበው አዲሱ ለገሠ የኢሕዴንን ምስረታ በዓል ሲያከብር ድርጅቱ ለዐማራ ሕዝብ መብት ለመታገል የተፈጠረ መሆኑን ተናግሮ ነበር። ልብ በሉ ድርጅቱኮ የተመሰረተው ሕብረ ብሔራዊ ድርጅት ሆኖ ነው። አሁን ለድርጅቱ መሪነት የተወከለው ደመቀ መኮነንም ቢጠየቅ ሌላ እንደሚመልስ እርግጠኛ ነኝ። ለዚያ ነው ስለድርጅቱ አለማ ኢሕዴን ወይም ብአዴን ነን ከሚሉ ሰዎች በላይ ድርጅቱን ለምን አላማ እንደተቋቋመ የሚያውቁት ፈጣሪዎቹ ወያኔና ሻዕብያ ብቻ ናቸው ያልሁት። የሆነው ሆኖ ኢሕዴን/ብአዴን ይህን ሁሉ የክህደት ውል ለወያኔ እየፈረመ ሲገለባበጥ የኖረው በኢትዮጵያና በተለይም በዐማራው ውርደት፣ ድህነት፣ ባርነት፣ ስደት፣ ግድያና ሰቆቃ ላይ የወያኔን የግዛት ዘመን ለማራዘም ነው።

የወያኔን አርባኛ ዓመት ድል ያለ የንግሥ በዓል ተከትሎ የኢሕአፓና የዐማራ ህዝብ ከሀዲዎች ማህበር የሆነው ጉደኛው ብአዴን ሳያፍር «የ35ተኛ ዓመት ልደቴን ላከብር ነው» በማለት ህዝቡን በመዋጮ ከማስጨነቁም አልፎ «በአለም ላይ የመጨረሻ ድሀ ክልል» የተባለውን የዐማራ ክልል ከፍተኛ በጀት ለበዓሉ ማክበሪያ መድቦ አክብሯል። ብአዴን በዐማራ ገንዘብ ድል አድርጎ ያከበረው የ35ኛ ዓመት የንግሥ በዓሉ ድርጅቱን የመሰረቱት ወያኔና ሻዕብያ ዐማራን እንዲያጠፋና በተገኘበት ሁሉ እንዲያሳርድ ስላደረገው አስተዋጽኦ ነው።

የብአዴኑ በረከት ሰምዖን የልደት ስም መብራህቱ ገብረህይወት ነው። ከመብራህቱ ገብረህይወት የተምታቱ ታሪኮች ዋናው በዘሩ ኤርትራዊ ሆኖ ሳለ የዐማራ ድርጅት መሪ መሆኑ ነው። ይሄ ከሞራል አንፃር ብአዴን ውስጥ ላሉ ዐማሮች ስድብ ነው። መብራህቱ ገብረህይወት በሕብረ ብሄራዊ ድርጅት ውስጥ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ከሆነ ኢትዮጵያንም ቢመራ ጥያቄ ባልተነሳበት ነበር። ሰው አገሬ የሚለው አገሩ መሆኑ ይታመናልና። የዘር ፖለቲካ የሚያራምድ ግን የግድ እሱም ዘሩን የሚያቅፍ የፖለቲካ ድርጅት ወስጥ መግባት ይጠበቅበታል። ወያኔ «ዐማራ በዘሩ መደራጀት አለበት» ብሎ ሲያበቃ፣ የዐማራ ድርጅት ፈጠርሁ ብሎ ዐማራውን እንዲመሩ ያስቀመጣቸው ግን ዐማራ ያልሆኑትንና ከልዩልዩ ዘሮች ያውጣጣቸውን ምንደኞችንና ዐማራን በመጥላት ክብረ ወሰን የተቀዳጁ ቅጥረኛ ሰው በላዎችን በመሰብሰብ ነው። ይህም በመሆኑ የተነሳ ቂም ባዘለ የጥላቻ ክፋት ውስጥ ሆነው የወያኔን ዐማራ የማጥፋት ፕሮጀክት ከግብ ለማድረስ ባለፉት ሀያ ስድስት ዓመታት አብረውት ደፋ ቀና እያሉ ከርመዋል።

አዲሱ ለገሰ፣ ህላዬ ዮሴፍ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ታደሰ ካሳ፣ ታምራት ላይኔ፣ ካሳ ተክለብርሀን፣ ወዘተ እንደ መብራህቱ ገብረሕይወት ሁሉ ዐማራ ያልሆኑና ራሳቸውን ግን የዐማራ ህዝብ ወኪል እኔ ነኝ የሚሉ የዐማራ ህዝብ ጠላቶች ናቸው። እነዚህ ሁሉ ወያኔ ያበጃቸው ፍጡራን ዐማራን ለማጥፋትና ዐማራውን በማዳከም ሕወሓትን ለማጠናከር በዐማራ ሕዝብ አናት ላይ የተቀመጡ የዐማራ ቀንደኛ ጠላቶች ናቸው። የወሎ መሬት ተቆርሶ ለትግራይ ሲሰጥ፤ የጎንደር መሬት ተገምሶ ለትግራይ ሲታደል፣ ጎጃም ለጉምዝ ተላልፎ ሲሰጥ፤ ሸዋ ለአምስት ሲከፈል፤ ዐማሮች እንደ ፋሲካ በግ በኦነግና በወያኔ ሲታረዱ እነመብራህቱ ገብረሕይወት፣ አዲሱ ለገሰና ታምራት ላይኔ የሰጡትን ምላሽ መቼም ልንረሳው አንችልም።

ነውረኛው አዲሱ ባለፈው ሰሞን ስለወልቃይትና ሁመራ እንዲሁም ሰሜን ወሎ ወደ ትግራይ ሪፑብሊክ ስለመካለሉ በትግርኛ ተጠይቆ በሰጠው መልስ እወልከዋለሁ በሚለው በዐማራ ወንበር እየፏለለ ከትግራይ ወገን ሆኖ «የዐማራው ገዢ መደብ ከትግራይ ቆርሶ የወሰዳቸው መሬቶች ስለነበሩ ነው ወደ ትግራይ የተካለሉት» ያለውን መቼም የማንረሳው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ዛሬ ፓስተር ሆኛለሁ እያለ የሚያጭበረብረው ታምራት ላይኔም ዐማሮች አርባጉጉ፣ ሀረር፣ ወለጋ፣ አርሲ ወዘተ እንደ ፋሲካ ዶሮ ሲታረዱ ካማራ ክልል ውጭ ያለ አማራ አናቅም ብሎ ተሳልቆባቸዋል።

የወያኔው በረከት ስምኦን ካሳሁን ገብረሕይወት የሚባል ወንድም ነበረው። መብርሀቱ ስሙን «በረከት ስምዖን» ሲል የቀየረው የሻዕብያን ተልእኮ ይዞ በረሀ ከገባ በኋላ ነው። እውነተኛው በረከት ስምዖን አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገ፤ ሊሴ ገብረማርያም የተማረ ኤርትራዊ ነው። እውነተኛው በረከት ሰምዖን ለኤርትራ መገንጠል ከኢሕአፓ ጋር በርሀ ወርዷል። ከጊዜ በኋላ ግን ባልታወቀ ምክንያት ከኢሕአፓ መካከል ጠፋና የውሀ ሽታ ሆነ። ሆኖም ግን ሰውየው ባልታወቀ ሁኔታ ፈረንሳይ ላይ ፓሪስ ተከሰተ። እውነተኛው በረከት ሰምዖን በድንገት ስለጠፋ ሊታገል አብሯቸው በረሀ የወረደ የመሰላቸው ኢሕአፓን የማያውቁት ተነጂዎች በረከት ስምዖን በደርግ የተገደለ ወይንም በነሱ ቋንቋ የተሰዋ መሰላቸውና በሰማዕትነት አሰቡት። በዚህ ጊዜ ነበር እንግዲህ በደርግ የተገደለ የመሰለውን እውነተኛውን በረከት ሰምዖን ለማስታወስ ሲባል ሌላኛው የኤርትራ ተወላጅ መብራህቱ ገብረህይወት ስሙን በረከት ስምዖን ሲል ስሙን ከናባቱ የለወጠው። ከዚህ ጊዜ በኋላ ነበር ኤርትራዊው መብርሀቱ ገብረሕይወት በረከት ስምዖን እየተባለ መጠራት ጀመረ።

ከፍ ሲል እንደገለጽሁት እውነተኛው በረከት ስምዖን በደርግ አልተገደለም ነበር። በኢሕአፓ ውስጥ ሻዕብያ የሰጠውን ስራ ጨርሶ በሌላ ምድብ ወደ ፓሪስ ተዛውሮ እንጂ። ይህ እውነተኛው በረከት አሁንም ድረስ በሕይወት ፓሪስ ውስጥ ከእህቱ ጋር ይኖራል። እውነተኛው በረከት ሰምዖን ሩት ሰምዖንና እና ሃና ሰምዖን የተባሉ የሻዕብያ ታፋዮች የነበሩ ሁለት እህቶች አሉት። እውነተኛው በረከት ሰምዖን አሁንም ድረስ በሕይወት ያለና ሃና ስምዖን ከምትባለው እህቱ ጋር በፓሪስ ይኖራል። በረከት ሰምዖን አብሯት የምትኖትረው ታናሽ እህቱ ሃና አምዖን በፓሪስ የኤርትራ አምባሳደር ናት። ሩት ሰምዖን ደግሞ በኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር መስሪያ ቤት ውስጥ በጋዜጠኛነት የምትሰራና አሁንም ድረስ አስመራ ውስጥ በስራ ላይ የምትገኝ ወይዘሮ ናት።

ከብአዴኑ በረከት ሰምዖን ሌላኛው የተምታታ ታሪኩ «የሁለት ምርጫዎች ወግ» ሲል የደረተውን የወያኔ ማኒፌስቶ በመታሰቢያ ገጸ በረከትነት እንዲውል ያደረገበት ጉዳይ ነው። የብአዴኑ በረከት በመጽሐፉ መግቢያ ላይ መጽሐፉን «መታሰቢያነቱ ለወንድሜ ለካሳሁን ገብረሕይወት» ይሁን ይላል። የኢሕአፓ ታጋይ የነበረው መንድሙ ካሳሁን ገብረሕይወት የሞተው ወያኔና ኢሕአፓ አሲምባ ላይ ባደረጉት ጦርነት ነው። ባጭሩ የብአዴኑ በረከት ሰምዖን ወንድም ካሳሁን ገብረሕይወት የተገደለው ከወያኔ በተተኮሰ ጥይት ነው። በረከት ግን «የሁለት ምርጫዎች ወግ» ሲል የጻፈውን የወያኔ ማኒፌስቶ መታሰቢያ ያደረገው በወያኔ ጥይት ለተገደለው ለወንድሙ ለካሳሁን ገብረሕይወት ነው። በረከት «የሁለት ምርጫዎች ወግ» ሲል የደረተውን የወያኔ ማኒፌስቶ በወያኔ ጥይት ለተገደለው ወንድሙ ያበረከተው ምን ለማለት ፈልጎ እንደሆነ ባብስ ባስብ ትርጉም ላገኝለት አልቻልሁም። ለነገሩ ትርጉሙን በረከት ራሱ ቢጠየቅ መግለጽ የሚችል አይመስለኝም። በረከት እንዲህ ከራሱ የተጣላ ሰው ነው። ዐማራ ሳይሆን አማራ ነኝ፤ መብርሀቱ ገብረሕይወት ሆኖ ሳለ ሙሉ በሙሉ ስሙን ቀይሮ ባልሞተ ሰው ስም በረከት ስምዖን ነኝ የሚል በሽተኛ ነው።
በረከት እያወቀ ይሆን ተስቶት ባላውቅም «የሁለት ምርጫዎች ወግ» በሚለው መጽሐፉ ግን አንድ እውነት ተናግሯል። በመጽሐፉ መግቢያ ላይ መታሰቢያ በሚለው ገጽ «ለወንድሜ ለካሳሁን ገብረህይወት መታሰቢያ ይሁን» ካለ በኋላ «እነሆ በተለምክልኝ መንገድ እጓዛለሁ» ይላል። በረከት ሰምዖን «የሁለት ምርጫዎች ወግ» የሚለውን መጽሐፉን ያበረከተለት ወንድሙ ካሳሁን ገብረሕይወት የኢሕአፓ ታጋይ እንደነብረ ከፍ ብዬ ገልጫለሁ። ኢሕአፓ የተፈጠረውና የታገለው «የዐማራ ማን አህሎኝነት የወለደው የብሔር ጭቆና አለ» ብሎ ነበር። ይህ ማለት ኢሕአፓ የታገለው «ጨቋን» ያለውን ዐማራን ለማጥፋት ነበር ማለት ነው። በዚህ ረገድ የብአዴኑ በረከት ሰምዖን አልተሳሳተም። ወንድሙ ካሳሁን ከኢሕአፓ ጋር በረሃ የወረደው ዐማራን ለማጥፋትና ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነበርና። የኢሕአፓው የካሳሁን ገብረሕወት ታናሽ ወንድም መብራህቱ ገብረሕይወት ወይንም በሚንስትር ስሙ በረከት ሰምዖን በታላቅ ወንድሙ ተጽዕኖ ይሄው እስከዛሬ ዐማራን ለማጥፋትና ኢትዮጵያን ለመበታተን እየሰራ ይገኛል።

ስለዚህ የብአዴኑ በረከት በጻፈው መጽሐፍ መታሰቢያ ገጽ ላይ እንዳሰፈረው ኢሕአፓው ካሳሁን ገብረሕይወት የድርጅቱን የኢሕአፓንና ተልዕኮ የሰጠውን የሻዕብያን አላማ ለታናሽ ወንድሙ ለካሳሁን ወይንም ካሳሁን ከሞተ በኋላ በሚታወቅበት ስሙ በረከት እየተባለ ለሚጠራው ወንድሙ አውርሷል። ምንም እንኳ ኢሕአፓው ካሳሁን በወያኔ ጥይት ቢገደልም አላማውንና የተከተለውን መንገድ ግን የናቱ ልጅ ታናሽ ወንድሙ ከግብ አድርሶለታል። ከሳሁን ዛሬ በሕይወት ቢኖር ኖሮ እንደ እውነተኛው በረከት ሰምዖን እህት እንደ ሃና የእናት ድርጅቱ የሻዕብያ ማእከላዊ ኮምቴ አባልና የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን ይሆን ነበር።

ከሰሞኑ ደግሞ ሰውየው [በረከትን ማለቴ ነው] መሄጃ እየፈለገ እንደሆነ የሚነገረው የሚታይ ቢሆንም ኢትዮጵያን ይዟት ገደል ሳይገባ ግን መሄጃ የሚፈልግ አይመስለኝም። በስውር የሚሰራውን ባናይ እንኳ በረከት ባንደበቱ የሻዕብያ ሰላይ የነበረው ኢሕአፓው ወንድሙ በተለመለት የሻዕብያ መንገድ እየተጓዘ እንደሆነ የነገረንን ግን መርሳት ያለብን አይመስለኝም። የሆነው ሆኖ በረከት ሰምዖን ኢትዮጵያን ይዟት ገደል ሳይገባ መሄጃውን የፈለገ እንደሆነ ሻዕብያ ላገራችን ትልቅ ውለታ እንደሰራተሚቆጠርለት ይመስለኛል።

16 Comments

16 Comments

 1. በለው!

  October 17, 2017 at 7:55 pm

  ** የብዝሃነትና የህዳሴ ዘመን አልቆ “መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ከፍታ ዘመን ነው!”ሲባል ከፍተኛ የፖለቲካ ተላላኪና አሽቃባጮች ወደታች የመውረጃቸው ዘመን የሆነው ለምንድነው!? ህወሓት እነሱ ላይ ቆሞ ነበር ወይስ እንዳይንቀሳቀሱ አቁሟቸው ነበር? ከዱ! ሸሹ! ወረዱ! ተባረሩ!ለቀቁ! በቃኝ አልቀጥልም አሉ ሲባል ግን ምኑን ነው?
  ___” ከትጥቅ ትግል ጀምሮ ዛሬም በኢህሓዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ትውልደ ኤርትራውያንና ኤርትራውያን አሉ እኔም ኤርትራዊ ነኝ አባታቸው ስብሃት ነጋ…ህወሓት ሻቢያ ኦነግ ወደብ አስረከበው የተገነጠሉት ከአማራ ብቻ ነበር?
  ** ብአዴን ማነው? የማነው?
  ** “ኢሕዴን እዚያው ትግራይ ውስጥ የሕወሓት «የጡት ልጅ» ሆኖ እንደተመሰረተ ለነአንበርብር ቡድን በመጀመሪያ ወታደራዊ ስልጠና የሰጣቸው የወያኔው የቀድሞው የመከላከያ ሚንስትር የነበረው ስዬ አብርሀ ነበር። የስዬን ስልጠና እንደጨረሱ ኢሕዴኖች መሳሪያ ታደላቸውና ወያኔ «በአማራ አገር» በሚለው ምድር ለሚደረገው የሕወሓት ትግል በመንገድ መሪነትና በአማርኛ አስተርጓሚነት ተመደቡ።”
  ___ ህወሓት መሳደብ ሲያምረው በረከት ስምዖንን ጎጃም ይልካል በአንድ የሜዳ ላይ ንግግሩ”ነፍጠኛውንና ትምክህተኛውን፡ የድሮ ናፋቂውን እንታገላለን!” ሲል ሁሉም ያጨባጭባል ጎጃም አማርኛ አይችልም? ወይስ ሰውዬው ይቺን ባዶ ሜዳ እንዴት ደፈራት? ብዬ ነበር…«በአለም ላይ የመጨረሻ ድሀ ክልል» የተባለውን የዐማራ ክልል ከፍተኛ በጀት ለበዓሉ ማክበሪያ መድቦ አክብሯል። ብአዴን በዐማራ ገንዘብ ድል አድርጎ ያከበረው የ፴፭ኛ ዓመት የንግሥ በዓሉ ድርጅቱን የመሰረቱት ወያኔና ሻዕብያ ዐማራን እንዲያጠፋና በተገኘበት ሁሉ እንዲያሳርድ ስላደረገው አስተዋጽኦ ነው።”እዚች ላይ ግን የሀላዊ ዮሴፍና በረከት ስምዖንን የሀዘን የሻማ ማብራት ሥነሥርዓት፡ ዕንባ አዘል ንግግሮች በደንብ አድምጠን የስንብት እንደሆነ ተረድተነዋል!።
  ** በረከት «የሁለት ምርጫዎች ወግ» መጣፍ ለነገሩ ትርጉሙን በረከት ራሱ ቢጠየቅ መግለጽ የሚችል አይመስለኝም። በረከት እንዲህ ከራሱ የተጣላ ሰው ነው። ዐማራ ሳይሆን አማራ ነኝ፤ መብርሀቱ ገብረሕይወት ሆኖ ሳለ ሙሉ በሙሉ ስሙን ቀይሮ ባልሞተ ሰው ስም በረከት ስምዖን ነኝ የሚል በሽተኛ ነው።”
  ___ በመጽሐፍ ምርቃቱ ላይ የተገኙ ማጅራቱን ይዘው ለሕክምና ባንኮክ የላኩት አላሙዲን “መጽሐፉን አላነበብኩትም ግን ለመጭው ትውልድ እንደሚጠቀም አምናለሁ”አሉ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁሃን ናቸው እኛም ፳፮ ዓመት ዲሞክራሲና ዕድገትን ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ሁለተኛ መሆናችንን አምነን ፳፪ ቢሊየን ዶላር ዕዳ ፲ሚሊየን ተመጽዋች ፵፭ ከመቶ ሥራአጥ ትውልድ ይዘን ዙሪያውን በቋንቋና ነገድ ተቧድነን በሜንጫ ስንጨፋጨፍ በዜና እወጃ ላይ አምነን ተቀብለን ተለማምደነው የለምን!?ለነገሩስ ብንሞት ብንሰደድ፡ በሱስ ብንደነዝዝ ቆጥሮ ያስረከባቸው የለም፡እራሱን ያስረከበ ባለቤት አልባ ሕዝብ..
  **የሆነው ሆኖ በረከት ሰምዖን ኢትዮጵያን ይዟት ገደል ሳይገባ መሄጃውን የፈለገ እንደሆነ ሻዕብያ ለሀገራችን ትልቅ ውለታ እንደሰራ ተሚቆጠርለት ይመስለኛል። የበረከት ሌጋሲ ““አንድ ለአምስት የሚባለውን መዋቅር ጨምሮ ድርጅቱ በጣም ግዙፍ የበላይ ጠቅላላ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችን ሁለንተናዊ ሕይወት እንዲቆጣጠር የሚያስችል መዋቅር በመዘርጋት የሚታወቁ ናቸው አቶ በረከት። ያልተማሩ እና በደንብ ያልሰለጠኑ የክልል የፖለቲካ ካድሬዎችን በመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ በመሰግሰግ ግንባር ቀደም ሚና የነበራቸው ናቸው።”
  ___ ህወሓት የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ፓሊሲ መቀየር ንድፍ..የጻድቃን ገ/ተንሳይ የወደብ ተማፅኖ..ነገር አላት። የተስፋዬ ግብረእባብና የአንበርብር ወግ በአስመራ ታማኝ ሰው ሲያስፈለግ ነቅሎ በመትከል ልምዳቸው መብርሃቱ ገብረሕይወት የአዲሲቷ ኤርትራ ልዩ ተጠሪ ሆኖ ሊቀጥል ነው። ግን ይህ ሁሉ የተሰባበረ ዜና ከሚሰሩት ሥራ ስለወጡ ከሀዘን ነው ወሬ አልቆ!?

 2. Analyst

  October 17, 2017 at 8:26 pm

  Good analysis

 3. yimer

  October 18, 2017 at 1:05 am

  የዲያቢሎስ ቀንድ ተሰበረ

 4. NANA

  October 18, 2017 at 2:22 am

  …«በአለም ላይ የመጨረሻ ድሀ ክልል»

  YOU KNOW WHY . YOU DO NOT HAVE WORKING CULTURE .
  ENVY HAS TO BE ABOLISHED AND TEAM WORK MUST BE PROMOTED .
  A CULTURE FULL OF PEOPLE WITH EMPTY BRAVADO AND HATE WILL NOT MAKE U RICH .

  THOSE LIVING OUT SIDE ARE ALSO GOOD AT SHOUTING AND FORMING SENSELESS ORGANIZATIONS . THEY DO NOT CONTRIBUTE A BIT FOR THE BETTERMENT OF THEIR PEOPLE .

  THEY CLAIM THEY LOVE THEIR PEOPLE . BUT IS ONLY EMPTY TALK .

 5. Medihanit

  October 18, 2017 at 7:15 am

  Aite Bereket belongs to the Eritrean Tigre ethnic group and does hate the Amharas as a whole. The Author should note that there are about 9 nationalities in Eritrea but the Tigrigna speakers dominate the political power in the country. The Eritrean Tigres despise their kins to the south of the Mereb river and call them with their generalizing name Agame.They associate Agames with immorality wickedness and evilness. The TPLF leadership is under the persons with Eritrean Tigre blood who feel superior to the Tigres of Tigray.The Tigray nationalists have been accusing the late TPLF master Meles Zenawi and his cliques of favoring Eritrean Tigres. This accusation was one of the reasons for the dismissal of Tigray nationalists from the TPLF top. As an Eritrean Tigre and loyal of Meles Zenawi, Berekt rose to prominence in the TPLF after the dismissal of Tigray nationalists. The so called Amhara National Movement is a Tigray Tigre organization and arm of the TPLF. It is the instrument the TPLF uses to control and kill the Amharas. In the other regions the TPLF uses its organizations such as the Oromo OPDO to displace and kill the Amharas. The Oromo people have nothing to do with the killings and displacements of the Amharas.

 6. ዝምታ ወርቅ አይደለም

  October 18, 2017 at 8:05 am

  ለምን የህብረ-ብሄር አንድነት ሀይሉ በአለፋት 50 አመታት በጎጥ ሀይሎች እንደተሸነፉ ፤ አማራው በአማራዊነት ስር መደራጀት እንዳለበት የሚያሳይ በጥናት ላይ የተሞረከዝ አስተማሬ ፅሁፍ። የአቶ በአሉ ግርማ ኦሮማይ መፅህፋ ፍሬ ነገር ተጨምቆ ባጭሩ።

 7. NANA

  October 18, 2017 at 8:18 am

  SOURCE -REPORTER

  የአገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ ትኩሳት ከአገርና ከሕዝብ ዘለቄታዊ ህልውና ጋር ሲነፃፀር፣ በግራ መጋባትና በውዥንብሮች መሞላቱ ግልጽ ነው፡፡ በተለይ በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች አመራሮች መካከል መቃቃር ተፈጥሯል ተብሎ በአደባባይ መሰማት ከጀመረ መሰነባበቱ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ በቀናት ልዩነት ውስጥ የድርጅቱ ነባር አመራሮች ከያዙት ኃላፊነት በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው መሰማቱ በድርጅቱ ታሪክ አዲስ ቢሆንም፣ በአባል ድርጅቶች መካከል የነበረው መስተጋብር ግን እንደ በፊቱ እንዳልሆነ ግን ግልጽ እየሆነ ለመምጣቱ ሌላው ማሳያ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ ላለፉት 26 ዓመታት በላይ አገር እንደ መምራቱ መጠን፣ በውስጡ የሚካሄዱ ሽኩቻዎች ወይም ልዩነቶች የሕዝብንና የአገርን ሰላም ማናጋት አይኖርባቸውም፡፡ የአመራሩ ፍላጎት ከሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች አፈንግጦ በሌላ አቅጣጫ የሚነጉድ ከሆነ፣ የአገርና የሕዝብ ህልውና ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ ይሆናል ተብሎ የሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅምና ህልውና፣ ከምንም ነገር በላይ እንደሚበልጥ ማመን ይገባል፡፡

  ላለፉት ሦስት ዓመታት በአገሪቱ የተለያዩ ሥፍራዎች የተከሰቱ ተቃውሞዎች ደም አፋሳሽ ስለነበሩ የበርካታ ዜጎች ሕይወት ተቀጥፏል፡፡ ብዙዎች ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በርካታ የአገር ሀብት ወድሟል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች አሁንም የተቃውሞ ድምፆች ይሰማሉ፡፡ ለችግሮች መፍትሔ ተገኝቶላቸው ሰላምና መረጋጋት በመፍጠር መሠረታዊ ለውጦችን ለማምጣት መሥራት ሲገባ፣ እንዲህ ዓይነት የተቃውሞ ድምፆች መሰማት መቀጠላቸው ያለ ነው በማለት መገላገል አይቻልም፡፡ በውስጥ ሽኩቻም ሆነ በሌላ ምክንያት የነባር አመራሮች በቃኝ ማለት ሳይሆን ዋናው ቁም ነገር በአገሪቱ ለሰላም፣ ለዴሞክራሲና ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት የሚጠቅሙ ተግባራት በአግባቡ እየተከናወኑ ነው ወይ የሚለው ነው የሚያሳስበው፡፡ የትኛውም አመራር በሆነ ጊዜ ሊበቃው ይችላል፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን፡፡ ልዩነትን አክብሮ ሁሉንም አሳታፊ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ዓውድ በመፍጠር ሕዝብን ማረጋጋት ደግሞ የመንግሥት ኃላፊነት ነው፡፡ ከአገርና ከሕዝብ በላይ ምንም ነገር ስለሌለ፡፡

  በአሁኑ ጊዜ በሕዝብ ውስጥ በርካታ መረጃዎች ይሠራጫሉ፡፡ ምንጫቸው ከማይታወቅ ተራ ጉዳዮች እስከ ትልልቅ አገራዊ ጉዳዮች ድረስ የሚሠራጩት ብዙዎቹ መረጃዎች፣ እንደ አገርና እንደ ሕዝብ የመቀጠልን ተስፋ የሚያጨልሙ ናቸው፡፡ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማኅበረሰብ እንደሚፈጥር የሚጠበቀው ፌዴራላዊ ሥርዓትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ ድርጊቶችን ማስቆም ሲገባ፣ በሥርዓቱ ላይ የሚቀርቡ ትችቶች ላይ ብቻ መንጠላጠል አይገባም፡፡ ለኢትዮጵያ ከፌዴራል ሥርዓቱ ውጪ ማሰብ እንደማይቻል ግልጽ ነው፡፡ ይህ ክርክር ጊዜ ያለፈበትም ነው፡፡ ነገር ግን የፌዴራል ሥርዓቱ ባለቤት ነን የሚሉ ወገኖች በሚፈጥሩት ችግር ሕዝብ ሲሞት፣ ጉዳት ሲደርስበትና ከቀዬው ሲፈናቀል ምክንያቱን አብጠርጥሮ የማወቅና የማስረዳት ኃላፊነት የመንግሥት ብቻ ነው፡፡ እግረ መንገዱንም በፌዴራል ሥርዓቱ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በሰከነ መንገድ አይቶ የማስተካከል ኃላፊነትም እንዲሁ፡፡ ከአገርና ከሕዝብ በላይ ማን አለ?

  የገዥው ፓርቲ አባል ድርጅቶችና የክልሎች አመራሮች እንደ ወትሮው እየተናበቡ መሥራት ቢያቅታቸው እንኳ፣ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ በሠፈሩ ድንጋጌዎች አማካይነት ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው፡፡ ለዘመናት የተጠራቀሙ የሕዝብ ብሶቶችና ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት ከሕገወጥ ድርጊቶች ይልቅ ለሕግ የበላይነት መገዛት ሲቻል ነው፡፡ በተለያዩ መንገዶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰሙ ድምፆች መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲህ ዓይነት ድምፆች ሲሰሙ ሊኖር የሚገባው ፈጣንና አስተማማኝ የሆነ መረጃ ነው፡፡ ሕዝብ በየጊዜው በሚደርሱት መረጃዎች ሳቢያ የወደፊት ዕጣ ፈንታው ሲያሳስበው፣ በጠንካራ ቁመና ላይ የሚገኝና አስተማማኝ መረጃ የሚሰጥ መንግሥታዊ አካል መኖር አለበት፡፡ የእዚህ አካል ፋይዳው ሕዝብን ለማረጋጋት ብቻ ሳይሆን፣ የአገርን ውሎና አዳር በአግባቡ ለማወቅ ይጠቅማል፡፡ አሉ የሚባሉት የአመራሮች ክፍተቶችና መቃቃሮች ደረጃም ይታወቃል፡፡ ይህ ለምን ይጠየቃል? ምክንያቱም የአገሪቱ ሕገ መንግሥት የመንግሥት አሠራር ለሕዝብ ግልጽ መሆን እንዳለበትና ተጠያቂነቱም በዚያው ልክ መሆኑን ስለደነገገ ነው፡፡ ሕግ ደግሞ መከበር አለበት፡፡

  የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ያስተሳሰረው የሰላም፣ የአንድነትና የፍቅር ገመድ እንዳይበጠስ ምን መደረግ አለበት መባል ይኖርበታል፡፡ ይህ ኩሩና ጨዋ ሕዝብ ከሚጠቀሱለት የጋራ እሴቶች መካከል ዋነኛው ለአገሩ ያለው ጥልቅ ፍቅር ነው፡፡ ይህ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ የዘመናት እሴት ሊከበር ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው የጀግኖችና የጨዋ ኢትዮጵያውያን አገር ለዘመናት ወራሪዎች ቢፈትኗትም አልተሳካላቸውም፡፡ ይህች ታሪካዊ የጀግኖች አገር ህልውናዋ አስተማማኝ ሆኖ መቀጠል አለበት፡፡ ማንኛውም የፖለቲካ ፍላጎት ወይም ጥቅም ከአገር በላይ አይደለም፡፡ ሆኖም አያውቅም፡፡ አስተዋዩና ጨዋው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምንም ነገር በላይ የሚያሳስበው የአገሩ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ይህንን ሕዝብ ማክበር ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዱን ጉዳይ ፖለቲካዊ ገጽታ በማላበስ ከተወሰኑ በድኖች ዕይታ አንፃር ብቻ ማንገዋለል ለአገር አይበጅም፡፡ ግለሰቦች ያልፋሉ፣ አገር ግን አታልፍም፡፡ ይልቁንም የትውልድና የታሪክ ተጠያቂ ላለመሆን ጥረት ማድረግ ይበጃል፡፡ ከአገርና ከሕዝብ በላይ ምንም ስለሌለ፡፡

  ሁሌም እንደምንለው መንግሥት ሕዝብን ማዳመጥ አለበት፡፡ ሀቁን ብንነጋገር ሕዝብ የመንግሥት ቀጣሪ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ከፌዴራል መንግሥቱ በተጨማሪ ክልሎችን ይመለከታል፡፡ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት ሕዝብን ያክብሩ፡፡ ለሕዝብ ፍላጎት ይገዙ፡፡ ሕዝብን አለማዳመጥ ነው ብዙ ችግሮችን የወለደው፡፡ በተለያዩ ጎራዎች የተሠለፉ የፖለቲካ ኃይሎችም ለሕዝብ ፍላጎት ራሳቸውን ማስገዛት አለባቸው፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰማሩም ቢሆኑ ይህ ኃላፊነት ይመለከታቸዋል፡፡ አገር የምታድገውና የምትበለፅገው ሰላም ሲኖራት ነው፡፡ ሰላም ከሌለ ንፁኃን ለአደጋ ይጋለጣሉ፡፡ አገር ትተራመሳለች፡፡ በዚህ መንገድ ደግሞ መቼም ቢሆን አገር መምራትም ሆነ፣ እንደምንም ብሎ ሥልጣን ላይ መውጣትም አይቻልም፡፡ በመከባበርና በመተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ውይይትና ክርክር ማድረግ ሲገባ፣ ያንን የተለመደ ጨፍጋጋና ጨለምተኛ መወነጃጀል ማስቀጠል ለማንም አይጠቅምም፡፡ ከዚህ በፊት ያፈራው ፍሬም የለም፡፡ አሁን መንግሥት ከመቼውም ጊዜ በላይ ማሰብ ያለበት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላም፣ በአንድነትና በፍቅር ለመኖር የሚያስችለውን አሳታፊ ዴሞክራሲያዊ ዓውድ ስለመፍጠር ነው፡፡ ከዚያ ውጭ ያሉ ድርጊቶች ለአገር አይበጁም፡፡ ከሕዝብና ከአገር በላይ ምንም ነገር የለም!

 8. NANA

  October 18, 2017 at 8:19 am

  NICE PIECE FROM REPORTER

  ሁሌም እንደምንለው መንግሥት ሕዝብን ማዳመጥ አለበት፡፡ ሀቁን ብንነጋገር ሕዝብ የመንግሥት ቀጣሪ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ከፌዴራል መንግሥቱ በተጨማሪ ክልሎችን ይመለከታል፡፡ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት ሕዝብን ያክብሩ፡፡ ለሕዝብ ፍላጎት ይገዙ፡፡ ሕዝብን አለማዳመጥ ነው ብዙ ችግሮችን የወለደው፡፡ በተለያዩ ጎራዎች የተሠለፉ የፖለቲካ ኃይሎችም ለሕዝብ ፍላጎት ራሳቸውን ማስገዛት አለባቸው፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰማሩም ቢሆኑ ይህ ኃላፊነት ይመለከታቸዋል፡፡ አገር የምታድገውና የምትበለፅገው ሰላም ሲኖራት ነው፡፡ ሰላም ከሌለ ንፁኃን ለአደጋ ይጋለጣሉ፡፡ አገር ትተራመሳለች፡፡ በዚህ መንገድ ደግሞ መቼም ቢሆን አገር መምራትም ሆነ፣ እንደምንም ብሎ ሥልጣን ላይ መውጣትም አይቻልም፡፡ በመከባበርና በመተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ውይይትና ክርክር ማድረግ ሲገባ፣ ያንን የተለመደ ጨፍጋጋና ጨለምተኛ መወነጃጀል ማስቀጠል ለማንም አይጠቅምም፡፡ ከዚህ በፊት ያፈራው ፍሬም የለም፡፡ አሁን መንግሥት ከመቼውም ጊዜ በላይ ማሰብ ያለበት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላም፣ በአንድነትና በፍቅር ለመኖር የሚያስችለውን አሳታፊ ዴሞክራሲያዊ ዓውድ ስለመፍጠር ነው፡፡ ከዚያ ውጭ ያሉ ድርጊቶች ለአገር አይበጁም፡፡ ከሕዝብና ከአገር በላይ ምንም ነገር የለም!

 9. Solomon

  October 18, 2017 at 10:27 am

  ኣቻምየለህ ይህን የጻፍከው ከተስፋየ ገ/ኣብ ጽሁፍ ገልብጠህ ነወ የጻፍከው። ማረጋገጥ ለሚፈልግ Tesfaye Gebreab|Jontambek’s Blog ማግኘነት ይቻላል።

 10. በላቸው

  October 18, 2017 at 12:21 pm

  እኔ የገረመኝ የግ7 ሰዎች በረከት ሰማዕንን ሽንጣቸውን ገትረው በfb በሬዲዎ ሲከላከሉለት አና ሲያደንቁት በማየቴ በጣሙን ገርሞኛል፡፡እረ ጎበዝ ጉድ ነው፡፡

 11. Tamirat

  October 18, 2017 at 1:12 pm

  አቶ አቻምየለህ ታምሩ የከተቡትን የሕወሓቱ ጆሴፍ ጎብልስ፤የኢሕአፓው አንበርብር፤ የሻዕብያው በረከት ሰምዖን መጣጥፍ እያነበብኩ በሃሳብ ግን ወደ ኤርትራ በርሃ ነበር የተጎዝኩት ለምን ቢባል በኤርትራ በሻቢያ እጅ ስር ያሉት የኢትዮጵያ የክፉ ቀን ልጆች ታስበውኝ:: በሌላ በኩል ደሞ እውነት ይህንን ታሪክ በአሁኑ ሰዓት በኤርትራ ውስጥ ያሉ የኢትዮጵያዊ ድርጅት መሪዎች አያውቁ ይሆን? ከነዚህ ውስጥስ የቀድሞው የኢሕአፓ አባላቶች ይታጡ ይሆን:: ለነዚህ የድርጅት መሪ ወንድሞቻችን የምላቸው ነገር ቢኖር “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” የሚለው አባባል ለወያኔ አመራሮችና ለሻቢያ መሪዎች አይሰራም:: ምክንያቱም ወያኔና ሻቢያ “የሳሎን ጸበኞች የጎዳ ፍቅረኞች” ነቸውና::

 12. ydidiya

  October 18, 2017 at 4:55 pm

  ውድ ሠለሞን! ድንቅ ታዘበሃል የዚህን ልታይ ልታይ ባይ ግብዝ ሰው ገመና።
  አቻምየለህ እኮ ሌላው በእነ በረከት የተላከ ጥብቅ የዲያስፖራው አህዴን ነው። በቅርቡ በ2016 የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጉዳይ በተቀጣጠለበትና የጎንደር ህዝብ ታሪካዊውን ሠላማዊ ሰልፍ ባደረገበት ወቅት ከየት መጣ ሳይባል ከስፔስ እንደወደቀ ምትህት ብቅ ብሎ ወደ ዲያስፖራው የተቀላቀለው አቻምየለህ ታምሩ ላቡ ሳይደርቅ “ፍየል ከመድርሷ ቅጠል መበጠሷ” አይነት ነገር፣ በየሚዲያው እራሱን ለመሸጥ ወይም ለማስተዋወቅ ብዙ ቦታ ረግጧል። ልታይ ልታይ ባይነቱንም ለማረጋገጥ ከሄደበት አንዱ፣ ለምሳሌ በሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዎርጊስ አማካኝነት የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንፍረንስ ላይ አማራን ወክሎ ተጋባዥ እንግዳ ሆኖ የቀረበውን ብናስታወስ አንዱ ገራሚ ቢዝነስ ማን መሆኑን ጠቛሚ ነው ። ወዲያው ደግሞ ተጣላና በተጋበዘ በማግስቱ ጋባዦቹን የሚያብጠለጥል እና አንባቢንም የሚያሰለች ረጅም ጽሁፉን ጽፎ ኮምፕሌኑን ጀመረ። ጃዋርም ዲያስፖራን እንደ አዲስ ሲቀላቀል ልክ እንደ አቻምየለህ እንዲህ ነበር የተንቀዥቀዥው። ሁሉም ጋ ረገጠ። ሁሉንም በረገጠ በሳምንቱ ሁሉንም ማውገዝ ጀመረ። ወዲያው ደግሞ “ኦሮሞ ፈርስት” ብሎ በአልጀዚራ፤ በቪኦኤ፤ በዶቼበሌ ወዘተ… ምደር ቁና ትሁን ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ አለ። አሁን ግን ሰልፉ ማ ጋ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ሆነ ወጣና መጋረጃው ተገፈፈ። አቻምየለህም 26 ዓመት ሙሉ ሲነገርና ሲጻፍ የኖረውን የትግሬ ወያኔን”ኢህአዴግ” አዉሬነት፣ ዛሬ እሱ ደርሶ የተደበቀ ምስጢር ያጋለጠ ይመሰል በየድረገጹ አንብቡኝ እያለ ይጎፈላል። አሁን ደግሞ ጭራሽ ከተሰፋዬ ገብረአብ ከርጆ የጻፈውን ጽሁፍ ልክ እንደ አዲስ መረጃ ጎብልስ፣ ጆሴፍ ስታሊን ወዘተ እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ ኣጃኢብ ነው። የሚደንቀው ደግሞ የዛሬ 50 ዓመት በፊት ያ የተቀዥቀዥ ትዉልድ ያመጣውን ብሄር ብሄረሰብ የሚል ጣጣ ራሱ እየረገመ እሱ ግን በረገመው ትዎሪ መርቅኖ በብሄረ ሰብ አጥር ታጠረና “አማራ ፈርስት”እያለ ሜንጫ መታጠቅ ቀረው እንጀ የከሸፈውን ጃዋር መሐመድ መምሰሉ ያጋጣሚ ወይስ ተለዕኮ ብንል ምን ይገረማል!? እሳት ካየው ምን ለየው። የአቻምየለህ የ”አማራ ፈርስት” ተለዕኮ የእነ በረከት ሲሆን የጃዋሩ “ኦሮሞ ፈረሰ” ተለዕኮ ደግሞ የእነ አባዱላ እና የትግሬው ወያኔ ቅሪት ለመሆኑ ዛሬ ዛሬ ተጋልጧልና ኢንሻላህ ! ነገም ሌላ ቀን ነው እና የነገ ሰው ይበለን እስቲ!!

 13. Gedif

  October 18, 2017 at 7:01 pm

  The writer of this article is full of hatred towards other Ethiopians. For me Bereket is a hero who sacrificed and dedicated his life for his country. Zim bilo ye tilacha kalat eyedenegoru ye haset ena ye fetera lib woled maserachet maninetihen ke masayet wuchi minim ayfeyidim. As one guy once told you,you need to read before writing an article. Bereket never ever compared to Goebbels. Be truthful for yourself. Mejemeria libehin kefteh yewustihen tilacha aswegid.Bante ye zewetir yehaset ena tilacha tsihuf mikniat gosahin atasedib.lenegeru ante maninim atiwekilim.

  • በላቸው

   October 18, 2017 at 10:30 pm

   Do bereket has a country? which one?

 14. Mulugeta Andargie

  October 18, 2017 at 7:33 pm

  ጉዳያችንን ከውጭ ዜጋ ጋር ኣታገናኙት!!! ኤርትራ ነጻነቷን ካገኘች ብዙ ጊዜ ኣስቆጥራለች!!! እኛ ኢትዮጵያውያን ነን!! የምናወራውም ስለሃገራችን እንጂ ስለሌላው ኣያገባንም!!

 15. ታዘበ

  October 20, 2017 at 12:42 pm

  አቻምየለህ ፅሑፍህ ብዙ ስም አጥፊ የወያኔ ቅጥረኛ ድረገፅ “ፀሐፊዎችን” / ሽልንጌዎችን/ ምን ያህል እንዳበሳጫቸው አየህ !!!! ሆድ አደር ትርክምርኪ የገደል ማሚቶዎች !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top