News Feature

የእግር ኳስ ቡድኖች ደጋፊዎች በወልዲያ ተጋጩ (የጀርመን ድምጽ ራድዮ ዘገባ)

የወልዲያ ከተማ እና የመቀሌ ከተማ የእግር ኳስ ቡድኖች ደጋፊዎች ወልዲያ ከተማ ውስጥ ዛሬ ተጋጩ። በግጭቱ ሰዎች መቁሰላቸውን እና ሕንፃ መቃጠሉን የዐይን እማኞች ተናግረዋል። ሁኔታውን በጣም አስጊ ነው ሲሉ የገለጹ የዐይን እማኝ እንደሚሉት ግጭቱ በደጋፊዎች መካከል ይፈጠር እንጂ የብሔር ግጭት መልክ ይዟል ብለዋል።

የወልዲያ ከተማ እና የመቀሌ ከተማ የእግር ኳስ ቡድኖች ደጋፊዎች ወልዲያ ከተማ ውስጥ ዛሬ ተጋጩ። በግጭቱ ሰዎች መቁሰላቸውን እና ሕንፃ መቃጠሉን የዐይን እማኞች ተናግረዋል። ሁኔታውን በጣም አስጊ ነው ሲሉ የገለጹ የዐይን እማኝ እንደሚሉት ግጭቱ በደጋፊዎች መካከል ይፈጠር እንጂ የብሔር ግጭት መልክ ይዟል ብለዋል። ስድብ እና ግርግር በወልዲያ ከተማ እንደነበር የተናገሩ ሌላ የዐይን እማኝ የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸውን እና ውሃ መርጨታቸውን ተናግረዋል።

የደሴ ነዋሪ እንደሆኑ የገለጡልን አድማጫችን ወልድያ የተገኙት በአጋጣሚ ነበር ወዳጃቸውን ለመጠየቅ። ጠዋት ሦስት ሰአት አካባቢ «ግርግር አለ ሲባል ለማየት» መውጣታቸውን ገልጠዋል። «የሆነ ደስ የማይል ስድብ ነበር» ሲሉም በሁለቱ ደጋፊዎች መካከል ግጭት ያጫረውን ምክንያት አክለዋል። «ከአካባቢው ራቅ ለማለት ሞከርን» ያሉት የዐይን እማኝ «ተኩሶቹ እየጨመሩ ነው የመጡት» ብለዋል። ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ በበኩላቸው፦ «ያየሁት ነገር፤ አስለቃሽ ጋዝ ይተኮስ ነበር፤ ከየት እንደሆነ ባላውቅም ጥይቶች ድምፅ ይሰሙ ነበር» ብለዋል።

የአማራ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ግጭቱ መከሰቱን አረጋግጦ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ሊደረግ የታቀደው ጨዋታ «ላልተወሰነ ጊዜ» መራዘሙን ዘግቧል። የአማራ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ያነጋገራቸው የሰሜን ወሎ ዞን ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልባሴ አሊጋዝ «ጨዋታውን ለማድረግ የሚያበቃ የጸጥታ ቁመና ባለመኖሩ» ምክንያት መራዘሙን ገልጠዋል።

2 Comments

2 Comments

 1. Tesfa

  December 4, 2017 at 6:07 am

  የወያኔ አሰራር መከፋፈል፤ ማታለል ብቻ ነው። ጎንደር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን በአየር መንገድ ከጎንደር ሰባስቦ መቀሌ ላይ ያራግፋቸዋል። አድራጎቱ አለንላችሁ ለማለት እንጂ መቀሌ ላይ ለሚጠብቃቸው የኑሮ ጫና ዝግጅት አልነበረውም ደንታም አይሰጠውም። ልበ ቢሶቹ የትግራይ ልጆችም ወያኔ ለእነርሱ መጠለያ የሰጣቸው ስለመሰላቸው መንግሥትን ያመሰግናለሁ በትግሬነታቸውም አለቅጥ ይኮራሉ። ያልታያቸው ነገር ግን ወያኔ ለፓለቲካ ፍጆታው እንደተጠቀመባቸውና ከኢትዮጵያ ህዝብም ህብረትና አንድነት መራቃቸውን ነው።
  አሁን ኳስ በሚጠለዘበት ሜዳ በተለይም በመቀሌ፤ በባህርዳር፤ በጎንደር፤ በወልድያ የምናየው የጠብ ፈላጊነትም ባህሪ የወያኔ የጠበንጃ አፈሙዝ ውጤት ነው። እኔ በህይወት ዘመኔ የኳስ ቡድን በወታደራዊ ተሽከርካሪ ታጅቦ ለጫወታ ሲጓዝ አይቼም ሰምቼም አላውቅም። በደጋፊዎቹ እንጂ! ወያኔ ያው የሚያስበውና የሚተነፍሰው በጠበንጃው በመሆኑ ልብ ላለው ዘረኛውና ጎጠኛው ወያኔ አላማው መከፋፈል፤ ማጣላት፤ ማገዳደል በመሆኑ በኳስ አሳቦ የሰውን ሰቆቃ ማራባት ነው። ደስታቸው የወደቀ ሬሳ ማየት ነው።
  ዛሬ የሃገሪቱ መታመስ እኔ ምን አገባኝ በማለት የራስን ኑሮ ለማሸነፍ ሃተፍ ተፍ ለሚሉ ሁሉ አንድ ምክር አለኝ። ያ እሳት እናንተንም አይተውም። በጊዜው እሳት ባይበላቹሁ ጢሱ የሰራቹሁትን ያበላሸዋል። ለህዝባችን አንድነትና ህብረት ጎሳን፤ ዘርንና ሃይማኖትን ያልተገነ አቋም በመያዝ የወያኔን አጥፊ ሥራ እንጋፈጥ። ከዘመናት በፊት ኑረዲን ኢሣ በጻፈው ግጥም ልሰናበታችሁ።

  እኔ ምን አገባኝ የምትሉት ሃረግ
  እሱ ነው አገሬን ያረዳት እንደበግ
  የሚል ግጥም ልጽፍ
  ብድግ አልኩኝና
  ምን አገባኝ ብዬ ቁጭ
  አልኩ እንደገና፡፡

  • Nana

   December 4, 2017 at 11:53 pm

   YOU CAN NOT HIDE THE GENOCIDE IN GONDOR . IT IS WRITTEN IN HISTORY BOOKS

Leave a Reply

Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top