News Feature

የዶ/ር ደብረጽዮን እና የጌታቸው ረዳ የዝሙት ምስጢር ከፌስ ቡክ ወረደ


የቀድሞው ኮሚኒኬሽን ሚንስትር ዴኤታ አቶ ጌታቸው ረዳ እና የህወሃቱ ሊቀ-መንበር ደብረጽዮን ገብረማርያም ክፉኛ ተቋስለዋል። በስብሰባቸው ፊት ለፊት አይቀመጡም፤ አይን ለአይንም አይተያዩም። እንደ አባት ገዳይ ጥርስ በመናከስ እየተገለማመጡ ሰንብተዋል። ለግዜው አንዱ ሌላው ላይ እጁን አያነሳም። ምክንያቱም አሁን ትኩረታቸው የጋራ ጠላት ላይ መሆን አለበት። የፋኖ እና ቄሮ አንድ ቋንቋ መናገር፣ የኦሮማራ ፖለቲካ የሁለቱን ቂም አዳፍኖ አቆይቶታል።


ጸባቸው የሃገር ጉዳይ አይደለም። የሴት ጉዳይ ነው። ደብረጺዎን ጉልበቱን ተጠቅሞ ከጌታቸው ፍቅረኛውን ቀምቶታል። 


በቅጽል ስምዋ አኮራ ትባላለች። ወይዘሮ አስካለ ገብረኪዳን። በሙስና ሃብት ካካበቱ የህወሃት ባስልጣን ተጠግታ አካልዋን በመሸጥ ሚሊዮነር እንደሆነች ይነገራል። በተለይ ጌታቸው ረዳ እና ደብረጽዮን እንደ መንደር ዱርዬ እየተፈራረቁ ይይዙዋታል። እንደ ተውሶ እቃ እየተፈራረቁ ከስዋ ጋር ይተኙ ነበር። ሴትዮዋ አሁን ጠቅልላ ደብረጽዮን ቤት ውስጥ ገብታ ሚስት ተብላለች። በቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ውስጥ ቁጥር አንድ የተባለ ቡቲክ አላት፣ ግብር የማይመለከተው የአስመጪ እና ላኪ ፈቃድ አላት። በወጋገን ባንክ ላይም የአንበሳውን ድርሻ ይዛለች። እንደማንኛውም የባለስልጣን ሚስት በአሜሪካ ቪላ ቤቶች አስገንብታለች።


የሰሞኑ የፖለቲካ ቴርሞሜትር ከፍ ያለ ቁጥር እያሳየን ነው። በደብረስዮን ድል አድራጊነት ከውጭ የተረጋጋ መስሎ ቢታይም ውስጡ ግን እየቦካ ነው። ይህንን ደግሞ የወያኔ ባለስልጣናት ከሚናገሩት፣ ከሚጽፉት እና ከፊታቸው መቀያየር እናነባለን።


በፌደራል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፌስ ቡክ ገጽ ላይ የሰፈረ አንድ መረጃ የህወሃቶችን መንደር እያተራመሰ ይገኛል። በኮሚኒኬሽኑ ጉዳዮች ሃላፊ ሃዱሽ ካሱ እየተለቀቀ የነበረው ምስጢር ምንም እንኳን ከበድ ያለ ቢሆንም፣ የደደቢት ቅሪቶቹ በሃላፊነት የማይጠየቁ ጉልበተኞች ስለሆኑ ጉዳዩ እንደዋዛ ተድበስብሶ እንዲያልፍ እየተደረገ ይገኛል።


ተሸፍኖ የኖረ ጉድ ሁሉ እየተጎለጎለ መውጣቱ ስርሃቱ በወድቀት ዋዜማ ላይ እንዳለ ሹክ ቢለንም፣ ከእንዲህ አይነቱ የእርስ በርስ ውንጀላ ግን ሃገሪቱ በምን አይነት ዱርዬዎች እየተመራች እንደሆነ ይጠቁመናል። የተሸናፊነት ስነልቦና ውስጥ የተዘፈቀው አንደኛው የህወሃት ቡድን የሌላውን ቡድን ጉድ አደባባይ ላይ ሲያወጣው ሊደንቀን አይገባም።


በችሎታ ሳይሆን በዘር መስፈርት የፌደራል ኮሙኒኬሽን ዳሬክተር ተብሎ የተቀመጠው አይተ ሃዱሽ ካሱ የፌስ ቡክ ገጹ “ሃክ” ተደርጎብኛል ሲል ቢያስተባብልም፣ ተለቅቆ የነበረው መረጃ ግን መሬት ጠብ የማይል ሃቅ ነበር።
አብዛኞቹ የህወሃት ካድሬዎች በደብረጽዮን ድርጊቶች ተበሳጭተዋል እየተባለ ነው። ሰውዬው ዝሙተኛ ነው ብለው ያሙታል። ብዙውን ግዜ ቢሮውን ዘግቶ የፖርኖግራፊ ፊልም ሲያይ እንደሚውል በስፋት ይነገራል። ወያኔን ያላስደሰተው ይህ ድርጊቱ ሳይሆን ይልቁንም በፖለቲካው የትግራይን የበላይነት አለማስረገጡ ነው። የነ ለማ መገርሳ ልቆ መገኘት አንገብግቧቸዋል። ሰውዬውን በዝሙተኝነቱ ሳይሆን በዘገምተኝነቱ ያወግዙታል።


ሰውየው ምንም ያህል አርቆ ማሰብ የማይችል፣ ፍጹም ርህራሄ እና ስብእና የጎደለው ደካማ ግለሰብ እንደሆነ በአንድ ወቅት የተናገረው ነውር ቃል ምስክር ነው። “ሰራዊታችን እንኳንስ ለ30 ሚሊዮን (የአማራ)ሕዝብ አደለም፤ መላው አፍሪካን ለመደምሰስ አቅም እንዳለው የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ያረጋገጡት ሃቅ ነው።” ሲል ተናግሯል።


የነስብሃት ነጋ ወሬ አቀባይ፣ ጌታቸው ረዳም በብሄራዊ ቴሌቭዥን ወጥቶ የተናገረው ለታሪክ ተቀምጧል። እሳት እና ጭድ የነበረው የአማራ ጽንፈኛ እና የኦሮሞ እብሪተኛ አንድ ላይ አብሮ መነሳቱ ኢህአዴግ አቅዶት የነበረውን ስራ ባለመስራቱ እንደሆነ ተናግሯል። ትላልቆቹን ነገዶች እያገዳደልን መቀጠል እንዴት ተሳነን ሲል ይጠይቃል።


ታድያ ህወሃት፣ ደብረጽዮንን ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጠው የአንደበት ዘገምተኝነቱን ጌታቸው ረዳ እንዲሸፍንለት ነበር። የራያው ጌታቸውም ቢሆን የድል አጥቢያ ታጋይ ሆኖ የህወህት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል እሆናለሁ ብሎ አስቦት አያውቅም። ክፍት አፉን እና ልቅ ምላሱን ለመጠቀም ኮሚቴ ውስጥ ቢገባም ደብረጽዮን ጋር አብሮ መስራቱን እንደውርደት ቆጥሮታል። ሌላም ችግር አለ። ሰውየው እንደ ቀትር እባብ ያለ ጫት አይኑ አይገለጥም፣ ጥዋት ተነስቶ የጀበና ካልቃመ ምላሱ ይተሳሰራል። ጋዜጣዊ መግለጫዎችን መስጠት ካለበት ደግሞ “አቦ ሚስማር” ወይንም “የአወዳይ” ጫት ቅሞ ሉሉቀቻ ማድረግ የግድ ነው። 


እንግዲህ አንዱ በዝሙት ፣ ሌላው በጫት ሱስ ተጠምደው፣ በታሪክ አጋጣሚ በከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጠዋል። ያለ ችሎታቸው እና የለቦታቸው። በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንዲሉ፣ በሱስ መታሰራቸው ሳያንስ እርስ በርሳቸው እየተባሉ ነው። ከማራቶኑ የኢህአዲግ ስብሰባ በህዋላ ደብረ ጽዮን ስለ ሽኩቻቸው እና ስለ መቧደናቸው እንዲህ ብሏል።


“ስልጣን ባይገኝ እንኳ ሥልጣን ላይ ከሚወጣው ሰው ጋር ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። በሕወሃት ውስጥ የተፈጠረው መርህ አልባ ግንኙነትና መቧደን አንዳንድ ጥሩ የሚሰሩ አመራሮችንም ሥራ የሚያደናቅፍ ነው።…በሕወሃት ውስጥ የተፈጠረው መርህ አልባ ግንኙነት የኦሕዴድንም አንድነት ሸርሽሮታል።”


ሽኩቻውን በድል እንደተወጣውም ይናገራል።


ካንድ መሪ የማይጠበቅ አንደበተ ዝግመት የሚያጠቃው በዚህ ሰው ላይ ዘመቻው በይፋ ተጀምሯል። እያወቁ ከለቀቁ በኋላ፣ ሃክ ተደረገ ምናምን የሚሉት ፖለቲካ ማንንም አያሳምንም። በዚህ አይነት መናናቅ፣ መተናነቅ እና መተላለቅ ውስጥ ሆነው አንዱ የሌላውን ምስጢር ቢያወጣ ፍጹም እንግዳ ሊሆን አይችልም።


በፌስ ቡክ የተለቀቀው የአስካለ ገብረኪዳን ምስጢር ሃገር ያወቀው እውነት ነው። እሁን እነሱ ስለምጣ እንጂ፣ ሁሉም በዝሙት እና ስካር ተዘፍቀዋል፣ መባሉ አድባባይ ወጥቷል። ለወንበዴዎች እውነት መራር ብትሆንም ስለለመዱት ግን አይሰቀጥጣቸውም።

Source: በኮሚኒኬሽኑ ጉዳዮች ሃላፊ ሃዱሽ ካሱ ፌስ ቡክ ላይ ከተገኘው መረጃ ተነስቶ የተዘጋጀ

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top