News Feature

ሰውየው! ሚኒስተር አይመስልም – (ቃልኪዳን ኃይሉ)

እኔ ዶክተር አብይን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት “ንባብ ለሕይወት” ዓመታዊው የመጽሐፍ አውደ ርዕይ ላይ የሳይንስና ቴክሎጂ ሚኒስተር ዲኤታ ሆኖ በእንግድት ተጋብዞ ንግግር ሲያደርግ ነው፡፡ ወትሮ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት በተለያዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅት ላይ ንግግር አድርጉ ተብለው የተጠሩ እንደሆነ መንግሥት በቀረጥ ላይ ቀረጥ፤ በጫና ላይ ጫና፤ በእጅ አዙር ሳንሱር ላይ ሳንሱር እየጨመረ ያቀጨጨውን የኢትዮጵያን ኪነጥበብ ባለሥልጣናቱ ግን “መንግሥት ለኪነጥበቡ በዚህ ወጥቶ በዚህ ወርዶ፤ በዚህ ተፈልጦ በዚህ ተገልብጦ፤ ቅብርጥሶ ቅብርጥሴ….. መንግሥት እንዲህ ብሎመንግሥት እንዲያ አድርጎ…” ይላሉ፡፡


ዶክተር አብይ ግን ሀሳብ አፍላቂዎች፤ ፈጣሪዎች ይበዙበታል በሚባልበት የንባብ ለሕይወት ታዳሚያን ውስጥ ነገሰ፡፡ የተለመደውን የካድሬ ጅንጀናና ድስኩሩን ይረጫል ሲባል ዶክተር አብይ ያልተጠበቀውን ንግግር አደረገ፡፡ ከንግግሩ ማማራ፤ ይዘቱ ይገርማል፤ ይዘቱን ስናደንቅ አቀራረቡ የንግግር አሰናሰሉ ይበልጥ ማራኪ ነበር፡፡ በዚያ ያነባልና ይጽፋል የሚበላውን ታዳሚ አፍ ያስከፈተ ያስደመመ ንግግ አደረገ፡፡

ከዶክተር አብይ ንግግር በኋላ የቀኑን ሙሉ የንባብ ለህይወት ታዳሚ ጉዳይ የዶክተር አብይ ንግግር ሆነ፡፡ አስታውሳለሁ ያኔ ዶክተር የሚለውን ማዕረጉን አልያዘም ነበር፡፡ አቶ አብይ ነበር፡፡ ግን ንግግሩ አስገራሚ ስለነበረ በብዙዎች ዘንድ አንቱ ሲባል ነበር የሰማሁት ጭራሽ ፈገግ ያስባለኝ አድናቆት ግን “ሚኒስተር አይመስልም” የሚለው አስተያየት ነው፡፡

ብዙዎች የኢሕአዴግ ሚኒስትሮች ንግግሮች የቸኩ፣ የነተቡ፣ ባይናገሯቸውም የታወቁ፣ ቢሏቸውም ባይሏቸውም ለውጥ የማያመጡ፤ መቼ በተናገሩ ሳይሆን፤ መቼ ተናግረው ባቆሙ ተብለው የሚናፈቅ ነው፡፡ ባለስልጣናቱ በቴሌቪዥን የሚናገሩ ከሆነ የእነሱ ንግግር እስኪያልፍ ቴሌቭዥኑን የምንዘጋበት፤ ፊትለፊታችን የሚያወሩ ከሆነም እየሰማን የማናደምጥበት ነበር፡፡ ለዶክተር አብይ ግን ይለያል፡፡

ዶክተር አብይ ሲናገር ከአፉ ማር ጠብ ይላል የሚባል አይነት ሰው ነው፡፡ አሰልቺ ጀንጃኝ ካድሬ ሳይሆን፤ ዘመንን የዋጀ በእውቀትና በተሞክሮና ጠለቅ ያለ መረዳት የታከለበት ረጋ ያለና ነዛሪ ድምጽ ያለው አንደበተ ርትዑ ነው፡፡ ከንባብ ለሕይወት በኋላ ዶክተር አብይን ያየሁት በቴሌቪዥን ኦህዴድ ጥርስ አወጣ ብቻ ሳይሆን ጉልበቱም ፈረጠም፤ ከሕወሐት ጋር ጉርምቦ ለጉርምቦ ተናነቃ የተባለ ጊዜ ነው፡፡

ልክ ነው፡፡ በዚህ ወሳኝ ሰአት እንዴት እንዲህ ያለ ተጋፋጭ የኦህዴድ ሰው ተገኘ ብዬ ነበር፡፡ በትክክልም አብይ ነበረ፡፡ ጉዩነን በጥሞና ባየውም ሰውየው እንደውም ባሰበት እንጂ አልቆመም፤ በሰለ እንጂ እንደ ካሮት አላደገም፤ ንግግሩ አንዳንዱን አካባቢ ይረብሸው ጀመር፡፡ ብዙኑነን ደግሞ ያረሰርሰው ያዘ፡፡

ለአብይ የምናውቀው አይነት የኢሕአዴግ አሰላለፍ ያፍነዋል፤ የዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት በሚል አደንዛዥ ማደናቆሪያ ፕሮፓጋንዳ መፈልፈል ያመዋል፡፡ አንድ ቃል እንደገደል ማሚቱ ማስተጋባት ለሰውየው አይመቸውም፡፡ ሰውየው ወጣ ያለ ነው፡፡ ለዚህ ወጣ ላለ ሰው በግሌ እስከማውቀው የኢሕአዴግ ቤት ምቹ አይደለም፡፡

አብይ የኦሮሚያ ምክትል ፐሬዝዳንት መሆኑን ሳይ ሚኒስተር የማይመስለው ሰውዬ ጉድ ሊያደርጋቸው እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ ሰውየው ለሕዝብነት እንጂ ለጅንን ሚኒስተርነት አይቀርብም፡፡ በተለይ በዘመኑ ለምናውቃቸው ሚኒስተርና ሌሎች ባለስልጣናትም ራቅና ጽድት ያለ የፖለቲካና የማገናዘብ ልእልናና ልቀት ላይ ያለ ሰው ነው፡፡

ሰውየው ኢህአዴግ አባል ይሆናል እንጂ ኢህአዴግ አይደለም፡፡ እሱ ሌላ ነው፡፡
በቃ የሰውየው አእምሮ የሰው ነው እንጂ የሌላ ሰው ራዕይ አይደለም፤ ሰውየው አልቆመም ይራመዳል፤ አይተኛም ያነባል፤ ንግግሩ ቁጣና ሽብር አይጋብዝም ይልቁንስ እውቀትና መረጋጋት አለው፤ ገፍታሪ አይደለም ይልቁንስ አቃፊ፣ አስተባባሪና አጽናኝ እንጂ፡፡

እጁ ግን ብእር ብቻ አልጨበጠም ይልቁንስ እሳት ተፊውንም ያውቀዋል፡፡ ውትድርናን በሽጉጥም ብቻሰ ሳይሆን በሳይንስም ያውቀዋል ይባላል፡፡ በሰላም አስከባሪነት ከኢትዮጵያ ውጪ ሌሎች አፍሪካ ሀገራትም አገልግሏል፡፡ ግን ደግሞ አስተሳሰቡ ጠመንጃዊ አይመስልም፡፡ ይልቁንስ እውቀት የገራው፤ ማወቅ እርቡቅ ያደረገው አይነት ሰው ነው፡፡

አስቀድሞ ማመሰገን ቢያስፈራም ሰውየው ከኢሕአዴግ መንጋ ግን ይለያል፡፡ ይነጠላል፡፡ ከፕሬዝዳንቱ በላይም ይህን ሰውዬ እፈራዋለሁ እጠብቀዋለሁ፡፡ ሰውየው አለ ወይ? እንድት አስቴር አወቀ እውነትም ሰውየው አለ፡፡

8 Comments

8 Comments

 1. nana

  January 9, 2018 at 10:10 am

  ሀበሻ ጫፍ ይዞ ይክባል ብፁእ ወቅዱስ ምናምን ያረጋል

  ትንሽ ይቆይና ከሱ ጋር ካልተስማማ የጭቃ ጅራፉን ያወናጭፋል ፡፡
  መረገም ነው !

  • Tazabi

   January 9, 2018 at 10:46 am

   Nana,
   ኣውቀንሃል።ትናንት በሌላ ጽሁፍህ ኣቶ ለማን ለመተቸት ዳድተሃል።ምቀኝነት የትም ኣያደርስህ!

   • Nana

    January 10, 2018 at 3:13 am

    Sorry for insulting your new GOD .
    silly boy !

  • haylu

   January 10, 2018 at 4:31 am

   Hi Nana you are Right

   የናናን ኣባባል እኔም እጋራዋለሁ፥፥ ይሄ ቶሎ የተጋነነ ምስጋና ሰዉን ኣምላክ ኣስመስሎ ማቅረብ በሁዋላ ደግሞ ክሰብኣዊነት በታች ኣዉርዶ መዝለፍ የተለመደ ነው፥፥
   ይሄን ጽዋ የቀመሰ ፖለቲከኛ ፣ ጋዜጠኛ እና ታዋቂ ሰው ቢዘረዘር ብዙ ነው፥፥
   ዶር ኣብይን በበኩሌ በተናገረው ነገር በሙሉ እስከኣሁን የምቃወመው ኣንድም ነገር የለም፥፥ ግን ከተፈጥሮ ዉጭ ኣድርጎ ኣጋኖ ማመስገን እና እላይ መስቀል ኣግባብም ኣይደል ለርሱም ኣጠገቡ ላሉትም ጥሩ ላይሆን ይችላል በማለት ነው፥፥
   ተንጠራርተው የሰቀሉትን ተንጠራርተው ለማውረድ ይከብዳል ይባል የለ፥፥

 2. Midri_Bahri

  January 9, 2018 at 4:30 pm

  Dr. Abiy is unique and THE ONLY REASON I LIKE HIM IS HE TALK WITH THE LANGUAGE I UNDERSTAND IT.
  WE NEED MANY MORE IN EAST AFRICA TO BRING PEACE AND PROSPERITY.

 3. Chala alemu

  January 10, 2018 at 4:23 pm

  በከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ላይ የሚገኝ ስው ውደ ታች ወርዶ ዕውቀቱን ለወገኑ ሲያካፍል እስካሁንባለማየታችን ተገርመናል ተደንቀናል ዶ/ር አብይ ርካሽ የወያኔ ፕሮፓጋንዳ አልስበከም ዕውቀትን ፍልስፍናን ነው የዘራው ስምን መልዓክ ያወጠዋል እንደሚባለው ዶ/ር አብይ እንደስሙ ታላቅ ስው ነው እርሱና ለማ ልክ በጭልማ ውስጥ እንደ ሚያበራ አንፀባራቂ ኮከብ ናቸው ኢትዮጵያውያን እንኮራባቸዋል ይህ ደግሞ ከዕውቀትና ከእውነት ጋር የማይተዋወቁ የወያኔ መንጋዎችን ምን ያህል በቅናትና በጥላቻ እንደሚያገበግባቸው ጠንቅቅን እናውቃለን
  ሌላው ቀርቶ ሳይታክቱ ቀንና ሌሊት
  የሚዘርፉዋትን ኢትዮጵያን እንኳ አጥብቀው እንደሚጠሏት እኛም ወያኔዎችም እናውቃለን ወያኔዎች ከጥላቻና ከስይጣናዊ ተግባራችው በስተቀር ምንም የማያውቁ ድዊና የአዕምሮ ስንኩላን ናቸው ይህንን ገበናቸውን ለመሽፈንም ድግሪ /ወረቀት/ “ማስትሬት”ዶክትሬት” በመማር ሳይሆን በመግዛት ጊዜያቸውንና ‘የአገሪቷን ም ገንዘብ ያባክናሉ ዛሬ አገራችን የ4ተኛ ክፍል ምሩቃን እነሳሞራ የኑስ ፕሮፌስር ዶክተር ጄነራል የሚባልባት አገር ሆናለች ተራ ስራተኛቸውንም ከበድ ያለ የውጪ ስምእየተስጣቸው የምንትሴ ድሬክቶሬት ድሬክተር ይሉታል በአገሪቷ የሚገኙ ማናቸውንም ስሞች ከእንግሊዘኛ በስተቀር በአገርኛ ስሞች አይሰየሙም አይጠሩምም እና ከዚህ የበለጠ ከዕድሜም ያለመማርና ወራዳነት መሃይምነት እንዴትና በምን መልኩ ይገልፃል?

 4. Mohammed

  January 11, 2018 at 4:09 pm

  ነፍስያዬ ተደሰተች: ረካሁ:: ከዚህም በላይ ይገበዋል ግን ይቆይ:: ያዝልቅልን::

 5. Fekadu

  January 13, 2018 at 7:55 am

  አንተ ዘረ ለማኝ የእግሩ እጣቢ አትሆንም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top