ነፃ አስተያየቶች

ወሮበላ እና ሌባ ከእስር ፈታሁ በማለት ህዝብ ካዘናጋ ብኋላ ህዝባችን ላይ የበቀል በትር ለመሰንዘር ያደባዉ ወያኔ


ሸንቁጥ አየለ

ጀግኖቻችን እናተ እስር ቤት የገባችሁት ስለ ህዝባችን ክብር ነዉ::ከመኢአድ: ከአንድነት: ከሰማያዊ ፓርቲ እንዲሁም ከልዩ ልዩ ፓርቲዎች በወያኔ እስር ቤት የተቆለፈባችሁ ሁሉ ለእናንተ ያለን ክብር ከፍ እና ላቅ ያለ ነዉ:: በህዝባዊ ተጋድሎ ወያኔን ያንበረበራችሁ ድንገት ከህዝብ መሃል የፈለቃችሁ ጀግኖች ሁሉ ለእናንተ ያለን አክብሮት ላቅ ያለ ነዉ::

ከሰሜን ኢትዮጵያ እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ: ከምስራቅ ኢትዮጵያ እስከ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሎም ከመሃል ኢትዮጵያ እስከ አጽናፍ አጽናፍ ወያኔን ስለህዝባችን መብት የታገላችሁ ብሎም አለወንጀላችሁ ወደ ወህኒ የተጋዛችሁ ሁሉ ለእናንተ ያለን አክብሮት እጅግ ላቅ ያለ ነዉ::

ጀግኖች ጋዜጠኞቻችን: የሰበአዊ መብት ተከራካሪዎቻችን እና በርካታ ቆራጥ የህዝብ ወገኖች ሁሉ ለእናንተ ያለን ክብር እጅግ ላቅ ያለ ነዉ::በመከራ እና በኢፍትሃዊነት ጨለማ ዉስጥ ስለሚሰቃዬዉ ህዝባችሁ ስትሉ አለ ወንጀላችሁ በሀሰተኛዉ ወያኔ ወደ ወህኒ ተግዛችኋል እና::

ሌባ እና ወሮበላ በመፍታት እስረኛ ፈታሁ የሚል ዜማ የለቀቀዉ ወያኔ ድንቁርናዉ እራሱን ያታልል እንደሆነ ነዉ እንጅ ህዝብን ከቶም ማታለል አይችልም::
የህዝብ ጀግኖችን በማሰር ብሎም እስረኛ ፈታሁ በማለት ህዝብን ለማደናገር መሞከር ፈጽሞ አይቻልም::
የህዝብ ጀግኖችን ሁሉ ወያኔ ከእስር እንዲፈታ በጥብቅ እናሳስባለን !

የሆነ ሆኖ አሁን ወያኔ አንድ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲናን ፈታሁ ብሎ ብዙ ፕሮፖጋንዳ እየነፋ ነዉ::የምዕራብ ሚዲያዎች እማ ምንም ሳያፍሩ ወያኔ እስረኛ ለቀቀ እያሉ እያናፉ ነዉ::

ሆኖም ወያኔ በርካታ የፈታቸዉ ታሳሪዎች ወሮበሎች እና ሌቦች ናቸዉ::በዚህ ሁኔታ ህዝባችን ተዘናግቶ ወደ ቤቱ ሲገባለት በወያኔ የመንደር ሰላዮች በመላዉ ሀገሪቱ የሚገኘዉ ህዝባችንን አመጽ አካሂደሃል: ከአማጺያኑ ጋር ተባብረሃል: ህዝባዊ ትግሉን ተባብረሃል: ቄሮ ረድተሃል: ፋኖ ረድተሃል: ተጋድሎዉን አግዘሃል ተብሎ የበቀል በትር ሊያርፍበት እንደሚችል መገመት ይገባል::

የወያኔ የበቀል በትር የኢኮኖሚ: የአካል: የማሰር: የመግደል እና የማንገላታት እንደሚሆንም መገመት ይገባል::ህዝባችን ላይ ሊሰነዘር የሚችለዉን የወያኔን የበቀል በትር በርትቶ ለማጋለጥ መዘጋጀት ከያንዳንዱ ሰዉ ይተበቃል::

እንዲሁም ይሄ የበቀል በትር ሊመጣ እንደሚችል ህዝቡን አሁኑኑ በርትቶ ማስተማር እና ማዘጋጀት ይገባል::ወያኔ አንዴ መሬቱ ከተረጋጋለት ብኋላ እና ሁኔታዎች ከቀዘቀዙለት ብኋላ ህዝቡን እንደሚበቀለዉ ሳይታለም የተፈታ ነዉ::

1 Comment

1 Comment

 1. Hailu

  January 21, 2018 at 8:38 pm

  በዶ/ር በዛብህ የሚመራዉ ቡድን እነ አቶ ማሙሸት አማረ እንዲሁም ከመቶ 120 በላይ የመኢአድ አመራሮች እንዳይፈቱ ከወያኔ ጋር ድርድር ላይ መሆናቸዉ ተሰማ
  ሸንቁጥ አየለ
  ————
  ማጠቃለያ
  ——

  – የእነ ዶ/ር በዛብህን እና የእነ ሙሉጌታን የባንዳ ስራ ሰሞኑን በርካታ የመኢአድ ጀግኖች ተቃዉመዉታል:: እነ ዶ/ር በዛብህንም በግንባር በመቅረብ ይሄን አካሄዳቸዉን እንዲያርሙ አሳስበዋቸዋል::እነዚህን ባንዶች ፊት ለፊት ተጋፍጠዋቸዋል:: በፊት ለፊትም “ትግሉ መራራ ነዉ::የመኢአድ ሀይላት በወያኔ ደባም ሆነ በእናንተ በእነ ዶ/ር በዛብህ እና በነ አቶ ሙሉጌታ የባንዳ ስራ ትግላችንን አናቆምም::እየታሰርንም ትግሉ ይቀጥላል::በሞታችን እንደ አባቶቻችን ኢትዮጵያን እንታደጋታለን:: ይሄንንም በተግባር እያያችሁ ነዉ::ከሀገር ቤት እስከ ዉጭ ያለዉ የመኢአድ ሀይላት አሁንም የሚመራዉ በአቶ ማሙሸት አማረ እና በአቶ ዘመነ ምህረት ነዉ::መኢአድን ማንም አያፈርሰዉም::መኢአድ የትግል መንፈስ የሚያስተባብረዉ ድርጅት እንጅ የቢሮ እና የማህተም ጋጋታ የሚያስተሳስረዉ ድርጅት አይደለም::መኢአድ 121 አመራሮቹ ታስረዉበት ምንም ሰዉ እንዳልታሰረበት አድርጋችሁ ያወጣችሁት መግለጫ የባንዳ ስራችሁን ያጋልጣል” ሲሉ ሞግተዋቸዋል::

  – እንደተባለዉም መኢአድን ማንም አያፈርሰዉም::መኢአድ የትግል መንፈስ የሚያስተባብረዉ ድርጅት እንጅ የቢሮ እና የማህተም ጋጋታ የሚያስተሳስረዉ ድርጅት አይደለም::
  —————————————

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top