News Feature

በወልዲያ የተፈጸመው ጭፍጨፋ አስቀድሞ በሕወሃት የታቀደ እንደነበር ተገለጸ | የሟቾች ቁጥር በትክክል አልታወቀም

በወልዲያ የሚካኤልን በዓል ለማክበርና ታቦት ለመሸኘት አደባባይ በወጡ ንጹሃን ላይ በፌዴራል ፖሊስ ስም የተሰማሩ የስርዓቱ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ፣አስለቃሽ ጭስና ድብደባ ሳቢያ በርካታዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን እስካሁን የሟቾች ቁጥር በትክክል ባይታወቅም የቅርብ ምንጮች እንዳረጋገጡት ቢያንስ የስድስት ሰዎች አስከሬን ሆስፒታል መድረሱን ነገር ግን ወታደሮቹ እየተኮሱ ሰውን በሚያሸብሩበት ወቅት የገደሉዋቸውን ንጹሃን አስከሬን ያሸሹ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።


የአማራ ልዩ ሀይል ፖሊሶች ጭምር በስፍራው የነበሩ ሲሆን በብዛት ከከተራ ዋዜማ ጀምሮ ከፍተኛ ታጣቂ ቡድን ወደ ወልዲያ የገባ ሲሆን ወጣቶችን ለማጥቃት አስቀድሞ የተደረገ ዝግጅት መኖሩን ያሳያል የሚሉ በርካቶች ሕወሓት በፍጹም እንደማይለወትና የወልዲያው ጥቃት ባለፈው የመቀሌ ከነማና ደጋፊዎች ለኳስ ጨዋታ በመጡበት ወቅት በወልዲያ ያስነሱትን አምቧጓሮ ተከትሎ በታጣቂ ጥይት አንድ ወጣት ሲገደል በአጸፋ ድንጋይ ውርወራ አንድ የመቀሌ ደጋፊ ዘግይቶ በሞተበት ወቅት በአደባባይ የህወሃት ደጋፊዎች ግልጽ እርምጃ ለመውሰድ ሲዝቱ እንደነበር አይዘነጋም። ዛሬ ወልዲያ ላይ በሰላማዊ መንገድ ሊያልቅ የነበረን ታጣቂዎች ዞር በሉልን በኣሉን በሰላም እናክብር የሚል ጥታቄን ወደ ሽብር ተግባር ቀይረውታል።

የክልሉ ባለስልጣን የወልዲያውን ጥቃት በእረብሸኞችና የጸጥታ አካላት መካከል አድርገው ለማሳየት መሞከር ትልቅ ድፍረት መሆኑን ተከትለው የወጡ ተቃውሞዎች ሲያሳዩ ማምሻውንም በወልዲያ ከተማ ሕዝቡን በተኩስ ሲያሸብሩና ተጨማሪ ዎጣቶች ከየመኖሪያቸው አስቀድሞ በነበረ ዝግጅት ሲታፈኑ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።ሕወሃት በፍጹም ለለውጥ አለመዘጋጀቱን አስቀድሞ በኢአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስም የወጣውና የሕወሃት አቋም ነበር በተባለው የጽሁፍ መግለጫ መሰረት የሚነሱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን በተለያዩ አፈናዎች ለመቀጠልና ለመቆጣጠር መግለጹ አይዘነጋም።

በወልዲያ ዛሬ ጥር 12 ቀን 2010 ባልታጠቁ ወገኖች ላይ የተከፈተውን ተኩስ ተከትሎ ሁኔታው ያበሳጫቸው ወጣቶች ሕዝቡን በድንጋይ ውርወራ ለመከላከልና ግድያውን ለመቃወም የሞከሩ ቢሆንም አስቀድሞ ታጣቂ አንፈልግም ለሚለው ሰላማዊ ጥያቄ የአስለቃሽ ጭስና ወዲያው ተኩስ በማስከተል ሟቾችን በቀጥታ አነጣጥረው በመተኮስ አባቶችን ሳይቀር በመደብደብ በጥይትና በዱላ የቆሰሉትን በትክክል ቁጥራቸው እንደማይታወቅ ለማወቅ ተችሏል።

ታጣቂዎች ሆስፒታልን በመውረራቸው በቀላሉ ቆሰሉትን ማወቅ ባይቻልም የሟቾች ቁጥር ከስድስት ሊጨምር ይችላል የሚለው ግምት የብዙዎች ሆኗል። የብአዴን አመራር የሕወሓት አሽከርነቱን ትቶ ሰልፉን እንዲያስተካክል ተጨማሪ ተቃውሞዎች የዛሬውን ግድያ ተከትሎ መደመጥ ጀምሯል።

በነገው ዕለት በባህር ዳር ስታዲየም በሚካሄደው የቴዴ አፍሮ ሰዓታት በቀረው ኮንሰርት ላይ በወልዲያ ለተገደሉት ግልጽ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ተቃውሞን መግለጽ ይገባል የሚሉ በአንድ በኩል ኮንሰርቱ ሊሰረዝ ይገባል የሚሉ በሌላ በኩል ከወዲሁ አስተያየታቸውን መስጠት ጀምረዋል። ኾንሰርቱን አስታኮ ሕወሓት የተለመደ የሽብር ተግባር ሊፈጽም ይችላል በሚል የከተማው ወጣቶች ጸጥታ ለማስከበር አስቀድሞ ከፖሊስ ጋር እስከመምከር መሄዳቸው መሰገቡ ይታወሳል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top