ነፃ አስተያየቶች

የኦሕዴድና የብአዴን ልዩነት


ከአቻምየለህ ታምሩ

ኦሕዴድ ለወያኔ ያደረ ይሁን እንጂ የኦሮሞ ልጆች ድርጅት ነው። ከሆዳሞቹ በቀር አብዛኛዎቹ በኦሮሞ መድማት የሚደሙ ናቸው። ብአድን ግን በአማራ መካከል ፋሽስት ወያኔን የሚወክሉ ትግሬዎችና አማራን የሚያደሙ ስብስቦች ድርጅት ነው። ብአዴን የትግሬዎቹ የነ በረከት ሰምዖን፣ ካሳ ተክለ ብርሃን፣ ታደሰ ጥንቅሹ፣ ሕላዌ ዮፌስ፣ ጫኔ ከበደ፣ አልምነው መኮነን ድርጅት ነው። ከነዚህና መሰል ነውረኞች በተጨማሪ ብአዴን አማራ ያልሆኑት ቀንደኛ አማራ ጠሎች የነ ደመቀ መኮነን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋና መሰል ተሸካሚ ነው።

እነዚህ ነውረኞች በአማራ መድማት ድርሳቸው እስኪደማ በደስታ የሚስቁ ቅጥረኞች ናቸው። አማራ ላለፉት ሀያ ሰባት አመታት ሲገዘገን የከረመው ፋሽስት ወያኔ አማራን ለማጥፋት ያዘጋጀው ፕሮግራም በሚተገብሩ በነውረኞች ጭምር እየተመተረ ነው።
ከቻት የታተመው ድምጽ የአንድ ኦዴድና የአንድ ብአዴን ሰዎች የሰጡት ቃለ መጠይቅ ነው። የመጀመሪያው ድምጽ የአምቦ ከተማ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የኦህዴዱ የአቦ ጋዲሳ ደሳለኝ ሲሆን፤ ኦቦ ጋዲሳ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል በሰጡት ቃለ ምልልስ የባለፈውን ሰሞን የአምቦ ወጣቶችን ግድያ በሰላማዊ የኦሮሞ ወጣቶች ላይ «የመከላከያ ሰራዊት» እንዳካሄደው እቅጩን ያስቀምጣሉ፤ ወጣቶች እየተጨፈጨፉ እውነቱን ከመናገር ውጭ አማራጭ እንደሌላቸውም ይናገራሉ። ኦቦ ጋዲያ ይህንን ለማድረግ የወሰኑት የወገኖቻቸው ደም የርሳቸውም ደም ስለሆነ ነው።

የነውረኛውኛ ብአዴን እንደራሴ አማረ ጎሹ ግን ቀለብ የሚሰፍሩለት ወያኔዎች በሚዘውሩት ቴሌቭዥን ላይ ዛሬ ቀርቦ ስለ ወልድያው ጭፍጨፋ ሲናገር በአማራ ምዕመናል ላይ የተካሄደውን የንጹሐን ጭፍጨፋ «የተለየ የፖለቲካ አላማ የያዙ ወጣቶች ባስነሱት ግጭት የተከሰተ ነው» ሲል ተናግሯል። ብአዴን ማለት እንዲህ ነው።

ላለፉት ሀያ ሰባት አመታት ፋሽስት ወያኔ በአማራ ላይ ያካሄደውን ግፍና ጨካኔ ሁሉ የተለየ የፖለቲካ አላማ የያዙ ሰዎች ያስከተሉት እንደሆነ ሲነግረን ኖሯል። ብአዴን የተፈጠረው ለዚህ ነበር። ብአዴን የተፈጠረው በአማራ ስም ተሰይሞ በአማራ ላይ ፋሽስት ወያኔ የሚያካሂደውን ጭፍጨፋ ግን ትምክህተኞች፣ የድሮ ስርዓት ናፋቂዎች፣ ለሀጫሞችን፣ ባዶ እግራቸውን የሚሄዱ ሰንፋጮች፣ የተለየ የፖለቲካ አላማ የያዙ ግለሰቦች፣ወዘተ ግለሰቦችና ቡድኖች እንደፈጥሩት እያነወ የአማራውን ደም ደመ ከልብ ማድረግ ነበር። ይህን በማድረግ ረገድም ተሳክቶለታል። ነውረኞች አማራ ጎሹም ዛሬ ያደረገው በፋሽስት ወያኔ የተካሄደውን የንጹሐንን ጭፍጨፋ ንጹሐንን ተጠያቂ በማድረግ ወያኔ ከደሙ ንጹህ ማድረግ ነበር። ነውረኛው ብአዴን እንዲህ ነው!

3 Comments

3 Comments

 1. HATRED KILLS

  January 22, 2018 at 12:28 am

  STOP BLAMING ANDEM . STOP THE HOOLIGANS PROVOCING SECURITY FORCES AND BURNING AND LOOTING PRIVATE PROPERTY .

  ANDEM NEVER STANDS WITH HOOLIGANS . IT STANDS WITH ALL PEACE AND DEVELOPMENT LOVING PEOPLE .

  THE PROBLEM OF THIS HOOLIGANS IS HATRED . HATRED IS MOVING THEM LIKE CRAZY . IMPORTED HATRED IS COSTING THEM DEARLY .

  WHAT WOULD YOU GET IF YOU HATE MILLIONS OF PEOPLE ? ONLY HEAD ACHE !

  IF YOU THINK ANDEM WILL STAND BY YOUR CRIMINAL ACTS , THEN YOU MUST BE SUPER FOOL .

 2. Lema Anbesaw

  January 22, 2018 at 5:49 am

  be Amara sim yetederajachu,,, enante ye siltan timegnoch teregagu !

  be wich yalachu , !

  Amara ena Oromo gena tarek yeseral !!

  siltan yemeyzew be Hager bet ke Hizbu gar yemetagel enji

  kitfo eyetebela bewiske eyaweraredk ,,kentu be Gura aydelem !

 3. እምቢ ለዳያስፖራ ፖለቲካ ድርጅቶች

  January 23, 2018 at 8:23 am

  የአንድ ድርጅት መሰረቱ ከላይ ያለው አመራር ሳይሆን ከታች ያለው ህዝባዌ ሀይል ነው ።በዚህም ምክንያት በኦሮሞ ብሄርተኝነት ተኮትኩተው ፡ ተጠምቀው ያደገቱ የኦሕዴድ የታች ወጣት አባላቶች (ቄሮ) በምስጢር እራሳቸውን አደራጅተው ፣ እንዲደራጅ ተደርገው የወያኔን አፖርታይድ ስርአት ለመታገል ቆርጠው በመነሳታቸው እና የኦሕዴድን ባለስልጣናትንም አላፈናፍን ብለው በመያዝ ለህዝባቸው መብት እንዲቆሙ አስገድደዎቸዎል።

  ባንፃሩ አማራ በወልድያ : በመተክል : በወልቃይት ፡ በራያ ወንድሙ እያለቀ ፤ ወያኔ ከሰራለት የአማራ ባንቱስታ ሲወጣ አንተ መጤ እየተባለ እየተባረረ ፤ በባህርዳር እስቴድየም ላይ ስለሌለ ኢትዮጵያዊነት እሼሼ ገዳሙ ይረጋጥል።

  የአማራ ድርጅት ተብዬዎቹ ? ስለአማራ ህዝብ መብት ከመጨነቅ ይልቅ በታሪክና በኢትዮጵያ ካርታ ፍቅር አብደዎል። በጣም ግራ የሚያጋባው በክልሉ ውስጥ እራሱን መከላከል ያልቻለውን አማራ ኢትዮጵያን ያድናል እያሉ ጥሩባ ይነፉሉ ። ስለዚህ በብአዴን ውስጥ ያሉትን የታች አባልት በአማራዌነት ማን ይፀንሳቸው ፡ያደራጃቸው? የአገራችን አርሶ አደሮች ሲተርቱ ያልዘራህውን አታጭድም እነደሚሉት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top