ተ.መ.ድ. በወልድያ አማራን የጨፈጨፉት የትግራይ ወታደሮች መሆናቸውን አመነ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

አቻየለህ ታምሩ

ወያኔዎች ለወትሮው በየአመቱ የሚጨምረውን ዘረፋቸውን በሚከፍሏቸው ምዕራባውያን የገጽታ ግንባታ የሕዝብ ግንኙነቶቻቸው በኩል «እድገትና ልማት» በማስመሰል ምስክርነት የሚሰጡ ተቋማትንና ግለሰቦችን ማቅረብ የማይታክታቸውና የራሳቸውን ሪፖርት የልማታዊነታቸው ምስክር አድርገው እኛ የምንኖረውን ሕይወት የኛን ሕይወት በማይጋሩ ፈረንጆች ስላስነገሩ በውድቀት አፋፍ ላይ እያጣጣረች የምትገኘዋን ኢትዮጵያን ወደ ተስፋ ምድርነት ለመቀየር ሩብ ጉዳይ የቀራት አድርገን እንድናስባት በደረቁ ይላጩን ነበር።

የምንኖረውን መናጢ የድሀነትና የችጋር ኑሮ ወደ ተስፋ ምድርነት ለመቀየር ሩብ ጉዳይ የቀረን አድርጎ የወያኔን ዘረፋ የኛ እድገት በማስመሰል እየተከፈለው የወያኔን ሪፖርት መልሰው ከሚያሰሙን አለማቀፍ ተቋማት መካከል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀዳሚው ነው።

የዚህ ድርጅት የደህነትና የጸጥታ መምሪያ [United Nations Department for Safety and Security] በትናንትናው እለት ለተቋሙ ሰራተኞች በላከው የውስጥ መልዕክት እንደገለጸው ወልድያ ውስጥ በትግራይ ወታደሮች የተካሄደውን ጭፍጨፋ “The Government deployed Tigrayan military forces to the area which triggered more resistance» ሲል በተደጋጋሚ « የትግራይ ወታደሮች ያካሄዱት ጭፍጨፋ» እያልን ስንገልጸው የነበረውን የወልድያ ጭፍጨፋ በትግራይ ወታደሮች የተካሄደ እንደሆነ ለራሱ አረጋግጧል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደህነትና የጸጥታ መምሪያ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ያን ያህል ጥናት የማያሻውን የትግራይ የበላይነት የለም ባሉበት ማግስት እየጨፈጨፉን ያሉት ለበቀል የሰለጠኑትና የተሰማሩት የትግራይ ወታደሮች መሆናቸውን [ምንም እንኳ ለኛ ለኢትዮጵያውያን አዲስ ባይሆንምና ለውጥ ባይኖረውም] ስለመሰግነው እንወዳለን።

ከዚህ በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደህነትና የጸጥታ መምሪያ የትግራይ ወታደሮች ያገኙትን አማራ ሁሉ ሊጨመጭፉ ስለሚችሉ በተለይ ትግራይ የሚኖሩ አማራሮች የበቀል ግድያ ሊፈጸምባቸው እንደሚችል አውቀው ራሳቸውን ከጥቃት እንዲጠብቁ በጥብቅ አሳስቧል።

ነፍሰ በላዎቹ የትግራይ ወታደሮች ቅዳሜና እሁድ ወሎ ምድር ወልድያ ከተማ አማራ ሲጨፈጭፉ ሰንብተው በዛሬው እለት ደግሞ ሸዋ ተሻግረው በአለም ገና ከተማ ሶስት ንጹሐንን በተካሁበት ጭካኔ በግፍ ረሽነዋል። በአለም ገና ከተማ በትግራይ ወታደሮች እጅ የወደቁትን ሰማዕታት እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያኑረው። ለወዳጆቻቸውና ለቤተሰባቸው በሙሉ ጽናትንና ብርታትን ፈጣሪ እንዲሰጣቸው ከልብ እመኛለሁ።

2 Responses to ተ.መ.ድ. በወልድያ አማራን የጨፈጨፉት የትግራይ ወታደሮች መሆናቸውን አመነ

 1. የሰው ህይወት መጥፋቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው። ነገር ግን በተመድ ደረጃ “የትግራይ ወታደር” የሚባል ነገር በዲፕሎማቲክም ሆነ ኦፊሴላዊ መንገድ የሚታወቅ ነገር የለም።ያሳያችሁት ደብዳቤ ከተመድ ከሆነ ሎጎውና ምልክቱ የታለ? የኢሜይል መልእክት ፖስት አድርጋችሁ ህዝቡን ታታልላላችሁ? ማጭበርበር የሚመስል ዘገባችሁ እጅግ አሳዛኝ ነው።
  ይህችን ሃገር ከሚያፈርሱ ኃይሎች ጋር እናንተም አብራችሁ የአፍራሽነት ሚና እየተጫወታችሁ መሆናችሁን እወቁት። ሃገርን የሚወድ ማንም ሰው አገዛዙና አመራሩ ላይ ያተኩራል እንጂ እንደዚህ ያለ ህዝብን በአንድ ህዝብ ላይ የሚያነሳሳ ዘገባ አይጽፉም።

  ኢትዮጵያዊ
  January 24, 2018 at 7:33 am
  Reply

 2. Bantebet ataleh motehal. Yantebitewin denkoro litatalil tichlaleh. Yetigray wetader😅😅😅. E-mailu lemanewyetelakew? Esatis yetigray wetader alalem?

  Wakjira
  January 24, 2018 at 10:13 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *