ትግራይ ትገንጠል ወይ? | ከካሳሁን ይልማ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ሀገርን መከፋፈል እንዲሁም መገንጠል የሚችሉት ፖለቲከኞች ወይም ነን ባዮችና የዚህ ዓላማ ማስፈጸሚያ ካድሬዎች ናቸው።ሕዝብ በሀገሩ ዕጣ ፈንታ ላይ ወስኖ እያውቅም። ለዚህ ሻዕቢያና ወያኔ ቁንጮ ምሳሌ ናቸው። ሻዕቢያ ኤርትራን አስገንጥሏል። የኤርትራ ሕዝብ በዚህ ውሳኔ ላይ ነፃነት ተሰጥቶት አልወሰነም። ጀበኻና ሻዕቢያ የነበሩ የኤርትራ ክፍለሀገር ተወላጅ ኢትዮጲያዊያን ስንት ነበሩ? ሁለቱ ሽፍቶች በርግጥ ሕዝባዊ ውክልና ነበራቸው ወይ?

ካሳሁን ይልማ

እነርሱ ወንበዴ ሐሳብ አፈለቁ፣ ወንበዴነታቸውን ነዙ፣ የገዛ ወገናቸው ላይ ጦር መዝዘው እየገደሉ…ኤርትራን በህወሓትና አሜሪካ አስተባባሪነት ገነጠሉ። የሻዕቢያ ባሪያ ወያኔዎች በበኩላቸው በተመሳሳይ ቋንቋ የሚሰበከውን ሸፍጥ ሲሰሙ ያደጉ፣ እነደ እነ ወዲ አፎምን መሆን የሚፈልጉ ነበሩ። የአሉላ አባነጋን ኢትዮጲያዊ ገድለ ታሪክ ሳይሆን የእነ ኢሳያስ አፈወርቂን የአፍራሽነት ትርክት ጭራ ሆነው ተከተሉ። መለስ ዜናዊ “ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ?” ሲባል “ኢሳያስ አፈወርቂን” ይል ነበር ብለው የሚሳለቁበትም በዚህ እውነት ምክንያት ነው። በአንድ ወቅት በተደረገለት ቃለ ምልልስም ይህን አረጋግጧል። ከኢሳያስ ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች ማሳለፍ ብዙ መጽሐፍ ማንበብ ነው ሲል።

 

እነ መለስ ሻዕቢያን መከተል ብቻ ሳይሆን ሸፍተው የሻዕቢያ አመራሮች ተልዕኮ ፈጻሚ በመሆን የትግራይን ወጣት አብረኸን ሸፍት እያሉ እስከመግደል ደረሱ። ያ ጭካኔ ለዓላማቸው ማሳኪያ ስላልበቃ “ሓውዜን መሽገናል” ብለው ለደርግ የተሳሳተ መረጃ እንዲደርሰው በማድረግ ሕዝቡን አስጨፈጨፉት። ዓላማቸው ተሳካ። ትግራይን ገነጠሉ።

ነገርግን የተገነጠለች ትግራይን ስልጣን ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ሲያስቧት ደነገጡ:: በኢትዮጲያ ውስጥ ሆነው ቢገነጠሉ እንደሚሻል አሴሩ። ከኢትዮጲያ ከተገነጠሉ ለአለቆቻቸው ሻዕቢያዎች ጠቃሚ እንደማይሆንም ቁንጥጫ ደረሳቸው። የኢትዮጲያ አንጡራ ሀበትን ማጓጓዣ ድልድይ ይጠፋል። አቶ ኢሳያስ ለኢሳትም ሆነ ለኦ.ኤ.ምኤን ከሰሞኑ ባደረገው ቃለምልልስ “ህወሓት ትግራይን እንዳይገነጥል የመከርነው እኛ ነን” ሲል እርሱ እንደሚለው ለኛ አስቦ ሳይሆን ለራሱ ረጅም ና ዘለቄታዊ ጥቅም ብቻ እንደሆነ ይገባኛል። እንደዚያ ካልሆነ ኤርትራን የገነጠለ ሰውዬ “ትግራይ እንዳትገነጠል ያደረግነው እኛ ነን” ሲል ደንቆሮ ሆኑልኝ እንደማለት ነው::

ይሁን እንጂ የህወሓቶች ከሻዕቢያ ጋር የነበረው የአለቃና ምንዝር ግኑኝነት ሌላውን ኢትዮጲያዊ እየመዘበሩ አቅም ሲያገኙ ጌቶቻቸው ላይ አሳመጻቸው። የሚጓጓዘው ጤፍ፣ቡናና ወርቅ ወደ ኤርትራ ሳይሆን ወደ ትግራይ ዞረ።ከዚያም በላይ ትግራይ ባላት የተፈጥሮ ሀብት ራሷን እንደማትችል ስለተገነዘቡ ሳይገነጠሉ ኢትዮጲያ ውስጥ ሆነው ለትግራይ የሚሆን መሬት ከአጎራባች ክፍለሀገሮች ለምሳሌ ወልቃይት፣ ራያና ቆቦ ከአማራ፣ ጨውና ማዕድን ያለበት የአፋር አካባቢ ላይ ዐይን ጣሉ፣ ከቤንሻንጉልም እንደዛው መሬት እየወሰዱ መበልጸግን መረጡ። ቤንሻንጉል ውስጥ በሱዳን ድንበር ላይ ያለውን የዕጣንና የጥሬ ዕቃ ንግድ እንዲሁም ኢንቨስትመንት ላይ ማን እንደተሰማራ ወደዚያ ተጉዛችሁ አረጋግጡ ወይም የአካባቢው ነዋሪ ጠይቁ:: የእርሻ መሬትንና የተፈጥሮ ሀበትን ምንጭን ጥያቄ በዚህ ሁኔታ በማሳካት ትግራይን በኢንዱስትሪ ማሳደግ ወሳኝ እንደሆነ በመስማማት ተግባራዊ አደረጉ። አዜብ መስፍን ሟች ባሏ በተለያት ማግስት መለስ ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል አደረጋለሁ ብሎ ሕልሙን ሳይጨርስ መሞቱ እንዳንገበገባት መግለጿ ለዚህ ማረጋገጫ ነው። ሕልሙንም ከግብ ለማድረስ በገባችው ቃል መሠረት በርካታ የኢንዱስትሪ ስምምነቶች ከውጭ ሀገር መንግስታትና ድርጅቶች ጋር በመፈራረም ተገባራዊ አደረገች። በላፈው አንድ ዓመት ብቻ ከ8 በላይ ፋብሪካዎች ስራ ጀምረዋል፣ ግንባታ ጀመረዋል። ከትግራይ ልማት ድርጅት ኃላፊነት ተባረረች የሚለው የህወሓት የውስጥ ሽኩቻ፣ ምናልባትም እንደታቀደው አልተሰራም ከሚል የዘለለ ሊሆን አይችልም።

እስካሁን በእቅዳቸው መሠረት ዓላማቸውን አሳክተዋል። ኢትዮጲያ ውስጥ ሆነው ኢትዮጲያዊያንን ከፍለው፣ ሌላ ሀገር ለብቻቸው እየገነቡ ቆይተዋል። ኢትዮጲያ የሚለውን ስም መጠየፍ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጲያን ማንነት ገላጭና ታሪካዊና ባህላዊ እሴትና ቅርሶቿን በነሱ ትርክት ሲቀይሩ፣ሲፈቀፍቁ፣ሲያጠፉ የከረሙበት ምክንያት ይኸው ነው፣ ጥላቻ። ባንዲራው ምስክር ነው። ኦሮሞን ለዚህ ዓላማ ማስፈጸሚያ በሚገባ ተጠቅመውበታል የሀገር ዋልታና ዋርካ ሳይሆን ሁሉጊዜ በተጠቂነት ስሜት እየማቀቀ የበታችነት ስሜት ውስጥ እንዲኖር አድርገዋል::

ለዚህ ሴራቸው እንቅፋት የሆኑትን ሁሉ ከፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እስከ ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያውያንን በግፍ እያሰሩ፣ እየገደሉ፣በሐሰት እየመሰከሩ፣ የዝንጀሮ ፍርድ እየሰጡ ሰቆቃ ፈጽመው በአረመኔነት ለመግደላቸው ምክንያት ለዓመታት የሸረቡት ይኸው እኩይ ሴራ ነው::

ነገርግን ፍጻሜው አላምር አላቸው፣ ግፋቸውና ውሸታቸው ሞልቶ ፈሰሰ። “ፈሪ፣ሽንታም ትውልድ” የተባለው፣እየተባለም የተሸናበት ወጣት አንገት ደፈቶ አምቆ የያዘው እሳቱ ፈንድቶ ወጣ። ያቃጥላቸውም ጀመር።

ከ3 ዓመታት በፊት በአምቦ የጀመረው ሕዝባዊ ቁጣ እየነደደ ኮንሶን አዳርሶ በጎንደር አሳብሮ ባህርዳርን አቃጥሎ መርሳ ደርሷል። በነዚህ 3 ዓመታት “አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግ ሲወነጀሉ፣ ሽብርተኞችና ፀረ ሠላሞችና ፀረ ልማቶች ሲባል፣ እደገቱ ያመጣው ፍላጎት ነው ሲባል፣ ማስተር ፕላኑ ተሰርዟል፣ ታችኛውና መካከለኛው አመራር ሕዝብ በድሎ ነው፣ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ጥልቅ ተሐድሶ …” እየተባለ እነደብረጺዮን “ጥፋተኞች ነን:: እስረኞች እንለቃለን፣ ሀገራዊ መገባባት …” እስከሚለው ሰምተናል። በዚህ ሁሉ የማዘናጊያ ኑዛዜ ውስጥ በ10 ሺዎችየሚቆጠሩትን አስረው፣ ሺህ ዜጎቻችንን እየገደሉ ነው።

ይህም ሆኖ እሳቱ ላይ ቤንዚን አርከፈከፈ እንጂ ሊያጠፋው አልቻለም።ስለዚህ የመጨረሻው ካርድን ለመሳብ እያቆበቆቡ ነው፣”እንገነጠላለን።”

የትግራይ ካድሬዎች “ንብረት ስለወደመ እንገነጠላለን” የምትል ተመሳሳይ ዜማ ይዘው መጥተዋል። የሕዝቡን ልብ ለመፈተሽ መሆኑ ነው። ሆኖም አካሄዱ ይበልጥ አደገኛና የማያስቡት ቅርቃር ውስጥ እንደሚከታቸው አላወቁትም።
27 ዓመታት እንዲነጠል ያደረጉትን የትግራይ ሕዝብ ወደየት ይዘውት ሊሄዱ ነው? ፣ የትግራይ ሕዝብስ እነዚህ የስርዓቱ ተጠቃሚ ካድሬዎች እስከመቼ ይጋልቡታል?

ከላይ ከኤርትራ ከታች ከአማራ ከጎን ከአፋር ከሁሉም አናድፈውት የት ሊያደርሱት ነው? መልሱ ያለው የትግራይ ሕዝብ ጋር ነው።

ሌላው፣ የህወሓት አፓርታይድ አገዛዝ ሰለባ ኢትዮጲያዊ ግን ግልጽ ጥያቄና መልስ አለው። “የትግራይ ሕዝብ ሆይ እባካህ ከአብራክህ የወጡ ልጆችህ ደሜን እያፈሰሱ ፣ የልጄን አስከሬን ሜዳ ላይ እየጣሉ ነውና እባክህ አብረኸኝ በቃ በላቸው” እያለ በጨዋነት ይጠይቃል።
“ትግራይን እንገነጥላለን” ሲሉ ለሚያስፈራሩት ካድሬዎቹ “ትግራይን ከገነጠላችሁ እኮ ቆየ፣ ከተለያየን 27 ዓመት ተቆጠረ” የሚል መልስ ይሰጣል። አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል:: እወነታው ይኼ ነው።

14 Responses to ትግራይ ትገንጠል ወይ? | ከካሳሁን ይልማ

 1. feudals always think that they own Ethiopia .

  Feudal and chauvinist thinkers assume themselves as givers and takers of nationality . The whole world is laughing at their empty GURA .

  WHO THE HACK GAVE YOU THE RIGHT TO TALK ABOUT MILLIONS OF PEOPLE IN OTHER KILIL ???

  MR KNOW IT ALL TIMKIHTEGNA , WHY IS IT ALWAYS THE AMHARAS TALKING TIGRAI THIS TIGRAI THAT ???

  HAVE YOU FORGOTEN THAT YOUR DAYS AS SOLE CUSTDIAN OF ETHIOPIA WAS SHATTRED A LONG TIME AGO ???

  NANA
  January 30, 2018 at 12:28 am
  Reply

 2. Who cares if they secede? I think nobody cares if cancer is removed from ones body.

  OM
  January 30, 2018 at 5:18 am
  Reply

 3. ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነገር ሲፈጠር ዘላችሁ ኤርትራ ላይ ማላከክ አይሰለቻችሁም። የኤርትራ ህዝብ በፍላጎቱ በትግሉ ነው ነጻ የወጣው። አስሬ የኢትዮጵያ ሃብት ሻእብያ ለመዝረፍ ይፈልጋል የሚል አነጋገር ይደጋገማል ግን ለመሆኑ ኢትዮጵያ በታሪዃ በምግብ ራስዋን ችላ ታቃለች? ህዝቧን በቅጡ መመገብ ያልቻለች ሃገር እንዴት ነው ለኤርትራ መሆን እምትችለው?

  Solomon
  January 30, 2018 at 5:51 am
  Reply

 4. የራሱ ሲገርመን ከገላ መለየት
  ኣዲስ ጥበብ መጣ ደረትን መጎተት
  ማን ይሆን የሚለው ደረቴ ኣይጠቅመኝም
  ማን ይሆን የሚለው ሆዴም ኣይጠቅመኝም
  ማን ይሆን የሚለው ኣከላቴ ይበለት
  ኣይሰማትም ብሎ ኣገርን መቀርጨት
  ሥጋን መቆራመት የመስለው መንፈስ
  መሬት መስላው ይሆን ሥሯ የሚቆረስ
  ሁሉን ማድረግ ቢቻል ለመቆራረሻ
  ሥሯ ላይበጠስ የዛለች ማርከሻ
  ቀን ይቆጥር እንደሆነ ህመም ማስታገሻ
  ኣገር ትሽራለች ሥሯ ይለውም ግርሻ

  ሳሀል
  January 30, 2018 at 7:51 am
  Reply

 5. የራሱ ሲገርመን ከገላ መለየት
  ኣዲስ ጥበብ መጣ ደረትን መጎተት
  ማን ይሆን የሚለው ደረቴ ኣይጠቅመኝም
  ማን ይሆን የሚለው ሆዴም ኣይጠቅመኝም
  ማን ይሆን የሚለው ኣከላቴ ይበለት
  ኣይሰማትም ብሎ ኣገርን መቀርጨት
  ሥጋን መቆራመት የመስለው መንፈስ
  መሬት መስላው ይሆን ሥሯ የሚቆረስ
  ሁሉን ማድረግ ቢቻል ለመቆራረሻ
  ሥሯ ላይበጠስ የዛለች ማርከሻ
  ቀን ይቆጥር እንደሆነ ህመም ማስታገሻ
  ኣገር ትሽራለች ሥሯ ይለውም ግርሻ

  ሳሀል
  January 30, 2018 at 8:11 am
  Reply

 6. ይቺ የህወሃት/ትግሬዎች የተለመደች የአስተያየት መሰብሰቢያ ሃሳብ ናት፡፡
  ለማንኛውም ሰውየውን “ባቄላ ጠፋ ቢሉት – ፈሱ ቀለለ” አለ አሉ ፡፡
  በእኔ ነፃ አስተያየት እና ሙሉ እምነት – ትግራይ ጦስ-ጥምቡሳሳችንን ይዛ ብትገነጠልም ሆነ ብትገነጣጠል – የኢትዮጵያ ነቀርሳ ተነቀለ ማለት ነው!!!
  ምክንያቱም አንድም ኢትዮጵያዊ ትግራይ ውስጥ የለም እና፡፡ ኢትዮጵያም በትግራይ ክልል ደሟ እየተመጠጠ እንጂ እየተጠቀመች አይደለም እና፡፡

  ግን ትግራይ ስትገነጠል ባንዳ ትግሬዎች በአቀዱት እና በቋመጡለት ዓላማ መልኩ አይደለም፡፡

  1. አንተ ከታች በካርታው ላይ እንዳመለከትከው ሳይሆን ከአማራ እና አፋር ክልሎች የወሰደቻቸውን ለም እና ስትራቴጂካዊ ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ ከ1983 ዓም በፊት ወደነበሩበት እናት አገራቸው ኢትዮጵያ የመመለስ ግዴታ አለባቸው፡፡

  2. ህወሃት/ትግሬዎች ከ1972 ዓ.ም ጀምረው በጎንደር እና ወሎ ክፍላተ-ሃገራት፤ እንዲሁም ህወሃት/ትግሬ ሥልጣን ላይ ከተቆናጠጡበት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያውያን ላይ ለፈፀሙት፣ ላስፈፀሙት የሰው ሕይወት መጥፋት፣ ከቤት ንብረት መፈናቀል እና መሰደድ፣ ላደረሱት/ላስደረሱት የንብረት መውደም በዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ መሆን አለባቸው፡፡ ይጠየቃሉም፡፡ እያንዳንዱ ትግሬ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የዘረፋው ጥቅም ተካፋይ፣ የግድያው ወንጀል ተባባሪ እና የገዳዩ ህወሃት/አጋዚ ደጋፊ እና አባል በመሆናቸው ለተጎጂ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች፣ ክልሎች ትግሬዎች እና የትግራይ ክልል ተገቢውን ካሣ መክፈል አለባቸው፡፡

  3. ህወሃት/ትግሬ ፖለቲካውን፣ መከላከያውን፣ ደህንነቱን፣ የሲቪል መሥሪያ ቤቱን፣ የንግድ ተቋማትን፣ ወዘተ… በበላይነት በመቆጣጠር፤ የልጅ ልጅ ከፍሎ የማይጨርሰው ብድር በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ስም በመበደር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከደረጃ በታች የሆነ የማስመሰያ ልማት አልፎ አልፎ በመሥራት፣ ለትግሬዎች የሥራ ዕድል ስለፈጠሩበት እና በስልጣናቸው በመባለግ (በሙስና) ያለአግባብ ስለበለጸጉበት፣ እንዲሁም ትግራይን ከሚገባት በላይ በአድሎ ስለገነቡበት የዚህ ሁሉ የውጭ ብድር ተጠያቂ ትግሬዎች እና የትግራይ ክልል ብቻ እና ብቻ ናቸው፡፡

  4. ትግሬ የተባለ ሁሉ የኢትዮጵያን ምድር ለቆ፣ ተጠራርገው መውጣት (Deport መደረግ) አለባቸው፡፡ ይደረጋሉም፡፡

  5. የአሰብ ወደብም የቀድሞ የወሎ ጠቅላይ ግዛት (ክፍለሃገር) አካል፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ስለሆነች ሕጋዊ የባለቤትነት መብታችንን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንጠይቃለን፡፡

  6.ወዘተ …. (ጨምሩበት)

  ይህንን ይፈጽሙታል ማለት ሰማይ ይታረሳል ማለት ነው፡፡
  ይህንን ስለማይፈፅሙት ደገሞ፣ ትግራይ እና ከሃዲ ባንዳ ትግሬዎች ተገነጠሉም አልተገነጠሉም፣ የእኛ “ትግል ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል” የምንለው ለዚህ ነው!!!

  Meyisaw Thewodros
  January 30, 2018 at 10:26 am
  Reply

 7. All we need is the unification of Amara and Oromo. Together we are the third of the population and yet we have been subjected to harsh and outright mischief by the Tigrian tugs. Let’s put the past in the past where it belong, and let’s focus on the future to build a fairer Ethiopia for all it’s citizens.
  The Oromo and Amara unity is the must to defeat TPLF. Let’s do it for the 700,000 displaced Oromo and the thousends killed in the past three years alone. Let’s do it for the Amara youth who has been killed demanding their rights.

  The Oromo and Amara unity is the must to liberate our country.

  One can’t do it by itself without full cooperation of the other. We have done it before to protect our country from foreign invaders, we should do it again.

  Let’s make unity today not tomorrow so that the suffering of our people will end quickly. Let’s reject the pessimists and the naysayers.

  Rise up
  January 30, 2018 at 10:58 am
  Reply

 8. You don’t know Eritrean so the, it better to stop not confused your peoples, you and some of you are writing about Eritrea and the Eritrean people and honestly know we are feeding up, pls you have a lot of an finish work if you want to write about your country rather than jamb to other countr. Full stop don’t cray

  Nabot
  January 30, 2018 at 11:00 am
  Reply

 9. ቅጥፈት ቤት ሰርታ!
  ማወናበድን ተጠግታ
  ልደር ብላ ተጠግታ!

  ቅሌትን ዳሩ ተሸፋፍና
  ትንንቅ ሆኖ ሃቅ ታየና
  ውጪ ነፍስ፣ግቢ ነፍስ ሆነና
  ኣምቡላንስ ቢፈለግ ጠፋና
  ቃሬዛ ፍለጋ፣ ወጣቱ እንዲሸከም ተባለና
  ወረወረው! በሽተኛውን ባዘተና!!

  ቅጥፈት ልትታክም ሆኖ ተብሎም
  ማወናበዷ ታውቆባት እንዲያ ሆኖም
  ኣልሸሹም ዞር ሆነ፣ እልሸሹም!!

  Mulugeta Andargie
  January 30, 2018 at 2:41 pm
  Reply

 10. ቆይ ቆዬ ትግራይ የኢትዮጵያ ታሪክ አካል መሆኑ እየታወቀ እንዴት ነው ወዲያ ይህዱልን የሚባለው ……. የሚያስፈልገው የኦሮሞና አማራ መተባበር ብቻ ነው የሚለውን ሃሳብ ስንመለከተው ደግሞ ጥሩ ፍቅርና አንድነት ያስፈልጋል ማለትን ያስብላል፡፡ ሆኖም የአገሪቱን ሙሉነት አያሳይም፡፡ እናም ፅሁፍ ሲፃፍ በጥልቀት እየታሰበበት ቢሆን ጥሩ ነው እላለሁ፡፡

  GSS
  January 31, 2018 at 3:41 am
  Reply

 11. AMHARAS THINK THEY OWN THE COUNTRY AND THEY CAN DECIDE WHO LEAVES AND WHO STAYS .

  MILUSHIN BESEMASH , GEBEYA BALWETASH !

  NANA
  February 1, 2018 at 2:11 am
  Reply

 12. Ahya nana! Yareje mezmurehen eyezemerk wede meqele. What are you doing here you nazi weyane!!The Snhara, Oromo, eritreans, afara, somale…. say together we hate you.

  nabil
  February 1, 2018 at 6:58 pm
  Reply

  • YOU IMPOVERISHED THE NATION FOR HUNDREDS OF YEARS .

   HATED , INSULTED AND DESTROYED OTHER NATIONS AND NATIONALITIES .

   WOLF IN A SHEEP CLOTHING !!!

   THE TRUTH IS ,

   IT IS ONLY THE EXISTENCE OF WOYANE THAT SPARED YOUR SORRY ASS FROM BEING CHASED BY NATION AND NATIONALITIES .

   THE MINUTE WOYANE LEAVES

   YOU WILL SEE HOW MUCH OTHERS LOVE YOU !!! KKIKKIKI

   nana
   February 2, 2018 at 12:00 am
   Reply

 13. Dear Editor
  Tigrae Ethiopia….Ethiopia Tegrae
  No seperation they are one country

  semayehu zenebe
  February 3, 2018 at 3:11 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *