ነፃ አስተያየቶች

ግንቦት ሰባት ወዴት እየሄደ ነው!? – ከአቻምየለህ ታምሩ

ብአዴን የሚባለው የወያኔ ነውረኛ ድርጅት ከቀናት በፊት ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫው ሰሜን ወሎ ወያኔ ያካሄደውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ሕዝቡ እየወሰደው ባለው ራስ የመከላከል እርምጃ ትግሬዎች በዘራቸው ብቻ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ መናገሩን ተከትሎ ሃቁ ምን እንደሚመስል መሬት ላይ እየሆነ ያለውን ማስረጃ በማሰባሰብ እዚህ ፌስቡክ ላይ በማተም ብአዴን ባማራ ሕዝብ ላይ ያካሄደው ውግዘትና የፈጠራ ክስ መሰረት የሌለው እንደሆነ አስረግጠን ነበር።

ሰሜን ወሎ ወያኔ ያካሄደውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ሕዝቡ በወሰደው ራስን የመከላከል እርምጃ ጥቃት የደረሰባቸው ሕዝቡን የሚያስገድሉ ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ ባንዳ አማራዎች ጭምር ናቸው። ይህንን ለመረዳት ከሁለት ቀን በፊት ያተምነውን ይህንን ትር በመጫን መመልከት ይቻላል፤ 

ንጉሱ ጥላሁን የሚባለው የብአዴን ቃል አቀባይ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ቀርቦ ትግሬዎች [በአማራ] ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ተናግሮ ነበር። ሆኖም ስለደረሰው ጥቃት፣ተጎዳ ስለሚባለው ንብረት መጠን፣ አይነትና ስለተጎዱ ሰዎች ቁጥር እንዲገልጽ ሲጠየቅ ግን መረጃው በእጁ እንደሌለና ገና እየተጠናቀረ እንደሆነ ተናግሯል። ይታያችሁ! ደረሰ ስለሚለው ጥቃት፣ተጎዳ ስለሚባለው ንብረት መጠንና አይነት እንዲሁም ስለተጎዱ ሰዎች ቁጥርና ዝርዝር እንዲገልጽ ሲጠየቅ በእጁ መረጃ የሌለ ሰው እንዴት ብሎ ነው ትግሬዎች በትግሬነታቸው ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ማወቅ የሚችለውና ትግሬዎች [በአማራ] ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ሊናገር የሚችለው?

በዚህም የተነሳ ነው ደረሰ ስለሚለው ጥቃት፣ተጎዳ ስለሚባለው ንብረት መጠንና አይነት እንዲሁም ስለተጎዱ ሰዎች ቁጥርና ዝርዝር እንዲገልጽ ሲጠየቅ በእጁ መረጃ እንደሌለ የተናገረው ንጉሱ ጥላሁን «ትግሬዎች [በአማራ] ቃት እየተፈጸመባቸው ነው» ሲል የሰጠው መግለጫ አይን ያወጣ ውሸት፣ ነውረኛነትና አለቃውን ወያኔን ለማስደሰት ሲል በትዕዛዝ የሰጠው የሕወሓት መግለጫ ነው ያልነው።

እንግዲህ! በፈጠራ ውሸት መግለጫ አቅራቢነቱ ያወገዝነው ነውረኛው ብአዴን የሰጠውን አይነት መግለጫ በማውጣት ሕዝባችን እያደረገ ባለው ትግል ላይ ተመሳሳይ በደል የሚፈጥሩትን ማንኛውንም አካላት ዝም አንልም።

ግንቦት ሰባት ዛሬ [ከደምሕት ጋር በመሆን] በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ ትግል ከሕወሓት ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች በትግሬነታቸው ብቻ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልጧል። ይህ ግንቦት ሰባት ያወጣው የነውረኛው ብአዴንና የፋሽስት ወያኔ አይነት የውሸት መግለጫ በውሸትነቱና የሕዝብ ትግልን ጥላሸት በመቀባቱ ልክ እንደ ብአዴንና ሕወሓት መግለጫ ሁሉ በጥብቅ የሚወገዝ የክፋት ተግባር ነው።

በጣም ገራሚው ነገር ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያ ውስጥ ተደረገ በሚባለው ጸረ ወያኔ ተጋድሎ ሁሉ እኔ አለሁበት እያለ ኃላፊነት ሲወስድ ከርሞ ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች እየተጠቁ ነው የሚል ራሱን የሚያወግዝ መግለጫ ይዞ መምጣቱ ነው። ጤና ይስጥልኝ ግንቦት ሰባቶች! ኢትዮጵያ ውስጥ ተደረገ የተባለን ጸረ ወያኔ ተግባር ሁሉ የኛ ነው ስትሉ ከርማችሁ ዛሬ
ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች እየተጠቁ ነው ስትሉ የምትከሱት ማንን ነው? ራሳችሁን ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ተደረገ የተባለን ጸረ ወያኔ ጥቃት ሁሉ እናንተ ስትፈጽሙ ከከረማችሁ ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት ሳይኖራቸው ተጠቁ ያላችኋቸው ትግሬዎችም ያጠቃችኋቸው እናንተ ናችሁ ማለት ነው።

ይህ ከሆነ ደግሞ ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች ተጠቁ ካላችሁ እየተካሄደ ባለው ትግል ጀግባ ሁሉ እናንተ አለን ስለምትሉ ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች ከተጠቁ ያጠቃችኋቸው እናንተ ናችሁና ተፈጠመ ያላችሁትን ጥቃት የማውገዝ ሞራሉ የላችሁም። ተፈጠመ ያላችሁትን ጥቃት የማውገዝ ሞራሉ የሌላችሁ እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ ትግል ሁሉ እናንተ እንደነገራችሁን ከጀርባ ስላላችሁ
ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ትግሬዎች ማጥቃት አልነበረባችሁምና ነው።

የሆነው ሆኖ ይህ የግንቦት ሰባ የውሸት መግለጫ ፍጹም የተሳሳተ፣ አንዳችም ማስረጃ የማይቀርብበትና ሕዝባች የማይተካ መስዕዋትነት እየከፈለ እያደረገ ያለውን ትግል የሚኮንን በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባው ተግባር ነው።

እስቲ የመግለጫው ባለቤቶች የሆናችሁ ግንቦት ሰባቶች የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ?

1. የትኛውና መቼ ነው ከሕወሓት ጋር ግንኙነት የሌለው ትግሬ ነው በሕዝባዊ ትግሉ ጥቃት የደረሰበት?

2. ጥቃት ደረሰበት ያላችሁት ትግሬው ከሕወሓት ጋር ግንኙነት ይዉረው አይኑረው እንዴት አረጋገጣችሁ?

3. ከሕወሓት ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ተጠቁ ያላችኋቸው ትግሬዎችስ ቁጥር ስንት ነው?

4. ከሕወሓት ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ተጠቁ ያላችኋቸው ትግሬዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ሁሉ ትግሬዎች በትግሬነታቸው ብቻ ጥቃት እየደረሰባቸው ከሆነ ለምን ሁሉም ትግሬዎች አልተጠቁም ትላላችሁ?

5. በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በሚማሩ ተማሪዎች ዘንድ ታየ ባላችሁት «መጨካከን» ማን በማን ላይ ነው የጨከነው? በጨካኑ ወያኔና ጭካኔ በሚፈጽምባቸው ንጹሐን ተጨፍጫፊዎች መካከል የበይና የተበይ ግንኙነት ሁለቱንም እንደ በይ ቆጥሮ «መጨካከን» በሚል መግለጹ ከሕዝብ ወገንተኛነት መራቅ አይደለምን?

እስቲ መልሱልን?!

17 Comments

17 Comments

 1. kastow

  February 1, 2018 at 11:38 pm

  asafare .shame for you.

 2. nana

  February 1, 2018 at 11:42 pm

  shameless lie !!!!

  Those hooligans attacking tigrians should not cry if same happens to them any time any where

 3. Ewunet

  February 2, 2018 at 2:49 am

  I can’t believe that . Is that statement really issued from AG7? What the hell are they concerned about Tigres? Are they condemning the people of Wollo that has proven their bravery for Tigrians and put the regime out of action .

  Till this moment I was die hard supporter of AG7 but now they let me down. OMG I am lost of words to express my disappointment.

  In stead of complimenting the positive action of Wolloyes they started to defend Tigrians. By the way there are no two kinds of categories in Tigray. They are one and all Woyanes. Shame on you AG7.

  We donot have mercy no matter who you are. If you are against the people of Wollo we are also the same to you.

  I am Wolloye and proud of my people.
  Wolloyes are brave and patriotism is in their blood.

  • Alex

   February 2, 2018 at 12:44 pm

   This is the true color of Gim bot 7 when it comes to the struggle of Amhara people for its survival

   This is good lesson for those Amhara foot soldiers Gim bot 7

   Victory to Amhara people
   Down with All anti Amhara groups!!!

 4. ራሄል

  February 2, 2018 at 4:26 am

  ኢሳያስ ዘገብ ብሎት ይሆናል ምን መላ አለው ጌቶችን ፍላጎት ማርካት ብቻ ነው ስራው ሚስኪን ክክክክክክ

 5. ourge kebed

  February 2, 2018 at 5:58 am

  deer Achame, ginbot 7 did not say that people those who are not with TPLF are attacked by.but, they get hate due to the wrong policy of the government.because of this the statement has tried to convey the message that the policy the government has exercised is the cause to be hated the the people of tigray . so in order to save the people from this chaos, we all have to stand together and condemn the ethnic rule which divide the people by their raise not by geographical area

  • Mechal Degu

   February 2, 2018 at 11:20 am

   That is not what the AG7/TPDM statement said. The statement condemned the killing of Tigres as ‘revenge’ (biqela) by other Ethiopians. The statement did not condemn the killing of innocent Timket akbari

 6. Faseka Assefa

  February 2, 2018 at 7:27 am

  This guy is jumping like hungry dog.Always he want some problem from unti weyanne I donnot why. The clapper is zehabesha no from him.

 7. Meseret

  February 2, 2018 at 12:16 pm

  Here we go again!!!! Is this the official communique of Ginbot 7 or that of Madebos and the likes-the anti-Amhara wing of Ginbot 7? When I think about the last 25 yrs of Ethiopian politics, there is one thing that always surprises me. Why all these so-called opposition parties in unison hate Amharas? Be it MEDREK, OLF, Ginbot 7, TPLF etc. Go to Gojjam, Gondar, and Wollo and see who these people are-hardworking and kind but poor, ever ready to die for their country.
  Is the crime of the Amharas the fact that they identify themselves as Ethiopians rather than as Amharas?

  Ginbot 7: Beware that ESAT is still on the air only because of the generosity of Amharas-of course, not Oromos or Tigres or others. You know that very well!!!

 8. Rise Up

  February 2, 2018 at 2:00 pm

  G7 leadership are a collection of a bunch of cowards. If anyone is waiting for G7 to liberate our country from the Weyane’s tugs, you are kidding yourself.
  THE ONLY THING THEY CAN BOMB IS THEIR FART! THE ONLY THING THEY KNOW HOW TO BOMB IS THEIR FART!

  I feel sorry for the young people who trusted them and suffer in the hot weather of Eritrean mountains, and just wasting their lives.

  Furthermore, we know that ESAT is an effective media, and they need to be supported, but they need also to distance themselves from this guy name Berehanu Nega. The only thing he knows is to talk, and give us empty hope. Therefore, ESAT support the struggle inside Ethiopia, and help to coordinate the Amahara and Oromo struggle. The only way we can see change is if the Oromo and the Amahara lead the struggle with close communications, plans, and strategies. We can be successful if we can do this, and that is the ONLY sure way to defeat Weyane. Apparently, Weyane is not scared of Berehanu, but they scared and they know that they will be history if the Oromo and Amahara coordinating their struggle as one. That is the only thing scares them, not Berhanu and his army.
  Have you heard Seyum Mesfin saying their party is in a crossroad. Have you heard of him saying that because of G7? Absolutely not!They are saying it now because of the unity we seen in recent months between the Amahara and the Oromo, that’s what scares them to death. Not the Brehanu army.

  TOGETHER THE OROMO AND THE AMAHARA WILL MAKE ETHIOPIA FREE FOR ALL!

 9. Samson

  February 2, 2018 at 4:36 pm

  You are wounderful u are rely pur
  e Amhara
  Your explaine is clear when i hear The news i wasn chocken.i stop to support this bulishet groups and i hop tamne beyene The time to waka up .

 10. nabil

  February 4, 2018 at 3:26 pm

  Ginbot 7 wedetem alhedem. Telatun weyanen lematfat serawen eyesera new. Enetebaber yelal tebaberew kalfelekew tewew. Aleq deqeq. Ante men eyaderek new? Menem new melsu. We have a big enemy infront of us. Some people like you spent so much time for such small problem. It is no wonder if the white people call us “neger”. We make sure for the whiti that we can’t solve our problem peacefully and wisely.

 11. Taye

  February 4, 2018 at 3:56 pm

  I see your point but we can’t discredit everything thing they have been doing because of this one letter. They have to work around a lot of challenges . I believe,despite their assurance that they are not under shabia’s influence, they have to walk a fine line not to upset Esayas Aforeke. I also believe that G7 was pressured by Tehden to issue this letter. If they don’t go with it it makes them look like they support attack against innocent Tigrians. But they should have issued a balanced statement which supports the people’s struggle and also warns the Tigrians who blindly support woyanne. At same time they could also warn the people not to be carried away with their hate to woyanne and their majority Tigrianian supporters and direct their anger against minority innocent tigrians. I believe G7 will learn from this mistake and watch the way they word this kind of statements. Also avoid looking like they can’t stand by themselves and always have to get approval of these groups who have other agendas.

 12. Belay Akalu

  February 5, 2018 at 9:28 am

  ይሄ አቻምየለህ የተባለ ወናፍ የአግ7 ላይ ከመሬት ተነስቶ እንደ ጀርባ ቅማል ይዞ እግሩ ከብአድን ተለቆ አሜሪካን ከገባ ጀምሮ ይዞቸዋል
  እኔን አንድ ግዜ እራሱን የሚያጋልጥ መረጃ አምጥቼ በፌስቡክ ሳፋጥጠው ባን አደረገኝ ከዛ ብዙ የማውቃቸው ሰዎች የእሱን የብአድን የቀድሞ ማንነት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው ሊያፋጥጡት ሲሞክሩ በተመሳሳይ ባን ያደረገና እራሱን የአማራ ተቆርቋሪ አድርጎ የሚቆጥር ግብዝ ነው
  ሲጀመር የእሱን ዝባዝንኬ የቃላት ድሪቶ ሼር ከማድረግህ በፊት አቻምየለህ ታምሩ ማነው ብትል ይመለስልሀል፡አቻምየለህ ታምሩ ማለት ከአማራው ህብረተሰብ የተወለደ ነገር ግን እንደ አንዳንድ በሆዳቸው እና በጥቅማቸው በሚንቀሳቀሱ አማሮች ልበ እርኩስ የሆነና በጣም ከልጅነቱ ጀምሮ በአካባቢው ተወላጆችና በተማሩት ጓደኞቹ ብዙ ተንኮል በመስራት የሚታወቅ እርጉም ነው፡
  እድሜው ለአቅመ ካድሬ እንደደረሰ በእርጉምነቱና ለአካባባው ባለው ማህበረሰብ ካለው ጥላቻ የተነሳ በት/ቤት በብአድን ካድሬዎች በመልመል በተለይ ከምርጫ 97 ምርጫ በኋላ የብዙ ምስኪን ነገር ግን ጀግና የነበሩ የአማራ ተወላጆችን ለብአድን ካድሬዎች በመጠቆም ያስበላና በዚህ ስራው የብአድን ቡድን ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አውሮፓ ፌንላንድ ልኮት የተማረ ከዛም ሲመለስ ለብአድን ከነበረው ታማኝ አገልጋይነት በወያኔ ባለስልጣኖች ተመርጦ መቀሌ ዩንቨርስቲ ያስተምር የነበረ ነው
  ከዛም ከጊዜ በኋላ ባሳየው ትልቅ የአድርባይነት አስተዋጽኦ ወያኔ የዲያስፓራውን ትግል በአማራ ትግል ስም እንዲያሽመደምዱ ከላካቸው ግለሰቦች መካከል ከጓደኞቹ ከነ ምስጋናው አንዱአለም፡ አያሌው መንበሩ ፡ ሙሉቀን ተሰፋው እና ሌሎች ጋር በመሆን ወደ ውጪ የመጣ ሲሆን ራሱን የአማራ ተቆርቋሪ ለማስመሰልና የወያኔ ተቃዋሚ ለማስመሰል ብዙ በመጻፍ እራሱን ለመደበቅና በአንዳንድ የዋህ ግለሰቦች የአማራ አዳኝ እና ፈዋሽ አድርጎ ለመታየት ቢሞክርም ማንነቱን ለሚያውቅ አይገርምም
  ይህ ግለሰብ ስራው አግ7 እየተከታተለ በማይታወቅ መልኩ ማዳከም መሆኑን ለማረጋገጥ ብዙ መሄድ አያሻም ሲጀመር እንደ ወያኔ እንደካካቸው የብአድን ወንድሞቹ አርበኞች ግንቦት 7 ብሎ ሳይሆን ግንቦት 7 እያለ ድርጅቱን ለማስጠላት ተጠቅሟል ሲቀጥል ድርጅቱ ካወጣው መግለጫ ውስጥ ቁንጽል ሀሳብ ወስዶ መግለጫው ያላለውን ነገር በራሱ የአማርኛ ድሪቶ አቅርቦ ድርጅቱን ለማስጠላት ሲንፈራገጥ ይታያል፡

  • Meseret

   February 5, 2018 at 9:24 pm

   Belay Akalu: What you wrote says a tone about you. You are gossipmonger. I value Achamyeleh simply for what he is doing right now!! He tirelessly exposes all the evils the woyanes do on Amharas and other Ethiopians. I do greatly appreciate him for that.

   It is your God-given right to support G7. But it is sad an organization as great as G7 has members like who like to discuss people rather than issues-this is very low.

   By the way, what Achamayeleh said was what was said by Abebe Gelaw, Fasil Yenealem and other prominent supporters of G7.

   Next time, try to discuss issues, not people!!!

 13. tolanaayana49@gmail.com

  February 5, 2018 at 10:11 am

  99% የትግራይ ተወላጆች የወያኔ ደጋፊዎች ናቸው። በወልድያ ወይንም በሌላ አካባቢ በአገዛዙ ደጋፊዎች ላይ ጥቃት ሲሰነዘር አብዛኛው ተጠቂ ማን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም። ችግሩ መስዋትነት እየከፈሉ አረመኔዎቹን እና ዘረኞቹን ነፍስ ገዳዮች እየተፋለሙ ካሉት ወጣቶች ዘንድ አይደለም። አርበኞች ግንቦት 7 ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ማውገዙ ትክክል ሆኖ ሳለ ስህተቱ የወያኔ ካድሬዎች የሚሉትን “በዘራችን ተጠቃን” የህወሃት ፕሮፓጋንዳ እንደ ትክክለኛ መረጃ ተቀብሎና እዚያ ላይ ተመርኩዞ መግለጫ ማውጣቱ ነው። መስተካከል ወይንም መታረም ያለበት ጉዳይም ይህ ይመስለኛል።
  ከዚያ በተረፈ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ጭቃ መለጠፍን ኑሮው ያደረገ በዚህም ተግባሩ እራሱን እንደ ታጋይ ቆጥሮ የሚኖር ድኩማን ይህንን ስህተት ለአስነዋሪ ተግባሩ እንደ ማስረጃ ቢቆጥር ጆሮ ሊሰጠው አይገባም።

 14. nana

  February 6, 2018 at 12:08 am

  Let all federal regions get exta autonomy .Let THE FEDERATION GROW TO CONFEDERATION .

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

Zehabesha - Latest Ethiopian News

Copyright © 2018 Zehabesha - Latest Ethiopian News Provider. All rights reserved.

To Top