ነፃ አስተያየቶች

የሕዝብ ትግልን የወነጀለው የግንቦት 7 መግለጫ – (በጌታቸው ሺፈራው)

ግንቦት 7 ከትህዴን ጋር አወጣሁት ባለው መግለጫ ባለፉት 3 አመት የተደረጉትን የሕዝብ እንቅስቃሴዎች በአንድ ዐረፍተ ነገር አፈር ድሜ አብልቷል። በቀል የተፈፀመባቸው ናቸው ሲልም ወንጅሏል። በመግለጫው የትህነግ/ህወሓት አባላት ያልሆኑት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ከመግለፁም ባሻገር፣ “ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተነሱ የጸረ ወያኔ እንቅስቃሴዎች የበቀል እርምጃ እየተወሰደባቸው ካሉ የህወሃት ካድሬዎች በተጨማሪ ከህወሃት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ያልነበራቸው ሰዎችም የጥቃቱ ሰልባ እንደሆኑ መስማት እየተለመደ መጥቶአል።” ሲል “የበቀል እርምጃ ተወስዷል” ሲል የሕዝብ ትግልን ያልተገባ ትርጉም ሰጥቷል።

ግንቦት 7 በሰሜን፣ ይሁን በደቡብ የተነሳ እንቅስቃሴ ላይ እጁ እንዳለበት ሲገልፅ ቆይቷል። በ2006 ዓም የቴፒ ወጣቶች እንቅስቃሴ ላይ እጄ አለበት ብሎ ነበር። ቂሊንጦ ያገኘሁት የቴፒ ወጣቶች መሪ እንዳጫወተኝ ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ሊኖረው ቀርቶ ስለ ግንቦት 7 የሚያውቀው እስር ቤት ከገባ በኋላ ነው። ግንቦት 7 የሌለባቸውን በርካታ እንቅስቃሴዎች የእኔ ናቸው እንደሚል የተረዳሁት ከዚህ በኋላ ነው። ሆኖም ሕዝብ የስነ ልቦና ብርታት እንዲኖረው፣ እንቅስቃሴውን እውቅና የሰጠው አካል እንዳለ እንዲያውቅ ከሚል ቀናኢ የፕሮፖጋንዳ ይሆናል በሚል በርካቶች ዝምታን ሲመርጡ ቆይተዋል። ይሁንና ግንቦት 7 የእኔ እጅ አለበት እያለ መግለጫ ሲያወጣበት የነበር የሕዝብ ትግል ከገዥዎቹ እኩል “በማንነት ላይ የተወሰደ በቀል” አድርጎ መግለጫ አውጥቷል። ለዚህ ፍረጃውም የገዥዎቹ ተከፋዮች ሳይቀሩ “ደግ አደረክ” ብለውታል።

ግራ የሚያጋባው መግለጫ

ሁለቱ ድርጅቶች የሰጡት መግለጫ “በትግራይ ሥም እየማለና እየተገዘተ ለመንግሥት በትረ ሥልጣን የበቃው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ላለፉት 26 አመታት በአገራችንና በህዝባችን ላይ ያልፈጸመው በደል የለም።” የሚል መንደርደሪያ አስቀምጠዋል። እንደ ድርጅት መሪዎቻቸው ተማክረው፣ መክረው ዘክረው ትህነግ “በትግራይ ስም እየማለ” በፈፀመው በደል ባለፉት 3 አመታት እነሱ አለንበት እያሉም ቢሆን የተበደለ፣ ፊቱ ላይ የንፁሃንም ደም ያየ ሕዝብ ያለ መሪ ድርጅት (በግብታዊነት) ባደረገው ትግል አጣርቶ፣ መርምሮ……” እርምጃ ሊወስድ ይችል ነበር” ብሎ ማሰብ ከመቼው የባሰ ትዝብት ውስጥ የሚከት ነው።

በመጀመርያ ደረጃ ባለፉት 3 አመታት በተደረጉት የሕዝብ ትግሎች “ተገደለ፣ ቆሰለ፣ ተቃጠለ” ብለው በቀዳሚነት መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩት በውጭ የሚገኙት የንቅናቄው አባላት እና ኤርትራ የሚገኘው ሬድዮ ጣቢያው ናቸው። አባላቱና ሬድዮ ጣቢያው በ”ሰበር” ዜና የሚያሰራጩዋቸው ዜናዎች ባሻገር “ግፋ በለው” አይነት መልዕክት ሲያስተላልፉ እንደነበር የሚካድ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቱ “አለሁበት” የሚል መግለጫ ሲጨምር፣ ጉዳዩ ሲበርድ በርካቶች በግንቦት 7 ስም ተከሰዋል። ግንቦት 7 አለሁበት አለም አላለም ገዥዎቹ የፈለጉትን በስሙ ሊከሱት ይችላሉ። ሆኖም እነዚህን እንቅስቃሴዎች ሳይኖር አለሁ እያለ በመግለጫ ሳይቀር ሲያበረታታ የነበር ድርጅት “በቀል ተፈፅሟል” የሚል መግለጫው በገዥዎቹ የሚቀለቡት ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንኳን ደፍተው ያልፈፀሙት ሀጥያት ነው። በእጅጉ የሚያሳዝነው ግንቦት 7 “በቀል ሲወሰድ መስማት የተለመደ ነው” ሲል “በቀል ተወሰደ” የሚለውን ከሕዝብ ሊሰማው እንደማይችል ግልፅ ነው። ይህን የሕዝብ ትግል የሚያጠለሽ ወሬ ሊሰማ የሚችለው “ወያኔ” ብሎ ከሚጠራው እና እሱን ሲያብጠለጥሉት ከሚውሉት የስርዓቱ ደጋፊ ሚዲያዎች ብቻ ነው። በዚህም ግንቦት ሰባት ወያኔ የሚለው አካል “በትግራይ ስም እየማለ” ስቃይ ከሚፈፅምበት ሕዝብ ይልቅ “ወያኔን” እና አፈቀላጤዎችን አምኗል ማለት ነው። ለጊዜውም በዚህ መግለጫውም መግባባት የቻለው ከእነዚህ አካላት ጋር ነው።

በሕዝባዊ እንቅስቃሴው “እርምጃ የተወሰደበት”

ግንቦት 7 እና ትህዴን ባወጡት መግለጫ የህወሓት አባላት ያልሆኑ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ሲሉ ሰማነው ያሉትን አስፍረዋል። ይሁንና በመግለጫው ከትግራይ ውጭ የሚኖረው የትግይራ ህዝብ በግድም ሆነ በውድ የትህነግ/ ህወሓት አባል መሆኑን ያትታል። ከዚህም ባሻገር ይህ ሕዝብ በሕዝብ ላይ ትህነግ/ህወሓት ለፈፀመው በደል ሁሉ “መረጃ አቀባይ፤ ጉዳይ አስፈጻሚና ያካባቢው የሥርዓቱ የድጋፍ ኃይል አድርጎ ተጠቅሞበታል።” ይላል። ከትግራይ ውጭ ያለውን የትግራይ ተወላጅ በአንድ በሌላም መንገድ የትህነግ/ህወሓት አባል፣ጉዳይ አስፈፃሚ ነው ሲል የደመደመው፣ “የህወሓት አባላት ያልሆኑት በቀል ተወስዶባቸዋል” የሚል ሌላ መደምደሚያ ላይ መድረሱ መግለጫውን የተምታታ እና ግራ አጋቢ አድርጎታል።

“ባለፉት 3 አመታት በተካሄዱት ፀረ ወያኔ እንቅስቃሴዎች የሕወሓት አባል ያልሆኑትም የበቀል እርምጃ እንደተወሰደባቸው ይሰማል” ብሎ የሕዝብ ትግልን የፈረጀው መግለጫ “የትግራይ ሕዝብና ህወሓት የተለያዩ ናቸው” ሲል በማስረጃነት ያቀረበው የሞላ አስግዶሙን “የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን” ነው። በመግለጫው ደግሞ “በቀል ተፈፅሟል” የተባለው ኤርትራ ያለ ድርጅት ላይ ሳይሆን በአማራና በኦሮሚያ የሚኖሩ የ”ትግራይ ተወላጆች” ላይ እንደሆነ ግልፅ ነው። ግንቦት 7 ለዚህ በአስረጅነት የሚያቀርብልን ኤርትራ ውስጥ ያለውን ድርጅት አባላት ነው።

በዚህ አጋጣሚ “የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ” ስለሚባለው የእነ ሞላ አስግዶም ድርጅት አንዳንድ መረጃዎችን መጥቀስ ተገቢ ነው። ይህ ድርጅት ስሙ የ”ትግራይ” ይሁን እንጅ አብዛኛዎቹ አባላቱ የአማራ እና ኦሮሞ ልጆች እንደሆኑ እስር ቤት የሚገኙት የግንቦት 7፣ የኦነግ፣ የትህዴን፣ እና የአዴኃን ታጋዮች ገልፀውልኛል። ከዚህም በተጨማሪ ከሞላ አስግዶም ጋር የገቡት ወደ ትውልድ ቦታቸው (አማራና ኦሮሚያ ክልል) መበተናቸው የሚታወቅ ነው። የአማራ እና ኦሮሞ ልጆች ወደዚህ ግንቦት 7 አብሬው እየሰራሁ ነው ወደሚለው ድርጅት የሚገቡት ወደውና ፈቅደው አይደለም። በበርሃው ለቀን ስራ የሚንከራተቱትን፣ ወልቃይት ውስጥ በእርሻ እና በወርቅ ቁፋሮ የተሰማሩትን የአማራ ወጣቶች እያፈነ እየወሰደ አባል እንደሚያደርግ የታወቀ ነው። ሌላው ቀርቶ የግንቦት 7 እና የአዴኃን ታጋዮችን እያፈነ በግድ የራሱ አባል እንደሚያደርግ ፀኃይ የሞቀው ሀቅ ነው። ግንቦት 7 እና አርበኞች ግንባር አንድ ከሆኑ በኋላ ይህ ጠለፋ እንዲቀር ምክር ቢሰጡም የእነ ሞላ ድርጅት የተቀመለው አይመስልም። በመሆኑም ትህዴን ውስጥ የሚታገሉ ወጣቶች የትግራይ ህዝብ የህወሓት አባል አይደለም ለሚል መከራከሪያ ብቁ ካለመሆኑም ባሻገር ሌላ ጉድ የሚጎትት ይሆናል።

እንደ አጠቃላይ መግለጫው የእነ ሞላ አስግዶምን ድርጅት፣ ወይም ሞላ አስግዶምን ያስጠለለውን “ወያኔን” ለማስደሰት ግልፅ ባይሆንም ኮሽ ባለ ቁጥር አለሁ የሚለውን ግንቦት 7 የህዝብን ትግል የወነጀለበት፣ ግንቦት 7ንም ከመቸውም ጊዜ በላይ ትዝብት ውስጥ የከተተ እንደሆነ ግልፅ ነው።

10 Comments

10 Comments

 1. Mechal Degu

  February 2, 2018 at 11:14 am

  Getachew,
  My huts off to your with huge respect for your courage to call a spade a spade.
  Ginbot 7 is showing its inner identity: it does not stand for the political and democratic rights of Ethiopians. On the contrary, it is sabotaging the struggle for freedom from the chains of TPLF and its surrogate EPRDF. Ginbot 7 is just like TPLF–Cheats and blood-sucking!
  I helped Ginbot 7 in its initial stages, thinking that it was a nationalist organization. But I withdrew my support when I realized that it was and still is a fake group of gangsters, who amass huge money for their own benefits.
  Fellow Ethiopians!
  Just ask yourselves: It was about 3 or 4 years ago that G7 told us it was forming an alliance with the TPDM. But we haven’t heard anything about their working together since. In fact, G7 did not say anything about TPDM when it once again declared it was working with Lencho letta’s Oromo group, Afar, and Sidama group. Why are we still keeping silent about this fake movement called G7 and ESAT?
  Thanks, Getachew. We need more Getachews who have reliable information to share it.

 2. Alem

  February 2, 2018 at 3:11 pm

  Getachew, Good please your exposing them. Ginbot 7 is a group of power monger people;

 3. ገስጥ በእውነቱ

  February 2, 2018 at 3:50 pm

  “ሻቦያን ያመነ ጉም የዘገነ አንድ ነው”

  በአቶ ጌታቸው የተጻፈውን የሕዝብ ትግልን የወነጀለው የግንቦት 7 መግለጫ ደጋግሜ አነበብኩት ደፍሮ የሚናገር ጠፍቶ ነው እንጂ አብዛኛው የግንቦት ሰባት አባላቶችም ሆኑ ደጋፊዎች ይህንን ጉዳይ በሚገባ ያውቁታል:: :: ሰሞኑን ኤርትራ ምድር ላይ በተደረገው ይግንቦት 7 አመታዊ ስብሰባ ላይ ከተሳተፉት ወንድሞችና እህቶች ውስጥ ቡዙ ጥያቄዎች ተነስተው የተጠየቁ ሲሆን ለምሳሌ ገብርዪን ማን ገደለው የትና እንዴት ነው የሞተው ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠት ተቸግረው ነበር:: ገብርዪ ሲሞት በሚዲያ የቀረበው እስክሬኑ እርቃኑን ነበር የለበሰው የደንብ ልብስ የት ሄዶ ነው ለሚለው ጥያቄ መልስ ሊሰጡት ያልቻሉት የግንቦት ሰባት አመራሮች በተከታዪ አባላቶች ላይ ቁጣ መሰል ንግግሮችን ጠጠቅመዋል:: አባዛኛው ደጋፊ ተስፋ የቆረጠ ሲሆን ከአመራሮች ውስጥም ስረ የለቀቁ ይግኛሉ ከነዚህም ውስጥ አንዳንድ በስራቸው አንቱ የተባሉ እህቶች ይግኛሉ:: ግንቦት ሰባት ከተነሳለት አቆሙ እያፈገፈገ የሄደው ሻቢያ ጉያ ስር ሄዶ ሲወሸቅ ሲሆን ያለቀለት ደሞ ዋና ጻሀፊውን በህወሀት መዳፍ ስር ባሰገባበት ወቅት ነው:: ግንቦት 7 ዋናው ጻሃፊው እንዴት በህወሀት እጅ ስር እንደወደቁ እስካሁኖ ሰዓት ድረስ የተናገረው ነገር የለም:: ዋናው ጻሃፊው አቶ አንዳርጋቸው ሲታሰሩ የድርጅቱም አባልም ሆነ ደጋፊ ሌሎቻችንም የአቶ አንዳርጋቸው ስም እያነሳን ጅግነታቸውን በማወደስና ስማቸውን በማቆላመጥ አንዴ አንዴ ስንላቸው ያለእቅድ የግንቦት 7 አመራሮች ስራቸውን እየተው ጉዞ ወደ ኤርትራ ሆነ በዛኑ ሰዓት በግፈኛው ህወሀት እስር ቤት የሚሰቃዩት አቶ አንዳርጋቸው ተረሱና አርበኛ እገሌ አርብርኛ እግሌ መባል ተጀመረ:: እነዚህ የግንቦት 7 አመራሮች ኤርትራ የሄዱት የአቶ አንደርጋቸው ስም በመላው ኢትዮጵያዊ አፍ መጠራት ስለ ጀመረ በመሆኑ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይስማማበታል:: በአሁን ሰዓት ግንቦት ሰባት ነጻ አውጪ ሳይሆን እራሱ ከሻቢ ጉያ ነጻ ወጪ ነው የሚሉ አባላቶቹ ቡዙ ናቸው:: በመጨረሻም በእኔ እይታ የአገር ቤቱን ሰላማዊ ትግል እንደ ግመል ሽንት ወደሆላ የጎተተው አንዱ ግንቦት ሰባት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም:: በመጨረሻም የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮች ካፈርኩ አይመልሰኝ የሚባለውን የሞኝ ጫወታ ትታችሁ በአገር ቤት እየተካሄደውን ሰላማዊ ትግል ተቀላቀሉ:: “ሻቦያን ያመነ ጉም የዘገነ አንድ ነው” ይባላልና::

 4. Wanka

  February 3, 2018 at 6:27 am

  You are one of stupid egoistic little person may be you get paid by Tplf it’s hard to trust anyone now a days, first of all you are irresponsible person driven by emotion Ethiopia on the verge of genocide AG7 has a moral Autority to warn people thier is always collateral damage any revolution the only thing what we can do is minimize lt thier is no way we can stope it 100 % having said that please try to stope frome this thing happening instead of serving your ego it doesn’t get you anywhere

  • tarik miskeru

   February 5, 2018 at 12:04 am

   Wanka you are emotional driven. AG7 practically don’t exist. AG7 never qualify as a freedom fighter. AG7 a big propaganda air balloon, stationed on Shabiya sky, for alms collection from the diaspora.

  • Mechal Degu

   February 5, 2018 at 8:58 am

   Wanka,
   I believe you are sleep-talking! Wake up and tell us what you feel about the current situation of our country. Do not simply vomit insults; come up with facts about your statements that Ginbot 7 has done this and that act to contribute to the struggle for freedom. What Getachew and Gesit did is support their arguments with facts. Being emotional is not a solution to our current problems. Cool down and open your mind, not your mouth!

 5. tolanaayana49@gmail.com

  February 5, 2018 at 10:08 am

  99% የትግራይ ተወላጆች የወያኔ ደጋፊዎች ናቸው። በወልድያ ወይንም በሌላ አካባቢ በአገዛዙ ደጋፊዎች ላይ ጥቃት ሲሰነዘር አብዛኛው ተጠቂ ማን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አያዳግትም። ችግሩ መስዋትነት እየከፈሉ አረመኔዎቹን እና ዘረኞቹን ነፍስ ገዳዮች እየተፋለሙ ካሉት ወጣቶች ዘንድ አይደለም። አርበኞች ግንቦት 7 ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ማውገዙ ትክክል ሆኖ ሳለ ስህተቱ የወያኔ ካድሬዎች የሚሉትን “በዘራችን ተጠቃን” የህወሃት ፕሮፓጋንዳ እንደ ትክክለኛ መረጃ ተቀብሎና እዚያ ላይ ተመርኩዞ መግለጫ ማውጣቱ ነው። መስተካከል ወይንም መታረም ያለበት ጉዳይም ይህ ይመስለኛል።
  ከዚያ በተረፈ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ጭቃ መለጠፍን ኑሮው ያደረገ በዚህም ተግባሩ እራሱን እንደ ታጋይ ቆጥሮ የሚኖር ድኩማን ይህንን ስህተት ለአስነዋሪ ተግባሩ እንደ ማስረጃ ቢቆጥር ጆሮ ሊሰጠው አይገባም።

 6. nana

  February 6, 2018 at 12:05 am

  hooligans attacking people because of race should know that their naïve act will back fire on their face very very soon .

 7. ቢሊጮው ባንዲራ

  February 6, 2018 at 10:32 am

  መላጣው ባንዲራ

  የድህነት የጭቆናና የባርነት የግዞት ምልክት !

 8. ቢሊጮው ባንዲራ

  February 6, 2018 at 10:33 am

  መላጣው ባንዲራ

  የድህነት የጭቆናና የባርነት የግዞት ምልክት !

  የነጭ ድህነት የራእይ አልቦነት አርማ !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top