News Feature

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ የሕወሓት የዘር ፍጅትን አውግዞ ሕዝብ የሚወስደውን ራሱን የመከላከል እርምጃ ደግፎ መግለጫ አወጣ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) በወልዲያ በሕወሓት ሰራዊት የተደረገውን ጭፍጨፋ በመቃወመም በራያና ቆቦ፣በመርሳ እና በሌሎችም የሰሜን ወሎ አካባቢዎች ሕዝቡ የተከፈተበትን የዘር ማጥፋት ሙሉ ለሙሉ መመከት ባይችልም በገዳዮችና አስገዳዮች ላይ ብሄር ሳይመርጥ የተወሰኑት ንብረት ላይ ቁጣውን ለመግለጽ የወሰደው እርምጃ ተገቢ መሆኑን ገለጸ።ሕዝቡ  አብረውት የሚኖሩ የስርዓቱ ሰዎችን ለይቶ አውቆ የወሰደው እርምጃ በመሆኑ ይህን ሆን ብሎ በማጣመም በሕዝቡ ላይ የተፈጸመውን ግፍ አቅጣጫ ለማስቀየር በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ የንብረት ጉዳት እንደደረሰ ተደርጎ የሚሰራጨው መሰረተ ቢስ ወሬ ተቀባይነት የለውም ሲል አውግዞ ንቅናቄው መግለጫ አወጣ።ሙሉ መግለጫውን  ያንብቡት፦

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃንወቅታዊ መግለጫ

በአማራና በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በመንግስትና በንግድ ስራዎች ሽፋን የሚንቀሳቀሱ የህወሃት ሰላዮች በመላ ሀገሪቱ ሲካሄዱ የነበሩና የሚካሄዱ ህወሃታዊ የዘር ፍጅቶችን በማቀነባበር ሴራ ቀንደኛ ተጠያቂዎች እስከሆኑ ድረስ እነዚህን ፀረ ሃገርና ፀረ ህዝብ የህወሃት ሎሌ ሰላዮች በመመንጠር የተጀመረው ዘመቻ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አዴኃን ጥሪውን ያስተላልፋል።ለህወሃት ጦር ሃይል መረጃ በመስጠትና ከህወሃት ሰራዊት ጋር በመተባበር ፣መንገድ በመምራትና ጥቆማ በመስጠት፣ንጹሃን በህወሃት ቡድን ታፍነው እንዲወሰዱና ደብዛቸው እንዲጠፋ በማድረግ የህወሃት ዙፋን ዘላለማዊ እንዲሆን በገንዘብና በቁሳቁስ በማገዝና በማደራጀት ህዝብና ሀገርን በጠላትነት ፈርጆ በመሰለል ስራ የተሰማሩ እነዚህ አካላት አስፈላጊው እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል።

ሆኖም ግን በአማራ አካባቢዎች ከተቀጣጠለው ፀረ ህወሃት የአማራ ህዝብ ትግል ጋር ተያይዞ በህወሃት ሰላዮች ላይ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በዘር ትግሬ በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ላይ እየተወሰዱ ያሉ ፀረ ትግሬ ጥቃቶች ስለሆኑ ሊቆሙ ይገባል ሲሉ የሚደመጡ አንዳንድ አካላት የሌለ ታምር በመፍጠርና በህወሃት ሰላዮች ላይ የሚካሄዱ ጥቃቶችን በትግሬ ዘር ላይ የተካሄዱ ጥቃቶች አድርጎ መመልከትና ፀረ ትግሬ የዘር ጥቃት እንደተካሄደ አድርጎ በማስመሰል መሰረተ ቢስ አሉባልታ በማሰራጨት ጸረ ህወሃት ትግሉ ወደ ፊት እንዳይቀጥል የሚደረገው ጥረት የህዝብን ክብር ዝቅ የሚያደርግና የሚያዋርድ ጉዳይ እስከ ሆነ ድረስ ይህን ዓይነት አመለካከት የሚያራምዱ ሊቆጠቡ ይገባል።ይህ በዘር ትግሬ በሆነው የትግራይ ህዝብ ስም ህወሃት እራሱን ለመከላከልና ለማዳን ሲል ከሚናገረው ንግግር የተለየ አይደለም፡፡ በእርግጥ በሰሜን ወሎ ወልድያ መርሳና ቆቦ ላይ በህወሃት የታጠቀ ጦር ሰራዊት በአደባባይ ጅምላ ስለተረሸኑ ንጹሐን አማራዎች ምንም ለማለት ያልደፈሩትና በዘር ተነጥለው በግፍ የተረሸኑ ንፁሃን አማራዎች ጉዳይ ያላሳሰባቸው እነዚህ አካላት ለምን ሱቃቸው የተቃጠለ የህወሃት ሰላዮች ንብረት መውደም እንዳሳሰባቸውና ይህንንም ለምን ጸረ ትግሬ የዘር ጥቃት እንዳሉት እጅግ የሚገርም እንቆቅልሽ ነው።ሰሜን ወሎ ላይ በተቆጡ የአማራ ወጣቶች የህንጻ መስታዎት መስበር ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነው ብሎ ያወገዘ አካል ህጻናትን ጨምሮ በአደባባይ የተረሸኑ አማራዎችን ፍጅት ለምን የዘር ጥቃት እንዳላሉና በዚህ ጉዳይ ላይ ድምፃቸውን አለማሰማታቸው የሚገርም ነው።ጭራሽ የሚያሳዝነው በአማራ ህዝብ ገንዘብ እየጨፈሩና አማራውን እየማገዱ ህወሃት ያለፈበትን የብልጣብልጥ ቁማር የሚቆምሩ አካላት መሪ ተዋናዮች መሆናቸው ነው።

አማራ የሆነ ሁሉ ከማን ጋር መታገል እንዳለበት ይወቅ!!

 

በቁርጥ ቀን ልጆች አጥንትና ደም ወያኔ ይደመሰሳል! አማራው ከታወጀበት የዘር ማጥፋትና ማፅዳት እራሱን ይታደጋል!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top