News Feature

ለጀነራል ሳሞራ የኑስ አራት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራሎች ተሾሙ | አለ ነገር??

(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለ40 ብ/ጄነራሎች፣ ለ14 ሜ/ጄነራሎች፣ ለ3 ሌ/ጄነራሎች፤ ለ4 ጄነራሎች ወታደራዊ ማዕረጎች ሰጡ:: ለጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ አራት ምክትሎች እንደተሾሙላቸውም ተገልጿል::

በዛሬው ሹመት አራት መኮንኖች የሙሉ ጄነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው ሲሆን የሳሞራ የኑስ ምክትል ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸው ወትሮም ከወ/ሮ አዜብ እና አባይ ወልዱ ግሩፕ ጋር ነበር እየተባለ የሚነገርላቸው ጄነራል ሳሞራ የኑስን ለመምታት ወይም ስልጣን ለማሳጣት የተደረገ ሴራ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ::

የሳሞራ ምክትል ኢታማዦር ሹም ሆነው የተመረጡት: 1. ሌ/ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ይመር 2. ሌ/ጄኔራል አብረሃ ወ/ማርያም ገንዘቡ
3. ሌ/ጄኔራል አደም መሐመድ ሟህመድ እና 4. ሌ/ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለልቻ ናቸው::

ጄነራል ሰዓረ መኮንን ጀነራል ሳሞራ ለህክምና በሚወጡበት ወቅት ቦታቸውን ሸፍነው ሲሰሩ እንደቆዩ የዘ-ሐበሻ ምንጮች የሚናገሩ ሲሆን ሳሞራ ድንገት ከቦታው ቢነሳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙን ቦታ እኚሁ ሰው ይይዙታል ተብሎ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል::

በዛሬው ዕለት ሹመት ያገኙትን መኮንኖች ዝርዝር ይመልከቱት:: (ስለመከላከያው ምስጢራዊ መረጃ ለማየት እዚህ ይጫኑ)

 

የብርጋዴር ጀነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው

1. ኮሎኔል ፍሰሃ ስንታየሁ ዕምሩ
2. ኮሎኔል አስረሴ አያሌው ተገኘ
3. ኮሎኔል ደዲ አስፋው አያኔ
4. ኮሎኔል ዓለማየሁ ወልዴ ጅሎ
5. ኮሎኔል በርሄ ኪዳነ ስራፍኤል
6. ኮሎኔል ዳዊት ወልደሰንበት አውግቸው
7. ኮሎኔል አስፋው ማመጫ ይርዳው
8. ኮሎኔል ጥላሁን አሸናፊ ማሞ
9. ኮሎኔል ግደይ ሀይሉ ገብረእግዚአብሄር
10. ኮሎኔል ሽመልስ አጥናፉ ድንቁ
11. ኮሎኔል ተስፋዬ ተመስገን አባይ
12. ኮሎኔል ደሳለኝ ዳቼ ኡልቴ
13. ኮሎኔል አባዲ ሰላምሳ አበበ
14. ኮሎኔል መኮንን በንቲ ቴሶ
15. ኮሎኔል ከበደ ረጋሳ ገርቢ
16. ኮሎኔል ታገሰ ላምባሞ ድምቦሬ
17. ኮሎኔል ነጋሲ ትኩእ ለውጠ
18. ኮሎኔል ዳኛቸው ይትባረክ ገ/ማርያም
19. ኮሎኔል ፍቃዱ ፀጋዬ እምሩ
20. ኮሎኔል ይርዳው ገ/መድህን/ ገ/ፀድቅ
21. ኮሎኔል ይልማ መኳንንት ተንሳይ
22. ኮሎኔል ብርሃኑ በቀለ በዳዳ
23. ኮሎኔል ጉዕሽ በርሀ ወለደስላሴ
24. ኮሎኔል አባተ ዓሊ ፍላቴ
25. ኮሎኔል አለሙ አየነ ዘሩ
26. ኮሎኔል ብርሃ በየነ ወልደንጉስ
27. ኮሎኔል ሀይሉ እንዳሻው አቶምሳ
28. ኮሎኔል ገ/ህይወት ሳሲኖስ ገብሩ
29. ኮሎኔል ከበደ ፍቃዱ ገ/መድህን
30. ኮሎኔል መኮንን አስፋው ቀልቦ
31. ኮሎኔል አለምሰገድ ወ/ወሰን በርሄ
32. ኮሎኔል ሰለሞን ቦጋለ መኮንን
33. ኮሎኔል ወ/ጂወርጊስ ተክላይ አስፋው
34. ኮሎኔል ተሾመ ገመቹ አደሬ
35. ኮሎኔል ሰይድ ትኩዬ አበጋዝ
36. ኮሎኔል መንግስቱ ተክሉ ተሰማ
37. ኮሎኔል ኑሩ ሙዘይን ኣራሮ
38. ኮሎኔል ዋኘው አለሜ አያሌው
39. ኮሎኔል ሓድጉ ገብረጊወርጊስ ገብረስላሴ
40. ኮሎኔል መኮንን ዘውዴ ዳመነ

የሜጀር ጀነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው

1. ብ/ጄነራል አታክልቲ በርሀ ገብረማርያም
2. ብ/ጄነራል ያይኔ ስዩም ገብረማርያም
3. ብ/ጄነራል አስራት ደኖይሮ አህመድ
4. ብ/ጄነራል ዘውዱ በላይ ማለፊያ
5. ብ/ጄነራል ሙሉ ግርማይ ገ/ህይወት
6. ብ/ጄነራል ፍሰሃ ኪ/ማርያም ወ/ሂወት
7. ብ/ጄነራል ኩምሳ ሻንቆ ደስታ
8. ብ/ጄነራል ዋኘው ኣማረ ደሳለኝ
9. ብ/ጄነራል ሹማ አብደታ ህካ
10. ብ/ጄነራል በላይ ስዩም አከለ
11. ብ/ጄነራል መሓመድ ተሰማ ገረመው
12. ብ/ጄነራል አብዱራህማን እስማኤል አሎ
13. ብ/ጄነራል መሰለ መሰረት ተገኝ
14. ብ/ጄነራል ክፍያለው አምዴ ተሰማ

የሌተናል ጄነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው
1. ሜጀር ጄነራል መሐሪ ዘውዴ ገ/ማሪያም
2. ሜጀር ጄነራል ሞላ ሐይለማርያም አለማየሁ
3. ሜጀር ጄነራል ሓሰን ኢብራሂም ሙሳ

የጄነራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው
1. ሌ/ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ይመር
2. ሌ/ጄኔራል አብረሃ ወ/ማርያም ገንዘቡ
3. ሌ/ጄኔራል አደም መሐመድ ሟህመድ
4. ሌ/ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለልቻ

 

በዚህ ዜና ዙሪያ የጋዜጠኛ መሳይ መኮንን አስተያየት:
በትላንትናው ዕለት ለ61 ወታደራዊ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ተሰጥቷል። ኢትዮጵያ ከአሜሪካ አንጻር ብዙ ጄነራሎች ያሉዋት ሀገር እየሆነች ነው። 1ነጥብ 5ሚሊየን ለሚሆነው የአሜሪካን ሰራዊት 231 ጄነራሎች ሲኖረው ከ200ሺህ ሰራዊት ያልበለጠ ያላት ኢትዮጵያ ከ400 በላይ ጄነራሎች እንዳሏት መረጃዎች ያሳያሉ። አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ ባለፉት 5 ዓመታት የተሰጡት ወታደራዊ ማዕረጎች፡ ከእሳቸው ሞት በፊት በነበሩት 21 ዓመታት ከተሰጡት በብዙ እጥፍ ይበልጣሉ።

ወታደራዊ ሳይንስ አካዳሚ ደጃፍ ሳይረግጡ፡ ይህ ነው የሚባል የዘመናዊ ውጊያ ልምድ ሳያካብቱ፡ ኮዳና ቀለብ በመቁጠር ሰራዊቱ ውስጥ የቆዩትን ሰብስቦ በማዕረግ ማንበሽበሽ የትግራይ ህዝብ ነጻአውጪ ግንባር የስልጣን ማረጋጊያ ስትራቴጂ የሆነ ይመስላል። እንደሰማነው በመከላከያ ውስጥ ጋዜጣና ደብዳቤ በማመላለስ ለዓመታት የቆየ አንድ ወታደራዊ መኮንንም የብርጋዴየር ጄነራልነት ማዕረግ ተሰጥቶታል። በዚህ ከቀጠልን ከቡና፡ ቆዳና ሌጦ በተጨማሪ ጄነራሎችን ኤክስፖርት የማድረግ አቅም ላይ መድረሳችን የማይቀር ነው።

 

ጥብቅ ምስጢር ስለመከላከያው Must Watch: Hidden Truth about Ethiopian National Defense Force 

4 Comments

4 Comments

 1. Tesfa

  February 4, 2018 at 7:46 am

  ወያኔ በየጊዜው በህዝባችን ላይ የሚፈጽማቸው በደሎች ክራራይሶ ያሰኛሉ። ጠ/ሚሩ የትግራይ የበላይነት የለም እያሉ በመድረክ የሚያላዝኑት ከፍራቻ እንጂ እውነትን ተመርኩዘው አይደለም። እንደ አሸን የበዛው የወያኔ ወታደራዊ የጄኔራሎች ክምችት ለመከራ ጊዜ እንደ ተሰበሰበ እህል ነቀዝ የሚበላውና የበላው ማዕረግ ነው። መሾም ሃገርን ወገንን ለማገልገል እስካልሆነ ድረስ ዋጋ የለውም። ለምዝበራና ለትግራይ ህዝብ የበላይነት ኮኮብ ቢጭኑ ትርፋቸው ጊዜአዊና ሁለገብነት የሌለው በህዝብ ያልተደገፈ በጠበንጃ አፈሙዝ የሚመራ የወስላቶች ስልጣን ነው። ህዝባችን ሲከፋው፤ ሲበደል፤ በግጥም፤ በቅኔ፤ በተቀበል (የዓለም አጫዋቾች)በየመጠጥ ቤቱና በየድግሱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይተነፍሳል። እጠቅሳለሁ።
  ክሽን ያለ ደሮ መብላት ካማራቹሁ
  በርበሬ ጨው ቅቤ ቅመም ካመጣቹሁ
  ለመገነጣጠል መለስ አለላቹሁ።
  አድዋ ያቺ የጥቁር ህዝቦች ተስፋ እንዴት እነዚህን ጠባብ ብሄርተኞች አምጣ እንደወለደች ማመን ይሳነኛል። እንዴት ከ100 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በሚኖርባት ሃገር ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ኦሮሞዎች ወያኔ ከሱማሊያ ክልል ጋር ተመሳጥሮ በከፈተው ዘመቻ ከቀያቸው ተፈናቅለው በረሃብና በብርድ ሜዳ ላይ ወድቀው ወያኔ የራሱን ወታደራዊ መዋቅር ማጠናከሩ እኔ ከሞትኩ ስርዶ አይብቀል እያለን እንደሆነ መገመት አያዳግትም። ከጎንደር በወያኔ ሴራ ተባረሩ የተባሉት የትግራይን ተወላጆች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው ወደ መቀሌ ያጓጓዛቸው። ወያኔ የተጣላው ከራሱም ጋር ነው። የሚገድለውና እሳት የሚለቅበት አንድ በሚያረገን ነገር ላይ ነው። አሁን ለትግራይ ህዝብ የሚለፈው የፓለቲካ አሻጥር ሆን ተብሎ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ ለማድረግ ነው። የሰሜኑን ክፍል የጦርነት ቀጠና ያደረገው ወያኔ ሻብያን እመክታለሁ በማለት የምድርና የዓየር ሃይልን ወደ ትግራይ ከሞላ ጎደል ማዛወሩ የታወቀ ነው። ወያኔ ግን ልብ የለውም። ሰው በጦር መሳሪያው አይድንም። የሰው ልጅና የመሪዎች በመከራ ጊዜ ሽፋናቸው ህዝብ ነው። የወታደር ጋጋታ፤ የጀኔራሎች የኮከብ ክምር ባዶ የሂሳብ ስሌት ነው። ህዝብ ደጀን ያልሆነው ሰራዊት በመከራ ጊዜ አይቆምም። በወልድያ በአልሞ ተኳሾች የተገደሉት ደም ይጮሃል። በኦሮሚያ የእናቶች እንባ ዛሬም አልደረቀም። ግፍና መከራ ለመጫን የወያኔ ወታደሮች የተካኑበት ሙያቸው ነው። አሁን ማን ይሙት አንድዓለም አንዳርጌ እድሜልክ የሚያስፈርድበት ወንጀል አለው? ወር የሚያሳስር ተግባር አለፈጸመም። ይሁን እንጂ እንነጋገር በማለት መድረክ ወይኔ ፈጥሮ የልባቸውን ሲነግራቸው የጠለፋ ትብታባቸውን በማብዛት ግዞት አወረድት። ሽብርተኛው፤ ጸረ አንድነትና ህዝብ፤ ዘረኛው፤ ለራሱ ሲቆርስ የማያሳንሰው ወያኔ ነው። ይህ የወታደራዊ የማዕረግ ስጦታም የወያኔን የማይቀር ሞት እንዳይፋጠን ያግዝ እንድሆነ እንጂ አያግደውም።

  • FARAW

   February 6, 2018 at 6:41 am

   Tesfa ,

   YOU MUST BE HIGH ON DRUG . YOUR COMMENT HAS NO SENSE .TALKING ALL THINGS AT ONCE MAKES YOUR MESSAGE A GARBAGE .

 2. NANA

  February 5, 2018 at 2:57 am

  HIGHLY EXPERIANCED , BATTLE HARDENED ,EFFECTIVE FIGHTING MACHINE ON EARTH .

  SOURCE OF PRIDE FOR FRIENDS
  FIRE AND FURY FOR ENEMIES

  VIVA !

 3. Mazegaja Mazegaja

  February 7, 2018 at 10:37 am

  One day we will have a government composed of leaders who think beyond their pockets and the day’s pleasure, leaders who think of the next generation because they understand that the current problems are results of previous decisions and actions, who understand that it is almost impossible to quench legitimate questions of the people forever, who want to build bridges between people not destroy them, who are brave enough to embrace the temporary pain of giving their dearest for the sake of benefiting many, who greatly value clean conscious, who are ready to say I am sorry I was wrong, who are determined to tell children (coming generation) only the “truth”, who understand they will not last but their work will definitely impact others.

  We are Ethiopians! We had many ups and downs, lots of stories we are proud of and many other we aren’t like any other country in the world but we will stand together and come victorious through the current problems and the ones to come!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top