News Feature

በፍራንክፎርት የኢትዮጵያዊያን የነፃነትና እኩልነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኅይል መግለጫ

በፍራንክፎርት የኢትዮጵያዊያን የነፃነትና እኩልነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኅይል (Frankfurt Task Force Freiheit und Gerechtigkeit für Äthiopien) በወለደያ የጥምቀት እለት የወያኔ ወታደሮች በሰላማዊ የጥምቀት በዓል ኣክባሪ ፅላት የተሸከሙ የሃይማኖት ኣባቶች፤ እናቶቻችን፤ ኣባቶቻችን፤ እህቶቻችን፤ወንድሞቻችን በኣጠቃላይ በምዕመናኑ ላይ ካለምንም ምክንያት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተደረገውን ጭፍጨፋ በጥብቅ እያወገዝን ይህንንም ተከትሎ በቆቦ፤ ሮቢት፤ መርሳ ብሎም በኣጠቃላይ በኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ኣሰቃቂ ፀረ ሕዝባዊ ጭፍጨፋን

ኣጥብቀን እያወገዝን፤ ይህንንም ኣረመኔያዊ ጭፍጨፋ የጀርመን ነዋሪ ዜጎችም እንዲያውቁት ለተለያዩ የመገናኛ ጣቢያዎች እንዲያውቁትና እንዲያሳውቁም በኣባሪነት የላክነውን ፅሑፍ ያሳወቅን መሆናችንን እየገለፅን ውድ የቤተሰባቸውን ኣካል ለኣጡ የተሰማንን ሐዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸው፤ ለዘመዶችና ጓዳኞቻቸው መፅናናት እየተመኘን ኣሁን በዚህ ሰዓት በየእስር ቤቱ ኢሰበዓዊ በሆነ መንገድ በመንገላታት፤ በመሰቃየት ወዘተ ከምትገኙ የኣገር ሽማግሌዎች፤ ወጣቶችና ኣባወራዎች የትግል ኣጋርነታችንን እንገልፃለን።

ነፃነት፤ እኩልነት፤ ሕጋዊነት፤የሰፈነባትን ዲሞክራሲዊት ኢትዮጵያን በትግላችን እናዋቅራለን !!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

4 Comments

4 Comments

 1. ታዲዎስ በላይነህ

  February 4, 2018 at 12:30 am

  አንዳንድ የዋህ አገር ወዳዶች ብዙ ሰው በመሞቱ ብቻ የወያኔ ዕድሜ የተቃረበ ይመስላቸዋል፡፡ አዎን ወያኔ ለሕዝብ እምነት የመገዛት ሥነምግባር ያለው አካል ቢሆን ኖሮ በዲሞክራሲ ባደጉ አገሮች እንደሚፈጸመው ባለሥልጣናቱ በራሳቸው ፈቃድ በለቀቁ ነበር። ነገር ግን ወያኔ መንግሥት ሳይሆን ወሮበላ ስለሆነ ለሺዎች ቀርቶ ለሚሊየኖች ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን ሞት ደንታ የለውም፤ ገና ሥልጣን ላይ ሳይወጣ ሦስት ሺ የሚሆን የትግራይን ሕዝብ በሐውዜን ገበያ ላይ አስጨርሶ ኣወክለዋለሁ የሚለውን የትግራይ ሕዝብ አታሎ ወደሥልጣን መሮጡ የአደባባይ ምስጢር ነው። ለሆዱ ያደረውና ጠባብ ብሔርተኛው የትግራይ ኤሊት እንጅ ሰፊው የትግራይ ሕዝብ ሐቁን ስለሚያውቀው ቆቅ ሆኖ ነው የኃይል ሚዛን እየጠበቀ ያለው። ወያኔ ዛሬ የቆሰለ ጅብ ነው፤ መጨረስ ያቀተን የዋህ በመሆናችን ብቻ ነው።
  ስለሆነም የአገሬ ወጣት ከእንግዲህ ሰላማዊ ሰልፍ እየወጣህ ለዚህ አውሬ አንገትህን አትስጥ። ወያኔ እንደሆነ የናት ያባትህን አገር ብቻ ሳይሆን መውጫ መግቢያህን እየተቆጣጠረ አንተን እንደዶሮ አሥሮ ወደ ቅርጫት እስከሚወረውርህ ድረስ ከእንሰሳ ባነሰ ሁኔታ ቀፍድዶ ይዞህ ሲሻው ባሪያው አድርጎ ሲያሻው በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ገድሎ እድሜውን ከማስረዘም በስተቀር ለማንም ሰው የማይመለስ ነው። ብትሰነብት እንኳ ዘር እንዳይኖርህ እያደረገ ነው፤ ስለሆነም ኖረህም ከመቃብር በላይ ስለሆነ እንድትሰነብት የሚያደርግህ፤ ባዶ እጅህን ከምትሞት የምትችል ወኔ ያለህ ቤትህን ዱር አድርገህ ይህን አውሬ ከሚያድኑት ጋር ተባበር፤ ካልቻልክ ድምጽህን አጥፍተህ በምትችለው መንገድ እርዳ፤ የጀግና ሞት ሙት እንጂ በአደባባይ እንደበግ አትታረድ።

 2. Dagne

  February 4, 2018 at 5:27 am

  እንደዚህ የሚባል ድርጅት ፍራንክፈርት ውስጥ አለ እንዴ? ካለ ከዚህ በፊት ምን ሰርቷል?

 3. Sintun tazebin

  February 4, 2018 at 12:53 pm

  Dagne kkkkkkk

  Gimo 7 new éko ,,simun eyeqeyayere be Hizb Genzeb yekelidal

  G7 yemebal direjit ,,yemote ahiya new !

 4. NANA

  February 5, 2018 at 8:06 am

  kikikikiki

  G7 acting as a witch . This desperate shabian slave pretends as a journalist , union , media , civil society …..

  PEOPLE ARE LAUGHING IN THEIR INHERENT BRAIN FAILURE .

  SHABIAN GOONS , ACT LIKE A MAN IF U CAN !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top