ለትግሉ ወገናዊ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የደሚሂትን የጋራ መግለጫ በሚመለከት ከነአምን ዘለቀ የተሰጠ ማብራሪያ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |


1. ማናቸው ድርጅት አርበኞች ግንቦት 7 ጨምሮ ከአባላቱም ፣ከደጋፊዎቹም። ከህዝብም የሚመጣ ትችት መቀበል የግድ ነው (ግዴታው ነው)። ፍጹም ሰው እንደሌለ ሁሉ ፍጹም ድርጅት ሊኖር አይችልም። የሚሰሩ ደግሞ ይሳሳታሉ። ስህተቶችን በአግባቡና ገንቢ በሆነ መልኩ በልዩ ልዩ መስመሮች ሲገለጽ አንድን ድርጅት የሚማርና ስህተቶቹንም እየረመ የሚሄድ ያደርገዋል። በዚህ አመለካከት ያለውን ለትግሉ ወገናዊ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ይስማማሉ ብዬ እገምታለሁ።

2. ሰሞኑን የወጣውና ብዙ ውዝግብ ያስነሳው የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የደሚሂት የጋራ መገለጫ በጣም አስፈላጊና ወቅታዊ እንደ ሆነ ምንም የሚያጠያይቅ አይደለም። ስርዓትን መለወጥ ብቻ ሣይሆን የተረጋጋ ሐገር ለመፍጠር እንደሚንቀሣቀስ የፖለቲካ ሃይል በበደል ብዛት የተቆጡ ኢትዮጵያውያን ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ዉስጥ እንዳይገቡ ማሣሠቡ ተገቢ ይሆናል።በመግለጫው እንደተቀሠው ሠማን እንጂ አረጋገጥን ተብሎ አልተጻፈም፤ በሐገሪቱ ክልሎች የሕወሐት አባላትና የሕወሐት መልዕክተኞች መኖራቸውንም በመግለጫው በግልፅ ያመለክታል፤ በአጠቃላይ የመግለጫው ይዘት ትናንት ከተከሠተው ይልቅ ሥለነገው የሚጨነቅ መሆኑንም ማስታወሡ ተገቢ ነው፡፡ የመግለጫው ዓላማ ይህ ቢሆንም በአንድ በተሻለና እወነታውን በተጨባጭ ከማሳየት ይልቅ አሻሚ በሆነ ቋንቋ በተጻፈ አንድ አንቀጽ ( በአንዱ ዛፍ) .ጫካው በመሸፈኑ ውዥንብር ተከስቷል፡፡

3. በዋናው ጭብጥና መንፈስ (በጫካው) ወስጥ የተካተተው መልክት ሕዛብዊ ወያኔ አርነት ትግራይ (ህወአት) በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ኢትዮጵያን ካልገዛሁ ኢትዮጵያን አፈርሳታላሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ፣ ይህንንም ተግባራዊ ለማድርግ የትኛውንም ስልት ከመጠቀም ወደሁዋላ እንደማይል፣ ከነዚህም መሰሪ ስልቶቹ ወስጥ በዋነኘት የትግራይን ህዝብ ምሽግ ለማድረግ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ማናከስና ወደ የማይታረቅ ቅራኔ ወስዶ የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያ ህዝብ መነጠል ብሎም መገነጠል በመሆኑ

ሀ) “የትግራይ ህዝብና ህወአት አንድና የማይነጣጠሉ ናቸው” የሚለውን የ 26 አመታት የወያኔ ትረካና ፕሮፕጋናዳ መናድ፣ ማፍረስ ወሳኝ የትግሉ አካል መሆኑን ።

ለ) የትግራይ ህዝብ ፣ የትግራይ ምሁራን፡ የትግራይ ድርጅቶች የዚህ የወያኔ መሰሪ ተግባር ሰለባ እንዳይሆኑ እንዲያውም ትግሉን ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን እንዲያቀጣጥሉ ጥሪ ማቅረቡ።

በትክክሉ፡ በጥልቀትና በረጅሙ በማሰብም የኢትዮጵያ ሀገራችን የወደፊት ሰላም ፣ ሀገራዊ አንድነት፡ የህዝቦች አብሮ መኖር መጻኢ እድል ለሚያስስበው ማናቸውም ቅን (ቅንን የሚለው ይሰመርልኝ) ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህ መልክት ወቅታዊም አንገብጋቢም መሆኑን ሊያጡት አይችሉም ።

4. የወያኔ ፋሽስቶች የትግራይን ህዝብ ምሽግ አድርጎ የአምባገናዊ የዘረፋና የዘረኘነት ስረአቱን ለማሰቀጠል የሚያደርገውን የአልሞት ባይ ተጋዳይ እንቅሳቃሴ ለማምከን የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረውን ሁለ ገብ ትግሎችና ከወያኔ ፋሽስቶች ጋር የሚያድርገውን ትንንቅና ፍልሚያም በሚያፋፋምበት በአሁኑ ሰአት በሁሉም አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦችና ታጋዮች ሁሉ (በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ የኣርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮችን ጨምሮ) የህወአትን ሰላዮችና ገዳዮች ከስርአቱ ጋር ምንም ቁርኘት ከሌላቸው የትግራይ ተወላጆች ነጥሎ መመታት አስፈላጊና ፡ ህዝቡም በትግሉ ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ነው በመግለጫው የተገለጸው።

5. ሌላው የመገለጫው ጫካ ዋና መንፈስ የአግ7 ንቅናቄ በወያኔ ፋሽቶች የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ተንኮልና መሰሪነት ሊመጣ የሚችለውን የእርስ በእርስ ጦርነት ከፍተኛ ስጋት እንዳለው ነው የተገለጸው። በዚህ ፋሽታዊው ሕወአት በሸረበው ወጥመድ ውስጥ ታጋዩ ማህበረሰብ እንዳይገባ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ነው ያሰመረበት፡ እነዚህ ዋና ዋና መልክቶች መግለጽ ሃላፊነት ከሚሠማው የፖሊቲካ ድርጅት የሚጠበቁ ተግባራት ናቹው፡፡

6. በእርግጥ በዚሁ ብዙ አነጋጋሪ በሆነው መግለጫ ላይ የተጻፈው አንድ አንቀጽ (አንድ ዣፍ) የሚሰጠው ትርጉም ከላይ በስተመጨረሻ #5 ከተጻፈው የተለየና ብዙዎች በሌላ መልኩ እንዲረዱት ማድረጉ ለተነሳው ውዝግብ መንሴኤ ሆናል።

7. በብዙሃን ቅን ኢትዮጵያውያን (አባላት፡ ደጋፊና፡ ለትግሉ ቀናዊ ከሆኑ) ኢትዮጵያውያን ወንድሞችና እህቶች አወዛጋቢዎችን አንቀጽ በሚመለከት የተነሱ ጥያቄዎች፣ ገንቢ አስተያየቶችና ፡ እርምት እንዲደረግና ንቅናቄው መልስ እንዲሰጥበት ከሚያስስቡ መልክቶች ሁሉ እንደተጠበቁ ሆነው ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ከወያኔ ይልቅ ትግላቸውን ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ለማድረገ የወስኑ ክፍሎችን በተመለከተ በአጭሩ ለማለት የምፈልገው በእርግጥ የሕዝቡ ሥቃይ ይሰማችኃልን ? በእርግጥ ከተሰማችሁ ሕዝብን ከሚያሠቃየውና ከሚጨፈጭፈው ሕወሐት ይልቅ ሕወሐትን የሚታገለው አርበኞች ግንቦት 7 እንዴት ዋነኛ ጠላታችሁ ሊሆን ቻለ? .መልሡን በቅንነት ለሚዳግፏቸው ወገኖቻችን እንደሚሰጡ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

8. የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ምንም ሳይደርስባቸው ገና ከጅምሩ በጠላትነት ፈርጀውት ከወያኔ ይልቅ ዱላቸውን በሙሉ ጊዜና ህይል ሳይቆጥቡ ለዚህ የጎንዮሽ ልፊያና ጠለፋ የሰጡ፣ ነገር ግን ለዚህ ውስብስብና ብዙ አቀበትና ቁልቁለት ለበዛበት ትግል ምንም ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የማያደርጉ ግለሰቦችና ቡድኖች ማህበራዊ ሚዲያውን አጨናንቀውት እያየን ነው፡

9. በአንጻሩ ይህን ትግል ዳር ለማድረስ ምን ያህል መስዋእትነት እየተከፈለና በተግባርም ብዙ ብዙ ተግባራዊ ስራዎች በሀገር ውስጥም በውጭም እየተሰሩ እንደሆነ የሚያውቁ፣ የሚረዱ፣ ለትግሉም ቀናኢ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የዚህ መሰሪ አካሄድ ሰለባ ላለመሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና ፡ በስሜት ሳይሆን በአምክንዮና ለትግሉ የሚጠቅመውን፡ የወያኔን ፋሽታዊ አገዛዝን የሚያስጨንቀውና የሚያዳክመውን፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ለድል የሚያደርሱ፣ የሚያበቁ ፣ ለሀገራችን ኢትጵዮጵያ ትንሳኤን የሚያፋጥኑ ተግባራት ላይ ማተኮር ይገባል። በሰከነ አእምሮ ማሰብ የሚያስፍልግበት ስሱ ወቅት ስለሆነ፡ ቆም ብለን ፡ ትንፋሽ ወስደን በረጅሙና ከፊታችን በተደቀነው ተግባሪዊ ትግል ላይ አይናችንን እንዳናነሳ ማድረግ ያስፈልጋል። ጥንቃቄ እንዳርግ በሚል በትህትና ለማሳሰብ እወዳለሁ።

ነአምን ዘለቀ

11 Responses to ለትግሉ ወገናዊ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የደሚሂትን የጋራ መግለጫ በሚመለከት ከነአምን ዘለቀ የተሰጠ ማብራሪያ

 1. Who was the one who said “when I hear Ethiopia and Ethiopiawinet, it suffocates me” ?

  Asmare
  February 3, 2018 at 11:28 pm
  Reply

 2. Neamin shabyaw , ante ayn awta !!

  achberbare werada ! be Hizb sim menegedu yebqa !!

  antem be Enatih shabya,,, be Abatih banda silehonk –

  ye Gim 7 ashker ayasfeligenim !!

  8 amet yebezebezachutin Genzebachnin melisu !!!!

  Sintun tazebin
  February 4, 2018 at 12:44 am
  Reply

 3. አቶ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር መሆኖትን ባውቅም ይህንን ማብራሪ የሰጡት መግለጫውን ያወጡትን ሁለቱን ድርጅቶች ወክለው ይሁን እርግጠኛ ባልሆንም በማብራሪያዎ በተራ ቁጥር 1 የጠቀሱትን ሙሉ በሙሉ እደግፋለሁ።
  ያንን እንዳነበብኩ የጠበኩት በግልጽ ቋንቋ በመግለጫው የተቀመጠውና አቧራ ያስነሳውን ጽንሰ ሀሳብ ብዙሃኑ አንባቢ በአግባቡ እንዳልተረዳው ወይንም አሻሚ ቃላት የፈጠረው አይነት ችግር ለማድረግ መሞከሩ አግባብ አይደለም። ሌላው “በበደል ብዛት የተቆጡ ኢትዮጵያውያን ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ዉስጥ እንዳይገቡ ማሣሠቡ ተገቢ ይሆናል” የሚለውም እንዳይሳሳቱ ማሳሰቢያ ሳይሆን ከሶስት ዓመት ወዲህ የበቀል እርምጃ በጅምላ እንደሚወሰድ የሚገልጽ ነው። በተጨማሪ “በመግለጫው እንደተቀሠው ሠማን እንጂ አረጋገጥን ተብሎ አልተጻፈም፤” ያሉት ይህም ቢሆን ጅ7ንን የሚያክል ድርጅት ባልተረጋገጥ በስሚ ስሚ ዝም ብሎ ድርጅታዊ መግለጫ የሚያወጣ ከሆነ ተአማንነትን አያሳጣውም ወይ? ሕባችን 26 ዓመት ሙሉ ዝም ብሎ ሞቷል አሁን ግን ጥሎ እየወደቀ ነጻነቱን ማወጅ ይፈልጋል ካልተሳሳትኩ ይህ የናነተም ተቀዳሚ ተግባርስችሁ ነው። ስለሆነም ነው ዱር የገባችሁ ስለሆነም ዙሪያ ጥምጥም ከመጓዝ ለተከሰተው ስህተት ይቅርታ መጠየቅ ብልህነት ይመስለኛል።

  ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር

  zegeyedelu
  February 4, 2018 at 8:13 am
  Reply

 4. Sintun, Ante Yewisha lij, abat enat yeleleg,diha adeg, Neamin yet tawekwaleh. Yeneamin Enat yene zemed nech, Amhara nat, keyet abak amiteh new endezih yemetesifew, wisha , chiqa, yesew ensesa.

  Hailu
  February 4, 2018 at 9:30 am
  Reply

 5. N. Zeleke,

  Do you have a mother at all? The woman who brought you to this world and made your father so happy and successful deserves mention and even some words of praise.

  In all your writings and speeches about yourself and your father, your mother is missing. Not even a single word. If you do not want to talk about it because of some kind of childhood trauma or you do not know her or was brought up by your father alone, then better say it than leave people to speculate about this woman who was a mother to you and a partner to your father. Maybe it is time to let go the resentment – if there is any.

  In any case, my interest is to know if your mother (was) is Eritrean? You say your father had been working and living in Eritrea for a considerable length of time and having a family there makes sense. I hope I am not rude in mentioning this, but it happens.

  I am stunned that Sisay A. did not ask you about your mother. If there was prior talk not to raise it during the interview, it explains why it was avoided. However, that still leaves many to wonder why women do not make part of men’s talk particularly in our culture.

  As the saying goes “blood is thicker than water”. This quote has been played and replayed regarding M. Zenaw. As you very well know, he has acted on it big time the consequences reverberating to this day.

  So, Neamen, come clean on this issue before people start quoting “blood is thicker than water” on you too. Particularly, after you made your position clear on the Eritrean issue in the interview.

  My regrets if this issue is touchy to you, but it is our country that is on the line.

  Thanks.

  Abbaa Selama
  February 4, 2018 at 10:32 am
  Reply

  • N.zeleke may be born without a mother like Jesses Christ. In that case he doesn’t need to mention his mam. If he was not born without a mother as earthly person he has the right to be a chauvinist. As a chauvinist he could see woman as a second class and born to make baby as a machine. Remember most Ethiopian old guards took the oath of the feudal lord. In the feudal Ethiopia we know the position of women in general. It isn’t a big deal for this “freedom” fighter to forget mentioning his mam if has one.

   tarik miskeru
   February 4, 2018 at 11:16 pm
   Reply

 6. ጥርስ የሌለው የንግድ ድርጅት ግንቦት 0 ሀገር ቤትውስጥ ወያኔን ከምር የሚታገሉ ሰዎችን ማሰርያ ሽፋን ከመስጠት በቀር ከተቋቋመ ጀምሮ ለፀረወያኔው ትግል ምንም ያበረከተው ነገር የለም። በአዲሱ መግለጫው ደግሞ ለብዙ ግዜ ሲታማበት የነበረውን የፀረ-አማራነት አቋሙን ግልፅ አርጋል።

  እምቢ ለዳያስፖራ ድርጅቶች
  February 4, 2018 at 11:59 am
  Reply

 7. keditu wede mattu

  al
  February 4, 2018 at 12:15 pm
  Reply

 8. Aba selama,

  Ye neamin Enat Amhara nat,harer tewelda yadegech yeruk zemed negn. Yematawekewin atkebatir. Kebatari hula. Neamin yemiserawin 1/% mesratachew yemaitawek yenegde lijoch, azaba.

  Sintun, Ante Yewisha lij, abat enat yeleleg,diha adeg, Neamin yet tawekwaleh. Yeneamin Enat yene zemed nech, Amhara nat, keyet abak amiteh new endezih yemetesifew, wisha , chiqa, yesew ensesa

  Hailu
  February 4, 2018 at 5:16 pm
  Reply

 9. አቶ ነአምን ዘለቀ :-በመጀመሪያ ድርጅቴ የምትለው ግንቦት ፯ ከስምና ገንዘብ ከመሰብሰብ በስተቀር አስካሁን
  የፈየደው ነገር የለም ! ድርጅቱ የአማራ ልጆችን በህወሓት ለማስገደልና ለማሳሰር የሻአቢያ ተላላኪና ቦቆሎ መግዢያ
  ለማኝ ከመሆን ባለፈ ማለቴ ነው ! ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ይባላል ! ድርጅትህ ለዚህ ጊዜ ካልሆነ
  ለመቼ አንድሆን አንዳሰባችሁ አላውቅም ! በመጀመሪያ ግንቦት ፯ ከኢሳያስ አፈወርቅ ተአዛዝ ውጭ መነቃነቅ
  የማይችል መሆኑን አንንኩዋን አኛ የትግራይ ፋሽሺቶችም አንጠርጥረው ያውቃሉ ! አኔ በእጅጉ የማዝነው
  ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ብቻ ነው ! ምክንያቱም ከተደላደለ ህይወቱ ወጥቶ አስመራ የኢሳያስን እጅ እየነሳ
  እንዲቀመጥ የተፈረደበትን ማለቴ ነው ! ነአምን ፕሮፌሰሩን ገፋፍታችሁ እንዲሄድ ካደረጋችሁት ውስጥም
  አንተ ትእቢተኛውና የሻዕቢያ ባለሙዋሉ እንደሆንክ የሚታወቅ ነው ! በአንድ ወቅት የቪዥን ወይም
  የብዥታ ኢትዮጵያ ስብሰባ ላይ የሻእብያ ጠበቃ ሆነህ ለስብሰባ የመጣውን ሕዝብ በግድ ካልፈረማችሁ
  እያልክ ስትወርፍና ስትደነፋ ነበር ! አሁን ደግሞ ምን ዓይነት ማስተባበያ ማቅረብህ ነው ? ግንቦት ፯
  ምን እያደረገ እንደሆነ ገሃድ እየውጣ ነው ! የህወሓት ተላላክና አሽከር የሆነው ባንዳው በአድን ያወጣ
  ውን መግለጫ ግንቦቴውም ደገመው ! ድንቀም ተቃዋሚ ! እባክህን አፍህን ዝጋ ! ጆንያም ናቅፋ ድረስ
  ዘምቷል ! ኢትዮጵያ በልጆቹዋ ደምና አጥንት ተከብራ ትኖራለች !

  አደባይ
  February 4, 2018 at 6:18 pm
  Reply

 10. የትግራይ ብሄር በዝህ መንግስት ተጠቃሚም ደጋፊም ነው ሀቅ ብትመርም የግድ መዋጥ ነው እርሶ ሚያወሩት 10 ማይሞሉ ተቃዋሚዎች ይሆናል እነሱ እራሳቸው ብሄራቸውን ሲወቅሱም አይሰማም ስለዝህ ከግምት ውስጥ ማስገባትም አይችልም ቀሪው የኢትዮጵያዊ እስቲ 1 አሳዮን ከትግራይ ብሄር ሆኖ ብሄሬ ትክክል አትሰራም ይህን ስረአት መደገፍህ የሚል? የለም ሁሉም ለብሄሩ ተቆርቌሪ ነው ለዝህ ሌላውም መቆርቆር አለበት አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳልእና!!!!

  ራሄል
  February 5, 2018 at 4:00 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *