የዕለቱ ዜናዎች

ሙስሊምና ክርስቲያን ወጣቶች በመጣመር ታሪክ እንሰራለን አሉ

ቢቢኤን ጥር 27/2010
በህወሃት የሚመራውን አምባገነናዊ መንግስትን እንቃወማለን ያሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ ሌሊት በተለያዩ ቦታዎች የተቃውሞ መልክቶችን ሲለጥፉ ማደራቸው ታወቀ።ከሌሊቱ ዘጠኝሰዓት ጀመሮ መረጃዎችን ለቢቢኤን መላክ የጀመሩት እነዚህ ወጣቶች በአማራ ክልል፣በኦሮሚያ ክልልና በተለያዩ የአገሪቱ ቦታዎች ላይ ህወሃት መራሹ ቡድን የሚያደርገውን ግድያ፣እስር ማፈናቀልና ዝርፊያን ማዉገዛቸውን ለማስያየት ለጨቋኞች የላኩት መልእክት መሆኑን ለቢቢኤን ተናግረዋል።
ወረቀት መለጠፋችን በኦሮሚያ ዉስጥ የተጀመረውን የቄሮ ንቅናቄ፣ በአማራ ክልል ያለውን የፋኖዎች ትግል፣ ወደ አዲስ አበባ ለማስገባትና የአዲስ አበባ ወጣቶችን ለማነቃቃት የጀመርነው ስራ ነው ሲሉ ወጣቶቹ አብራርተዋል። «በአማራ ክልልና በኦሮምያ ክልል ዉስጥ ያሉ ወጣቶች የህይወት መስዋእትነት እየከፈሉ ባለበት ወቅት ወረቀት መለጠፉ እንዴት ይታያል?» በማለት ቢቢኤን ላቀረበላቸው ጥያቄ ወጣቶቹ ሲመልሱ «አዲስ አበባ የስርዓቱ የመጨረሻ እስትንፋስ ነው! በከተማዉ ዉስጥ በህወሃት የሚመራው ጨቋኝና አፋኝ ቡድን መደበኛ ፖሊስን፣ፌዴራል ፖሊስን፣የደህንነት መዋቅሩን፣አጋዚንና የመከላከያ ሰራዊት ባሰማራበት በዚህ ፈታኝ ወቅት ወቅት ያለውን ፍርሃት ሰብሮ ወጣቶችን ለማነቃቃትና ለወሳኝ ትግል ለማዘጋጀት የተጀመረ እርምጃ በመሆኑ ፋይዳዉ የላቀ ነው» ሲሉ ጥረታቸውን አስረድተዋል።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ መብራት መጥፋቱን ለቢቢኤን የገለጹት ወጣቶቹ «ህወሃት የሚባል አምባገነናዊ፣ዘርፊና አሸባሪ ቡድን በመዲናይቱ ዉስጥ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚተነፍሰውን አየር ለማሳጣት እንሰራለን» ሲሉ ቆርጠው መነሳታቸውን ያስረዳሉ። አክለውም «ህወሃት እኛን ለማስፈራራትና ለማታለል የሚያደርገውን የወታደራዊ ማዕርግ ሽግሽግ ረብ-የለሽ ነው፣ ቀኑን እነርሱ በስልጣን ሲሞሻሸሩ እኛ ደግሞ እነሆ ሌሊቱን በመሉ አዲስ አበባን በቅዋሜ ወረቀት ስንሞሽራት አድረናልና ትግሉ ይቀጥላል» ሲሉ አሳስበዋል።

ወጣቶቹ አገራዊና ወቅታዊ የሆኑ መልእክቶችን በተለያዩ የአዲስ አበባ ወረዳዎች ለጥፈዋል። የሰሞኑን የአማራ ክልል ግድያና ብሎም በኦሮሚያ ዉስጥ ያለውን የህወሃት ግድያ ለማዉገዝ «አዲስ አበባዎች ከተገደሉት የአማራና የኦሮሞ ወጣቶች ጎን እንቆማለን» ብለዋል። ወጣቶቹ የስርዓት ለዉጥን በፍጥነት እንደሚሹ ለማሳየት « ከወያኔ ነጻ መውጫ ቀን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው!» የሚል ቀጠሮ-አልባ የሆነ ለውጥን ፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል። አገሪቷ ዉስጥ ያለው የአንድ ዘር የበላይነት ለህልዉናችን አደጋ ነው የሚሉት የአዲስ አበባ ወጣቶች «የአንድ ብሔር የበላይነት ያለባትን አገር ማየት አንሻም» የሚል ምሬት የታከለበትን መልእክት ለጥፈዋል።


ህወሃት መራሹ መንግስት በሐይማኖት ጉዳዮች ዉስጥ ያደረገውን ጣልቃ ገብነትና ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ከስድስት አመታት በላይ እያደረጉት ያለውን ሰላማዊ ትግል ደጋፊ መሆናቸውን አጉልቶ ለማሳየት «ዉድ ኮሚቴዎቻችን ዛሬ በእስር ላይ ብትሆኑም ደማቅ ታሪካችሁ ዝንታለም ደምቆ ይኖራል፤የተፈቱትን ይዘን የታሰሩትን እስኪፈቱ ጥያቄዎቻን ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል፤በማሰር በመግደል ያለአግባብ ግብር በማስከፈል ንብረት በመዉረስ የሙስሊሙን ጥያቄ ማፈን አይቻልም፤ህዝበ ሙስሊሙን ትንኮሳ እንደማያደናቅፈው ሁላ ሽንገላም አያደናቅፈውም፤ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ለቀጣይ ትግል በአዲስ መንፈስ ተዘጋጅተናል» የሚሉ መልክቶች በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳኖች ላይ መለጥፈፋቸውን ቢቢኤን ከደረሰው የፎቶና የቪዲዮ መረጃ ለማረጋገጥ ችሏል።

ወጣቶቹ በዘርና በሐይምኖት የተገደቡ አልነበሩም።ለአገርና ለሐማኖት ሲባል የሚከፈል መስዋትነት ዋጋው የላቀ መሆኑን ለማመላከት መልእክታቸውን የለጠፉ ክርስቲያን ወጣቶች አባቶቼ ያወረሱኝን ሐይማኖትና ባንዲራ እጠብቃለሁ፣ለአገርና ለሐይማኖት መሞት ሰማእትነት ነው፣በእግዚያብሔር ሐይል ጎጠኖችን ድል እናደርጋለን ሲሉ ቁርጠኝነታቸውን አሳዉቀዋል።ህወሃት መራሹ መንግስት ጥምቀትን በመሰሉ አመት በዓላት ላይ የሚፈጽመውን ጥቃት በመቃወም ታቦት በእጣን እንጂ ባስለቃሽ ጭስ አይታጠንም የሚል መል እልትን ወጣቶቹ አስተላልፈዋል።

እነዚህ ወጣቶች በጥር 2/2010 ተመሳሳይ የሆኑ መልእክቶችን በተለያዩ የአዲስ አበባ ወረዳዎች ላይ መለጥፋቸውን ቢቢኤን መዘገቡ ይታወሳል። ለኢትዮጵያ ህዝብ መልእክት እንዳላቸው በመግለጽም ይህንን የተቃዉሞ መልእክት መለጠፋችን ላይቀሬው የለዉጥ ትግል ቆርጠን መነሳታችን ማመላከታችን ነዉና የመዲናዋን የትግል እርከን ለማሳደግ ህዝባችን ከጎናችን በመሆን ይተባበረን ብለዋል።

አዲስ አበባዎች የታሉ? ተብሎ ጥሪ ሲቀርብ ለጥሪ ‹ጆሮ ዳባ ልብሰ› ያልን አይደልንም።ሐይላችንን በአግባባቡ መጠቅም ይኖርብናል። አራት ኪሎ ቤተ-መንግስትን ህዝባዊ ለማድረግ በሚደረገው የመጨረሻ ፍልሚያ ላይ ወሳኝ ሚና እንዲኖረን እኛ አዲስ አበባዎች ተዘጋጅተናል ሲሉ ያስረዳሉ። እኛን የሚመልሰን የተሃድሶ ሽንገላ ሳይሆን የአሸባሪው ህወሃት መንግስት ተንኮታኩቶ መውደቅ ብቻ ነው። ይህንንም መልእክታችንን ለወገናችን አድርሱልን ብለዋል-ወጣቶቹ።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top