ነፃ አስተያየቶች

ከአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ ነአምን ዘለቀ ማብራሪያ የከነከኑኝ ነጥቦች | በያሬድ ጥበቡ

ሰሞኑን የአርበኞች ግንቦት 7 (አግ7) ድርጅታዊ መግለጫ ታላቅ አቧራ አስነስቶ መሰንበቱን ሁላችንም እናውቃለን ። በተለይ ራሳቸውን እንደ አማራ ብሄርተኛ የሚቆጥሩ ወገኖች የመረረ ተቃውሞ ሲያሰሙ ሰንብተዋል ። ይህም የድርጅቱ የአግ7 አመራር አባል የሆኑትን የአቶ ነዓምን ዘለቀን ተጨማሪ ማብራሪያ እስከማስገደድ ደርሷል።

በተጨማሪ ማብራሪያው ላይም አቶ ነዓምን ዘለቀ የሚከተለውን አስፍሯል ። “በአሁኑ ሰአት በሁሉም አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦችና ታጋዮች ሁሉ (በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ የኣርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮችን ጨምሮ) የህወሓትን ሰላዮችና ገዳዮች ከስርአቱ ጋር ምንም ቁርኘት ከሌላቸው የትግራይ ተወላጆች ነጥሎ መመታት አስፈላጊና ፡ ህዝቡም በትግሉ ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ነው በመግለጫው የተገለጸው” ይላል ። አንብቤም ጉዳዩ ከነከነኝ ። ለምን ማለት ደግ ነው።

በመጀመሪያ አርበኞች ግንቦት 7 ይህን መግለጫ ማውጣት የተገደደው በየማእዘኑ በሚነሱት የህዝብ ሰላማዊ ተቃውሞዎች የመንግስት ምላሽ ጥይት በመሆኑ፣ በዚህ ፍጅት የተናደዱ ወጣቶች በደመነፍስ “የወያኔ ተባባሪ ናቸው” በሚባሉ ላይ የሚወስዱት ግብታዊና አመፃዊ እርምጃ ነው አወዛጋቢ ሆኖ የተገኘው። መግለጫው ራሱ “ንብረታቸው የተቃጠለባቸው ሰዎች ከትግሬነታቸው ውጪ የተገኘባቸው በደል የለም” ብሎ እስካላስተባበለ ድረስ፣ የአቶ ነዓምን ተጨማሪ ጉዳዩን ይበልጥ ከማወሳሰብ ውጪ ለጥራቱ ሊረዳ አልቻለም።

አቶ ነዓምን እንደሚሉት “የህወሓትን ሰላዮችና ገዳዮች ከስርአቱ ጋር ምንም ቁርኘት ከሌላቸው የትግራይ ተወላጆች ነጥሎ መመታት አስፈላጊ” ከሆነ፣ ያልተደራጀና ግብታዊ የህዝብ ትግል እንዴት አድርጎ ከሥርአቱ ጋት ቁርኝት ያላቸውን ከሌላቸው መለየት እንደሚችል ወንፊቱን ማቅረብ ነበረባቸው ። ያንን ማድረግ አልፈቀዱም ወይም አልቻሉም፣ ደግሞም አይችሉምም። እንኳንስ እንዲህ ዓይነት የቃና ዘገሊላ በዓልን ለማክበር ወጥቶ ታቦት ያጀበ ወጣት በደረሰበት ግፈኛ ጭፍጨፋ ተናዶ በወሰደው የመልስ ምት የደረሰ የንብረት ውድመት ቀርቶ፣ የተደራጀ ትግል ባለበት ሁኔታ እንኳ ጠቅላላ አቅሙን በመከላከያና ደህንነተ ላይ የሚያውል መንግስትን በዚህን መሰል የትግል ስልት መግጠም ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ። የትዬለሌ የሆነ የድርጅት አቅም፣ ዲሲፕሊንና አመራር የነበረው ኢህአፓ እንኳ በከተሞች ጥንካሬ ካለው መንግስት ጋር ያደረገው የሞትና ሽረት ትግል ለሽንፈት የዳረገው ከመሆኑም ባሻገር ፣ ስንት ስህተቶችና መዝረክረኮች እንደነበሩት የምናውቀው ነው። በስንት ጦር የተከበበውን መንግስቱን ሳይሆን፣ የአርቆ አሳቢውን የዶክተር ፍቅሬ መርእድን ህይወት ነው በአጭር የቀጠፈው። ለዚህ ዘመን ወጣቶች ትምህርት ሊሆን የሚችለውም፣ እስከ አፍንጫው ከታጠቀ ሥርአት ጋር፣ የርሱ ጥንካሬ ባለባቸው ከተሞች፣ የሥርአቱ ደጋፊዎች ናቸው የሚባሉትን በጠራራ ፀሃይ መግደል ወይም ንብረታቸውን ማቃጠል፣ የሥርአቱን እድሜ የሚቀጥል እርምጃ ብቻ እንጂ ነው። ደርጉ ከቀዩ ሽብር በኋላ ለ15 ዓመታት ሊገዛ የቻለው፣ የከተማው ሽብር የፈጠረለትን አመፅ ተገን በማድረግ ነው። ስለሆነም እንኳንስ ሰሞኑን በሰሜን ወሎ ከተሞች ያየናቸው የወጣቶች የደመነብስና ስሜታዊ እርምጃዎች ቀርቶ ፣ ኢህአፓን በመሰሉ እንደ ብረት የጠነከረ ዲሲፕሊን የነበራቸው እንቅስቃሴዎች እንኳ ለወጣት አባሎቻቸው የሰጧቸው “የነፃ እርምጃ” መብቶች የጋዜጠኛ የሸዋልዑል መንግስቱን ዓይነት ዜጎች መረሸንን ነው ያስከተለው ። እዚያ የተጨማለቀና አሸማቃቂ ታሪክ ውስጥ ዳግም መንቦጫረቅ የለብንም። የተወሰኑት የግንቦት 7 መሪዎችም በዚያ ታሪክ ውስጥ ያለፉ ስለነበሩ፣ ያንን ልምዳቸውን ዘወር ብለው ማየትና መመርመር ይገባቸዋል። የግንቦት7 መሪዎች ከኢህአፓ አነሳስና ውድቀት ሊማሩ የሚችሉት ብዙ ትምህርት ያለ ይመስለኛል።

ከላይ በግልፅ እንዳስቀመጥኩት ከአቶ ነአምን ተጨማሪ መግለጫ ውስጥ ያልተስማማኝን ተችቻለሁ። የሰሞኑን የሰሜን ወሎ ወጣቶችን ተጋድሎ በተመለከተ፣ ንብረት አወደማችሁ ብዬ ላወግዛቸው ፈቃደኛ አይደለሁም። ወንድሙ፣ ጓደኛው በአላሚ ተኳሽ ከጎኑ ሲወድቅ የተናደደ ወጣት ሄዶ የወርቅ ቤት ቢዘርፍ ወይም ቢያቃጥል ስሜቱ ይገባኛል፣ ይረዳኛልም። የተከፈለውንም መስዋእትነት አከብራለሁ ። ሆኖም በዚህ መንገድ ነፃነት ይገኛል ብዬ ለማመን እድሜዬም፣ ልምዴም፣ እውቀቴም አይፈቅዱልኝም። አስተማማኝና ዘላቂ ለውጥ የሚገኘው ከተራዘመ ሰላማዊ ህዝባዊ ትግ ል ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ ትግል ሥርአቱን አወዛውዞ “ከጭንቅላቴ በስብሻለሁ” ባሰኘበት ወቅት፣ ኦሮሚያና አማራ ክልሎች ውስጥ ህዝባዊ ትግሎቹን የሚደግፉ ሃይሎች በተበራከቱበት ወቅት፣ የግንቦት7ና የአቶ ነዓምን “የህወሓትን ሰላዮችና ገዳዮች ከስርአቱ ጋር ምንም ቁርኘት ከሌላቸው የትግራይ ተወላጆች ነጥሎ መመታት አስፈላጊ” ነው አስተሳሰብና እርምጃ፣ ወያኔ ከገባበት ማጥ ወጥቶ የበለጠ እንዲጠናከር የሚረዳው ይሆናል የሚል ፍርሃት አለኝ ። ወቅቱ በጣም ስሱ በመሆኑ፣ በተለይ ከፖለቲካ መሪዎች የበከጠ ስሱነት የሚጠየቅበት ነው። በእንዲህ ያለ ወቅት አመፅን የመጠቀም መብት ላልተደራጀ ህዝብ መስጠት ብዙ ሊያስከፍል ሰለሚችል፣ ቢያንስ ከታሪካችን እንማር! የተራዘመ ሰላማዊ ህዝባዊ ትግል ውስጥ በአላሚ ተኳሽ አጋዚ መገደል አለ፣ በዚያው መጠን በደምፍላት የሚደረግ መልስ ይኖራል፣ ለዚህም ተጠያቂው አልሞ ተኳሹ ነው። ይህን ሃቅ ህዝቡም ይረዳል። ከዚህ በላይ ሄደን ግን በፖለቲካ አመራር ደረጃ “የህወሓትን ሰላዮችና ገዳዮች ከስርአቱ ጋር ምንም ቁርኘት ከሌላቸው የትግራይ ተወላጆች ነጥሎ መመታት አስፈላጊ” ነው ብለን አናውጅ ። ያ ፍፁም ስህተት ነው። የህወሓትን ሰላዮችና ገዳዮች የመፋረድ ጥያቄ የህዝብ ነፃ እርምጃ ሳይሆን፣ ትግሉ ድል ካደረገ በኋላ በመደበኛ ፍርድቤቶች የሚያዝ የፍትህ ጉዳይ ነው ።

ለትግሉ ወገናዊ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የደሚሂትን የጋራ መግለጫ በሚመለከት ከነአምን ዘለቀ የተሰጠ ማብራሪያ

21 Comments

21 Comments

 1. እበበ ጃርሶ

  February 4, 2018 at 10:47 pm

  ትክክል እጅግ የበሰለ ትንተና ከመሆንኑም በተጨማሪ የማይገባ ጉዳትን የሚያስቀር ብልህነት የተሞላበት የድል ምንገድ ነው እንዳንተ ያለ የፓሎቲካ ሊቅ ትውልድን ስለሚያድን በጣም እናመስግናለን ደግሞም የ1955 አ.ም ክምሮ የነበረውን የፖሎቲካ ታሪክ የአሁኑንም ድረስ ጭምር በመጽሃፍ ለትውልድ መማሪያ ይሆናልና ቃል ግባልን ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ።

 2. ዘረ-ያዕቖብ

  February 5, 2018 at 2:07 am

  ከያዴድ ጥበቡ ጎን በመሆን፣ ቀደም ሲል ያሰማነውን ድምፃችንን እነሆ በጥቅስ መልክ ከታች እንደሚታየው፣

  (“Das Leben kann nur rückwärts verstanden werden – es muss aber vorwärts gelebt werden ” Sören Kierkegaard
  ስለሆነም፣ የኋላው እና የፊቱ ታሪክንም አብጠርጥሮ እየተስተዋለ እንጂ እንዲያው ዝም ብሎ….. ብቻ ብዙም የሚያስኬድ አይመስለንም!)

 3. Ewunet

  February 5, 2018 at 3:45 am

  Yared Tibebu an active TPLF / ANDM member in the diaspora would like to give us strategies as to how we conduct our struggle to remove chronic and cancer Tigre gov from Ethiopia.

  Yared has put forward three important issues on his critics for Neamen Zelek.

  1. The public struggle has to be only peaceful and time consuming.

  Yared has got a gut to tell the people of Ethiopia to avoid any kinds violence irrespective of barbaric brutality they have had recieved from Tigre Woyanes.

  Because he make sure Tigres would remain on power if not challenged by arms so he would like to tell us the strategy that we have tried for a quarter of a century.

  As far as I know it is that bloody peaceful means of struggle that offers plenty of chances for Tigrians to loot our resources all the he way through and consolidate their power that had left the nation captivated.

  …..cont.

 4. Ewunet

  February 5, 2018 at 3:56 am

  2. Yared strongly opposed any action taken on criminals by the nation rather he suggested they should face trial later if the gov is willing to go. Because if we donot use different means of strategies and only rely on peaceful means of struggle that means it would be upto the Tigre gov to give up power willingly which is not feasible and the nature of the gov doesnt allow them to do it. So we have no other option but to challenge the regime with violence.

  ….cont

 5. Sintun tazebin

  February 5, 2018 at 4:44 am

  egna; siriz diliz yalebet sew ayashnim !!

  Neamin be Enatu Ertirawi new,,abatum ewiq banda !

  ye shabya qitregna new !

  ye siltan tim yasabedew Birhanu, Abatu, ye weyane serawit Addis Abeba segeba, dinkuwan tilew bere ardew ,, le weyane serawit Gibir yabelu sew nachew

  ye Addis Abeben Hizb teyqu !!

  Neamin teregaga !

 6. Ewunet

  February 5, 2018 at 6:11 am

  Yared never wants to see either Woyanes or Tigrians punished by the public. If that is so he knows what will happen to him and his coworkers.

  3. Yared also said that granting the the public the right to use violence to attack their enemy is wrong. In this sentence what he would like to say is that is AG7 directing the people of Wollo to cause harms to Woyanes and Tigres. Which is ridiculous and unfounded as always.

  Tegadaly Yared , I can assure you AG7 had nothing to do with recent incidents in Wollo. That is purely done by Wolloyes because of culminated grievances and injustice committed by Tigre Woyanes .

  So if you were genuine what you should have to say was:

  A. Tigre Woyanes to return back lands of Wollo which they took it by force such as Alemata Korem Kobo Raya and others.

  B. To tell Tigrians to condemn their gov and show solidarity with Wolloyes or If they can’t do that leave my country or face the consquences.

  Cont….

 7. Mesfin

  February 5, 2018 at 1:09 pm

  Your diatribe on EPRP is a non-ending nuisance. You were a member of the party, and you left it for a narrow nationalist organization, ANDM/TPLF. You were hand and glove when you destroyed the country and crowned the ethno-fascists. EPRP whom you loath was the only organization that fought back this organization. Now, how dare you talk about EPRP? What do you know about Fikre and Shawalul, that we don’t know? I really felt pity for your martyred brother, for having such a weakling sibling. Months back, I read from your scribbles that your mum shares the same Tsewa with the killer of her son…and you seem to be lauding it. Pathetic. You wrote that you are talking from experience? What experience Ato Tibebe? The art of destroying a country and switching sides (EPRP-ANDM/Woyanne and Now??? God knows where you belong now). One last word, most people will take it for wisdom if you stop talking and stop scribbling your nonsenses.

 8. ገብረየሱስ

  February 5, 2018 at 2:46 pm

  ያሬድ እንደ ወትሮ መልካም ብለሃል። የቀረው ጨምረን ትምክህተኞችና ጠባቦች ቦታ እናሳጣቸው።

 9. genet yilma

  February 5, 2018 at 3:50 pm

  ያሬድ ጥበቡ ትክክል ነው። ግንቦት 7 አርበኞች እና የሻቢያ ተላላኪው ነአምን ትክክል አይደሉም።

  • Chala alemu

   February 6, 2018 at 2:39 pm

   20 ዓመት ሙሉ የሻዕቢያ ተላላኪ የነበረው ወያኔ ዛሬ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኇላ አግ7 ን ተላላኪ ሲል ትንሽ ሀፍረት አይስማውም
   ዛሬስ ቢሆን የምዕራቡ ዓለምና የቻይና ተላላኪ ማነው? ማፈሪያ ሁሉ !!!

 10. zele

  February 5, 2018 at 4:19 pm

  I’ve never trusted this guy ‘Yared Tibebu’ before (i’ve been always suspicious of his cynicism) pretending as if he is on the opposition side, however, i’ve now confirmed that he is a classic t.p.l.f. agent.

  Ethiopians gave TPLF a chance for over 26 years, Tibebu is yet here to telling us that 26 years is just nothing but keep dying, looted, displace and get destroyed as a nation. it’s ok according to Tibebu. ‘Hodd SeiaQ DerO Mata’.

  Death to TPLF and its loyal servants.

 11. Demiss Genanaw

  February 5, 2018 at 5:38 pm

  Zim bel leba! Maneh degmo ante?

 12. ምናቡ

  February 5, 2018 at 9:40 pm

  ያሬድ ጥበቡ አሁንም ስለ ኢህአፓ ያነሳሉ????????የዛሬ 42 ዓመት ታሪክ ምን ይጠቅማል?????????? የአረቡ ማዕበል መሪዎቹን እንዳፈረሰ የቅርብ ጊዜውን ያስተውሉ።

 13. እምቢ የዳያስፖራ ፓለቲካል ድርጅቶች

  February 6, 2018 at 6:26 am

  ይሄን ፅሁፍ አንድ የወያኔ ታማኝ የሆኑ የብአዲን ባለስልጣን በያሬድ የብዕር ስም የፃፋት ነው የሚመስለው።

  • Mechal Degu

   February 9, 2018 at 8:35 am

   I agree, I thought Yared and Neamin have the same goal: to discredit the popular uprising against TPLF-EPRDF. Both Yared and neamin/Ginbot 7 ‘advise’ the Ethiopian people to put our hands down and wait until the Tigre-aremenie agazi finishes us. Both have no moral ground to tell the Ethiopian people what and how to struggle for our own freedom.
   Yared and Woyane are the same: they are scared of EPRP.

 14. እምቢ ለዳያስፖራ ፓለቲካል ድርጅቶች

  February 6, 2018 at 7:17 am

  ይሄን ፅሁፍ አንድ የወያኔ ታማኝ የሆኑ የብአዲን ባለስልጣን በያሬድ የብዕር ስም የፃፋት ነው የሚመስለው።

 15. Hailu

  February 6, 2018 at 8:47 am

  Sintun, Melse setichew neber bekedem leta, abat enat yeleleh,diha adeg, Neamin yet tawekwaleh. Yeneamin Enat yene zemed nech, Amhara nat, keyet abak amiteh new endezih yemetesifew, chiqa, yesew ensesa, Komata, yeset lij

 16. HIwot

  February 6, 2018 at 10:12 am

  Yared, these kids are fighting the monster you helped to create. In fact, I wish we had squads that could get rid of your good friends Addisu Legesse, Bereket, Alemnew and others. We know you still sleep with the enemy, as you used to do when you first joined the ideologically bankrupted organization i.e. Woyanne. Whom were you fighting at the time? Wasn’t it the poor soldiers that were defending Ethiopia from secessionist and narrow nationalist forces? Were not the wrongly labeled farmers-cum- soldiers “Ethiopianist” by ideology? Haven’t you sided with narrow nationalists that created the boogyman “Amhara” to destroy Ethiopia? By what moral standard would you leave EPRP and “joined” the organization that chased EPRP from Tigray (and killed many of your comrades), with its “Get out of my Tigray” mantra? Reading your article is disgusting. You are politically irrelevant and experientially schizoid. You have no credential to show, so why should we take your advice?

 17. Leyikun

  February 7, 2018 at 6:37 am

  ህይወት፣ ምናቡ፣ ዘለ፤ ትገርማላቹሁ፣
  ያሬድ ሓሳቡን ገልጸዋል፣ የማይስማማቹሁ እናንተ የምታምኑት እስቲ እንስማው critically። ኣላምነውም ምን ኣመጣው። በሓሳብ ተስማምተህ ለተግባራዊነቱ መስራት፣ እንቅፋት የሆነው ማጋለጥ። ስለ ኢህኣፖ ቢገልጽ እንዳይደገም ትምህርት ይሆናል፣ እናንተ ግን ተመሳሳይ እየሰራቹሁ ናቹሁ፡ ጥላቻ/ምቀኝነት፣ ራሳቹሁን ኣጽዱ ካልሆነ ከህወሓት/እህኣዴግ በምን ልለያቹሁ።

 18. bazin

  February 7, 2018 at 10:42 pm

  the irredeemable traitor called yared never miss an opportunity to show his loyalty to his master, woyane, and expectedly demonizing the EPRP with the usual diatribe and white lie. The existence of EPRP to yared and his likes is a constant reminder of their crimes. yared is awaiting trial for his treason against Ethiopia for his collaboration with woyane.

  • Mechal Degu

   February 9, 2018 at 8:42 am

   Right on!
   Yared is a woyane camouflaging as mihur tentagn. he is scared of EPRP because he knew what he and his traitors did to EPRP and to Ethiopia. By the way, what did he say when his EPDM was ordered by Meles to change its name to ANDM (Amhara for EPRDF)? How could EPDM which was created by traitors but from all ethnic groups represent Amhara and be called ANDM? All of the EPDM who changed to ANDM are woyanes puppets. Only those who joined ANDM after 1991 are better–like Gedu Andargachew, who was NOT in the bush fighting alongside Woyanes and Shabiya.

Leave a Reply

Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

Zehabesha - Latest Ethiopian News

Copyright © 2018 Zehabesha - Latest Ethiopian News Provider. All rights reserved.

To Top