“በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው፣ በሕዝባዊ አመጽ፤ ትግሉ ይጋም ይፋፋም” – ነአምን ዘለቀ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

ፋሽስታዊው የሕወአት አገዛዝ የቆመበትን ኢኮኖሚያዊ ምሰሶዎች ለማሽመድመድ አለም አቀፍ የሃዋላ ተአቅቦ ዘመቻ አካል እንሁን!!

ከፋሽስቱ የወያኔ አገዛዝ ጋር በሚደርገው ሁለገብ ትግል ስልቶች መካከል የኢኮኖሚያዊ ጦርነት (Economic Warfare) አንዱ ነው። ስርአቱ የቆመበትን ምሰሶ የማዳከም የኢኮኖሚያዊ ጦርነት ስልቶች እንዱ የሃዋላ ተአቅቦ ነው። የሃዋላ ተአቅቦ ለአጠቃላይ ትግሉ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግና ስርአቱን ለማዳከም ያለው ሚና ከፍተኛ ነው።


በፋሽስቱ የሕዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ የበላይነት ስር የሚገኘው አምባገነናዊ አገዛዝ በከባድ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኝ ከሶስት ወራት በፊት በስርአቱ ሾልኮ የወጣ የራሱ የብሄራዊ ጸጥታ ም/ቤት የውይይት ሰነድ ያረጋግጣል። ከዚህም በላይ በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ፣ እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎች በየጊዜው እንደወጡ ይታወቃል።
ፋሽታዊው የወያኔ አገዛዝ የገባበትን ሁለንተናዊ የፓለቲካና የኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ትተን በውጭ ምንዛሪ በኩል አገዛዙ የደረሰበት የቀውስ ደረጃ በሚመለከት በቅርቡ በኢሳት ፥ ኦሜን፣ ዋዜማ፣ ኣንዲሁም በልዩ ልዩ የሚዲያ አውታሮች የወጡ መረጃዎችን ስንመለከት የቀውሱን ጥልቀት ለመረዳት ይቻላል። ከእነዚህም መረጃዎች ውስጥ የሚከተሉትን ለናሙና እንይ፦

1. የቴሌ ፣ የንግድ መርከብ ድርጅት፣ የመብራት ሃይል፡ ለልዩ ልዩ ፕሮጄክቶች ከውጭ ባንኮች የተበደሩትን ገንዘብ ለመክፈል (Debt servicing) በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ መክፈል እንዳልቻሉ፣

2. የአገዛዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ ለሚገኙ ኢምባሲዎችና ቆንስላዎችን በጀት በገባበት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ መሸፈን አለመቻሉ፣

3. በአዲስ አበባ የአርማታ ብረት ዋጋ ሰማይ እየነካ መሆኑ፣ የዶላር ግዢ በጥቁር ገበያ 35 ብር መድረሱ፣ ብረት በ9 ወራት ውስጥ በእጥፍ መጨመሩ፣ በአዲስ አበባ ብቻ 26ሺህየሕንጻ ግንባታዎች ሊስተጓጎሉ እንደሚችሉ ከላይ በተጠቀሱት የሚዲያ አውታሮችና ሌሎችም ተዘግቦአል።

ስርአቱን እየናጡ ከሚገኙት የኢትዮጵያ ሕዝብ የእምቢተኝነትና የአመጽ ትግሎች ሳቢያ የህወአት ፋሽታዊ አገዛዝ ከባድ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኝ ሌሎችም መገለጫዎችና መረጃዎች ማቅረብ ይቻላል። ለዚህም ነው የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ዘመቻው ከተጀመረ በኋላ አገዛዙ ከፍጠኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባው። በቅርቡም ወደ ሀገር ውስጥ ግለሰቦች ይዘው የሚገቡትንና ይዘውም የሚወጡትን የውጭ ምንዛሪ ለመቆጣጠርና ለመገደብ አዲስ ህግም እስከማውጣት ድረስ የተገደደው።
ከላይ የቀረቡት መረጃዎች አለም አቀፍ የሀዋላ እቀባ ዘመቻው በስርአቱ ላይ ከፍተኛ ጫና እያመጣ መሆኑን ያረጋግጣሉ። የፋሽስቱ የህዝባዊ ወያኔ ስርአት አገዛዝ አንዱና ትልቁ ጭንቀት የገባበት የኢኮኖሚያዊ ቀውስና ከዚህ ጋር የተያያዘው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ቀውስ መሆናቸውን ሁሉም ኢትዮጵያዊ መገንዘብ ያለበት ጉዳይ ነው።

የወያኔ አገዛዝ ከውጭ በሃዋላ የሚያገኘው 4.5 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ የአፈና ስርአቱን ለማንሰራርት፡ ገዳዮቹን ፣ አፋኞቹን ለመክፈል ፡ ህዝብን የሚጨፈጭፍበት መሳሪያዎች ለመግዛት ጭምር የሚጠቀምበት በመሆኑ፡ የአገዛዙን የውጭ ምንዛሪ ምንጮች ማድረቅ የትግሉ ትልቅና ወሳኝ አካል መሆኑን መገንዘብ በጣም አስፈላጊና ወቅታዊ ነው ።

በኢትዮጵያዊያን አለም አቀፍ ግብረ ሃይል የተጀመረውን የሃዋላ ተአቅቦ ዘመቻ እንደግፍ፣ ለዘመድ አዝማድ ፣ ለጓደኞች፣ በማህበራዊ ግንኙነቶችና በሁልም መንገዶች የዘመቻውን አላማና ግብ በማሰራጨት ይህን ዘመቻ ለማጠናከር፣ ግቡንም እንዲመታ ሁላችንም መረባረብ ይገባናል።

8 Responses to “በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው፣ በሕዝባዊ አመጽ፤ ትግሉ ይጋም ይፋፋም” – ነአምን ዘለቀ

 1. አንተና ድርጅትህ በመጀመሪያ የአማራ ሕዝብ ጠላት መሆናችሁን ስታቆሙ ህወሃትን ልናስወግደው እንችላለን !
  አለበለዚያ ይሄ በየቦታው የማስመሰያ ድንፋታ የተለመደና ከአገር ወዳዱ የአማራ ሕዝብ ላይ ገንዘብ መሰብሰቢያ
  ስልት ነው ! ግንቦት O የሻዕብያ ቦቆሎ ሸማች እንጂ የትግራይ ፋሺሽቶችን የሚዋጋ ድርጅት አይደለም ::
  ያገሬ ሰው ምን ይላል መሰለህ ” ትልቅ ዱላ ባይመቱበትም ማስፈራሪያ ይሆናል” ይላል እንደ ግንቦት
  o አይነቱን ማለት ነው ! አስመራ ተቀምጦ ህወሃትን ማስፈራራት ! ሕዝቡ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ
  መስዋዕትነትን እየከፈለ እያለ ከጎኑ ያልተሰለፈ ድርጅትም ሆነ ነፃነት ፈላጊ ባይኖር ይመረጣል !!!

  አደባይ
  February 7, 2018 at 8:57 pm
  Reply

 2. We are preparing for coming election. We will beat TPLF/EPRDF.

  genet yilma
  February 8, 2018 at 12:07 am
  Reply

 3. Neamin ,,, minew biq bir abezah ?

  siltan aygegnim atilfa

  siltan Hizb lemeretew ,, be Hager lemetagel new

  yantena ye Birhanu ayn awtanet demo qit ata !!

  Sintun tazebin
  February 8, 2018 at 12:54 am
  Reply

 4. Does the boycott include your Eritrea or is it only for my beloved Ethiopia?

  Gedif
  February 8, 2018 at 4:28 am
  Reply

 5. ሁሉን አቀፍ ትግል a la ግንቦት 7
  ዘራፊዎች

  Asmare
  February 8, 2018 at 7:56 am
  Reply

 6. ነአምን ዘለቀ
  አባክህ ይህችን ወደድከትን ግጥም በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስተርጉመህ ለዴምህት አሰተላልፍልኝ። ግጥሟን የወሰድኳት ከኢትዮ ፓትሪዎትስ ነው።

  አርስቷ እመን እውነታውን ትላለች። ጀመርኩ!

  ሓጎስና ወልዳይ፣ ጉዑሽና ገብሩ
  ብርክቲና ግደይ፣ እሙሐይ ሳይቀሩ
  መሠቀል የጨበጡት፣ መነኩሴው መምሩ
  አፈር ገፍቶ አዳሪው፣ ዘብናይ ምሁሩ
  ትዕቢት የነፋቸው፣ ያበጡ የኮሩ
  የባንዳው ወያኔ፣ ስውር ግብር አበሩ
  እንደሆኑ እወቁ ፣ አትጠራጠሩ
  አጋር እንዲሆኑ፣ ለትግል አትጥሩ
  እነርሱን ማባባል፣ ማለት እሽሩሩ
  ትግሉን አኮላሽተው፣ ይልቅ እንዳታፍሩ
  ከነሸበጣቸው፣ ይሻላል ቢቀሩ።

  አማራው ሲደማ፣ ኦሮሞው ሲደማ
  ሃብትና ንብረቱን፣ ሲገፍፍ ሲቀማ
  በተዘረፈው ሃብት፣ ትግሬው እየለማ
  ቁንጣን ያስከረው፣ የበላ እንደ አሣማ
  ዜናው በዓለም ሲናኝ፣ ጆሮ እከሚያገማ
  ቅምጥሉ ትግሬ፣ እንዴት ሆኖ ይስማ

  ወሎ እየተረደ፣ እያነባ ሸዋ
  ጎርፍ ሆኖ ሲወርድ፣ የወላጅ እንባዋ
  ቀንበር በርትቶባት፣ ጎብጦ ትከሻዋ
  ሞልቶ እየፈሠሠ፣ ግፉ ከዋንጫዋ
  ትግሬ ትዘፍናለች፣ ከነሹሩባዋ።

  ሲጠራ የማይሰማ፣ ሲያብል የተኛውን
  ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ፣ ስናውቀው ስራውን
  27 ዓመት፣ ጆሮ ዳባ ያለውን
  የማይነጋ መስሎት ፣ የተኮፈሰውን
  ጠባቡን ጎጠኛ፣ የሠሜን ትግሬውን
  ትግሉን ተቀላቀል እያሉ ጥሪውን
  ጨዋታው ይቀየር፣ ቀይሩ ዜማውን
  አፈሙዙን አዙር ፣ ያዝና ቃታዉን
  ጠላት አታባብል፣ እመን እዉነታውን።

  ታዛቢው
  JanJanuary 27/2018

  ጳውሎስ
  February 8, 2018 at 11:41 am
  Reply

 7. አቶ ነአም ለመሆኑ እናንተ ያሻብያ ፍየል ጠባቂዎች የአቶ በአሉ ግርማን መፀሀፍ ኦሮማይን አንባችሃል። አንዱ የአቶ በአሉ ግርማ መልክእክት ለወታደራዊው መንግስት ፤ የጦር መኮንኖችህ ፣ ከጀነራል እስከ መአከለኛ መኮንኖች ሻብያ በላካቸው ሰላይ የትግሪ ሴቶች ተጠልፈዎል ነበር። ነጮቹ ሲተርቱ well ,well ,well ይላሉ። ታሪክ እራራሱን ደገመ አይደል እንዴ ? የወያኔው ሰላይ አለቃ አቶ ጌታቸው እረዳ ፤ የሚያምር ጋቢና ፣ ትልቅ ደረት እና ቀላ ያለ ቆዳ ያላቸውን ሞንጆሪኖዎችን ልኮ የግንቦት ባዶ ከፍተኛ ባለስልጣኖችን ፣ ፀሀፌዎችን ፣ አክትቪስቶችን አጥምዳል ። የዚህም ውጢት አንድ የግንቦት ባለስልጣን የአዲስ አበባን አማራ መጤ ብለው እስከመፈረጅ አድርሶአቸዎል። አቶ ነአም ድርጅቶህ ተሽናፊ ብቻ ሳይሆን የህዝብ ደህነት ድፓርትምነት እንደሌለው በቀላሉ ማወቅ ይቻላል ። ከዚህ በላይ በጣም የሚያሳዝ ነው የአማራ ወጣቶች በወያኔ ሰላይች በተጋለጠ የወታደራዊ ዘመቻችሁ ውስጥ ተካፍለው እንዲያልቁ ልትልካቸው ትፈልጋላችሁ።

  እምቢ ለዳያስፖራ ድርጅቶች
  February 8, 2018 at 3:12 pm
  Reply

 8. ይሄ ኤርትራ ያለው የትግራይ ተቃዋሚ ሚባለው አርማውን ልብ ብላችሁታል? ክክክክክክ ሌላውም አንድቀን ያሳየናል ብለን እናስባለን!!!!

  ራሄል
  February 9, 2018 at 3:02 am
  Reply

Leave a Reply to ራሄል Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *