ነፃ አስተያየቶች

የወያኔ ኢህአዴግ የእሳት አደጋ መከላከያው አቶ አብረሃም ያዬህ  ማነው?

ከዘገየ ድሉ

የፖለቲካ ተንታኝ አብርሃም ያየህ፤ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ ያላቸውን ሥጋትና ተስፋ ያንጸባርቃሉ። አማራጭ የሚሏቸውን የመፍትሔ ምክረ ሃሳቦች ያጋራሉ በሚል ውብ አረፍተ ነገር ታጅበው ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በተመለከተ ስለ ግለሰቡ የማውቀውን ማለት ስላለብኝ ይህችን አነስተኛ አስተያዬት ለመስጠት ፈለኩኝ። 

አቶ አብረሃም ያዬህን በአካል የማያዉቅ በተለይም እኔ በምኖርበት በጀርመን አገር በዚያን ወቅት ማለቴ ነው አዲስ የመጡ ግለሰቦች ካልሆኑ በቀር ያለ አይመስለኝም:: ምክንያቱም ግለሰቡ በደርግ ዘመን ጓዶቻቸዉን ከድተዉ ሚስጥር ይዘዉ የወጡ መስለዉ ብዙዎቻችንን የሸነገሉበት ወቅትና ታላቁ ሴራ በሚል በጻፉት አነስተኛ መጽሐፍ ምክንያት ከብዙሀኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድጋፍና እምነት የተቸራቸዉ ግለሰብ ስለነበሩ ነው። በጀርመን አገር የሚገኙ የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች በተለያዩ ወቅቶች ስለ ሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ እንዲያብራሩ ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ጋር በመጋበዝ „የፖለቲካ ተንታኝ“ አድርገናቸውም ነበር ::

ለእኚህ ግለሰብ በወቅቱ ሁሉም ባይሆን አብዛኞቻችን የዋህነት ባጠቃው ቅንነት  በመነሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ አምባሳደር የሚል የክብር ሹመት እስከመስጠት የደረስንበት ጊዜ ነበር:: ታዲያ እኚህ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላ ለአገሩና ለወገኑ ቀናዕ የሆነዉ የዋህ ኢትዮጵያዊ የቸራቸዉን እምነት ለማንና ለምን እየተጠቀሙ እንደሆነ ዘግይተንም ቢሆን ስናውቅ ከአራጃችን ጋር የዋልን እንሰሶች መሆናችንን የምናስታዉሰዉ በቁጭት ነዉ::

የጽሑፌን ርእስ የመረጥኩት ያለ ምክንያት አይደለም አቶ አብረሃም ያዬህ ግንቦት ሰባት 2005 ቅንጅት በምርጫ ማሸነፉን እንዳረጋገጡ ተደናግጠዉ ለትግራይ ህዝብና ለወያኔ ሰራዊት ከህዋሐት ጉን እንዲቆም ጥሪ ካቀረቡ በኋላ ወያኔ ህወሓት የንጹሀንን ደም እንደ ጎርፍ አፍሶ ነፍስ መዝራቱን ሲያረጋግጡ ከሚዲያ መሰወራቸዉ ይታወቃል:: ቀጥሎም የአቶ መለስ ዜናዊ ሞትን ተከትሎ በህወሀት ኢህአዴግ ዉስጥ የተፈጠረዉ ክፍፍልና  በሀገር ውስጥም ሆን በዉጭ እየተካሄደ የነበረው ትግል የወያኔ ኢህአዴግን መንግሥት ህልዉና ከጥያቄ ዉስጥ ያስገባ በመሆኑ ከተደበቁበት ጉድጓድ ብቅ በማለት የተለመደዉን የእሣት አደጋ መከላከያነታቸዉን የጀመሩበት ወቅት ነበር::

አቶ አብረሃም ያየህ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ከተደበቁበት ስርቻ ብቅ የሚሉት ወያኔ ሕወሓት ሲጠቃ እንጂ ህዝብ ሲጠቃ አለመሆኑን ማሰረጃ ካስፈለገ በ25.05.2013 ከአውራምባ ታይመስ አዘጋጅ ዳዊት ከበደ ጋር ያደረጉትን ቃለመጠይቅ  ማዳመጠና እና “ ከግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ እና “ከኤርትራ መንግሥትና ህዝብ ጋር የሚደረግ ግንኙነትና ትብብር ለምን ?  „ በሚል ርዕስ የጻፉትን ክፍል አንድና ሁለት በኢትዮጵያ ዛሬ ድህረ ገጽ ወጥቶ የነበረውን ማየቱ በቂ  ነዉ:: እኚህ ግለሰብ አስመራ ድረስ ተጉዘው ስለ ኤርትሪያ በተለይም ስለ አቶ ኢሳኢያስ አፈወርቂ የተናገሩት መረጃው በእጀ ላይ ይገኛል እንዲ ነበር ያሉት አቶ ኢሳኢያስ ያለ ምንም አጃቢ አስመራ ውስጥ መዘዋወር የሚችሉ የህዝብ ተቀባይነት ያላቸው መሪ አድርገው ያቀረቡና ብዙም ሳይቆዩ ግንቦት 7ን አስመራ ለምን ገባ ብለው ኮነኑ። ይህ አለ ምክንያት አልነበረም ጅ7 ከአስመራ ጋር ማበር ለህወሓት ሥልጣን አስጊ በመሆኑ ነው። በአሁኑም ቃለ ምልልስ ተባብረን ይህንን መንግሥት ለማርገብ የሚቻልበትን መንገድ ይፈጠር የሚል እንጂ የህዝቡ ህወሓት ከስልጣን ይውረድ ምላሽ ያግኝ አይደለም። ስጋታቸው ህወሓትን እንደት እንታደገው ነው።

አቶ አብረሃም ያየህ የወያኔ እህአዴግ  የእሳት አደጋ መከላከያ ለመሆናቸው ማረጋገጫው ከላይ የጠቀስኩት ሲሆን ወቅቶቹን በማገናዘብ አንባቢ ሊፈርድ ይችላል። የእርሳቸውን ቃል ልዋስና ለምን አሁን? በአንቀጽ 39 እና በፕላን የሚያስፈራሩንስ እስከ መቼ ነው?

እኔ የኑሮዬ ሁኔታ እንኳንስ በተለያዩ ወቅቶች ለሰጡት ቃለ መጠይቅና  ጽሑፍ መልስ ለመስጠት ይቅርና ሀሳቤን ሰብሰብ አድርጌ አንዲት ገጽ ጥሩ ይዘት ያላት አርቲክል ለመጻፍ የሚያስችለኝ አይደለም ሆኖም ግን የግለሰቡ የእምነት ክህደት ስላስቆጣኝ ሳልፍና ሳገድም የጫርኳት በመሆኗ የይዘት ግድፈት ካለ  እኔዉ ተጠያቂ ሁኜ የአጻጻፍ ጉድለቱን አስተካክላችሁ መሰረተ ሀሳቡን ትረዱ ዘንድ እጠይቃለሁ::

5 Comments

5 Comments

 1. Abel

  February 8, 2018 at 10:00 pm

  You are a supporter of “Ginbot 0” the useless organisation. Ato Abreham Yaeh was right to tell Ginbot 0 not to go to Eritrea. Ato Abreham Yaehh is a true Ethiopian who also warned us about the fascist TPLF way back earlier during the DERG time. His call now for Tigrians to denounce TPLF and side with the Ethiopian people is timely, admirable and correct. That is all the Ethiopian people want to see. Tigrians should know Woyane is killing innocent Ethiopians in their name. There is a terrible price to pay for this crime. As Ato Abreham Yaeh said, this is the time for all Tigrians to come-out and denounce TPLF’s crimes. Particularly those Tigrians who live outside of the country in Europe and America have no excuse to stay silent. Silence is equal to collaboration to TPLF’s crimes and there will be a terrible consequence for this. May God help our country.

 2. Alemu

  February 9, 2018 at 4:16 am

  አቶ ኢሳኢያስ ያለ ምንም አጃቢ አስመራ ውስጥ መዘዋወር የሚችሉ የህዝብ ተቀባይነት ያላቸው መሪ አድርገው ያቀረቡና ብዙም ሳይቆዩ ግንቦት 7ን አስመራ ለምን ገባ ብለው ኮነኑ። ይህ አለ ምክንያት አልነበረም ጅ7 ከአስመራ ጋር ማበር ለህወሓት ሥልጣን አስጊ በመሆኑ ነው። Hahhahahhahhhhahahah… G7 has been in Eritrea for more than 8 years. Apart from being a laughing stock because of its lies, it hasn’t done anything. So far, it has never been a real threat to TPLF and it won’t be in the future, ’cause its leadership is composed of liars and thieves

 3. bazin

  February 10, 2018 at 4:23 pm

  TPLF is constantly promoting G7. The latest is demanding Eskinder and Andualem sign as a G7 members. Both TPLF and Shabia are working in unison for the distraction of Ethiopia. The pretentious ‘animosity’ between the two is just a boring drama. Berhanu’s mission is to confuse and prvent the realization of a united Ethiopian opposition.

 4. bazin

  February 10, 2018 at 4:25 pm

  I know you won’t publish my ‘reply’ but its ok.

 5. Fred

  February 11, 2018 at 7:51 pm

  I wonder why Wedi Yayeh wants to speak up only when he senses some danger to the existing order. I also wonder why he never likes to condemn the atrocities and killings committed by the TPLFascists. Not that we care. But he should know that he is fooling nobody but himself.

Leave a Reply

Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top