የዕለቱ ዜናዎች

ማሳሰቢያ – ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ ተጠርቷል | ከኦሮሚያ ቄሮዎች የቀረበ ጥሪ

የሥራ ማቆም አድማ ከኦሮሚያ ቄሮዎች የቀረበ ጥሪ

አማራ ክልል፣ ደቡብ ክልልና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ

ከ5/6/2010 – 9/6/2010 ዓ.ም የሁሉም ስራ ማቆም አድማ እንዲካሄድ የ ኦሮሚያ ቄሮዎች ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል። አድማው ከኦሮሚያ ክልል አማራ ደቡብና ከሌሎች ጋር የሚካሄድ ይሆናል። ተቃውሞው ያስፈለገበት ምክንያት
1. የ ፖለቲካ እስረኞች ያለምን ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ
2. በኦሮሞ እና አማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመው ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆም
3. ወንጀልን የፈፀሙ በህግ መጠየቅ አለባቸው። ወዘተ
ቀጣዩ እርምጃ ወደፊት ይፋ ይሆናል።
ስራ ማቆም ላይ የሚሳተፉ:-
የመንግስት ስራ፣ የግል ስራ፣ ትራንስፓርት ላይ(ታክሲ፣ ባጃጅ እና ወዘተ) የንግድ ስራ ሁሉ ይዘጋል::
አድማው ስራ ላይ መዋሉን ቄሮዎች ይቆጣጠራሉ። እስከዛ ድረስ መላው የኦሮሚያ ቄሮዎች በወደዋወል እስከዛው ድረስ ሼር ተደረረጉ።
ህዝቡ ምግብ፣ ከሰል፣ ለማገዶ የሚያስፈልጉትን ቅድመ ዝግጅት ማረግ አለባቸው።
ከኦሮሚያ ቄሮዎች የቀረበ መልእክት

 

“በነዚህ ቀናት ከዚህ በፊት እንደሚደረገው የመንግስት ስራ አይኖርም፣ ሶቆች ዝግ ይሆናሉ፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ይገታል። ህዝቡ ይህንን አውቆ ከወዲሁ ዝግጃድ እንዲያደርቅ ይመከራል። በተለይ ወደ ፊንፊነ የሚገባ እና የሚወጣ ተሸከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር እና እርምጃ ስለሚወሰድ ተጓዦች እና አሸከርካሪዎች ከአሁኑ ዝግጅት በማድረግ ለሶስቱ ቀናት ባሉበት እንዲቆዩ ይመከራል።”

– ጀዋር መሐመድ የቄሮን ጥሪ ተከትሎ ካስተላለፈው መል ዕክት የተወሰደ::

1 Comment

1 Comment

  1. areda

    February 11, 2018 at 10:44 am

    ከ5-9 ቀናት ሦስት ቀን ብቻኮ አይደለም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ ጽሁፎች

To Top