ዛሬ በባህርዳር ከተማ ዝናብ እየዘነበም ቢሆን ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ያለው ምስል በከፊል

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

ያማራው ህዝብ ጨዋ እንጂ ፈሪ አይደለም!
ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠው መሬታችን ይመለስ!
የሙስሊም መፍት ሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ባስቸኩዋይ ይፈቱ!
እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም።!
የመሳሰሉት መፈክሮች ተሰምተል!

አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር የጠራው ሰላማዊ የተዋውሞ ሰልፍ በድምቀት ተጠናቋል። በመጨረሻም የምዕራብ ጎጃም የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሩ እና ሌሎችም አመራሮች በሰልፉ ላይ ንግግር እድርገዋል፡፡ በዕለቱ ከ 50 ሺህ በላይ የሚሆን ሰልፈኛ መሳተፉ ተገልጿል። ቨሌላ በኩል በሰ፤ፉ መካክል አንድ የቀበሌ አመራር ሰዎችን ለማስፈራራት ሲሞክሩ በሕዝብ ትብብር ከሰልፉ እንዲገለሉ የተደርገ ሲሆን ሕብረተስቡም የግለሰቡን ማስፈራራት አጣጥሎታል።
ዛሬ በባህርዳር ከተማ ዝናብ እየዘነበም ቢሆን ሰላማዊ ሰልፍ ሳይቋረጥ የተካሄደ ሲሆን በወቅቱም የሚሰሙ የነበሩ መፈክሮች
ያማራው ህዝብ ጨዋ እንጂ ፈሪ አይደለም!
ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠው መሬታችን ይመለስ!
የሙስሊም መፍት ሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ባስቸኩዋይ ይፈቱ!
እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም።!
የታሰሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ!
መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር!
መንግስት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም!
መንግስት ለብሄራዊ መግባባት ባስቸኳይ መልስ ይስጥ!
ውሸት ሰልችቶናል! ይቁም!!!
የጸረ – ሽብር ህጉ ባስቸኳይ ይሰረዝ!
ዘርን መሰረት ያደረገ ማፈናቀል ባስቸኳይ ይቁም!!
ሙወስና የስርአቱ መገለጫ ነው!!
የአባይ ጉዳይ የኢትጵያ ሕዝብ ነው!
ለተከሰተው የኑሮ ውድነት ተጠያቂው መንግስት ነው!!
የዜጎች ሰብአዊ መብታቸውን የማግኘት መብታቸው ይከበር!!
ዜጎች በሀገራቸው ስራ የማግኘት መብታቸው ይከበር!!
በአባይ ጉዳይ ወሳኙ የኢትጵያ ሕዝብ እንጂ ግብጾች ይደሉም!!
የፓርቲ አባልነት በፍላጎት መሆን አለበት!!
የመሳሰሉት መፈክሮች ተሰምተል!
በተያያዘም ዜና በባህር ዳር የመንግስት ካላት አረንጓዴ ሽብር የሚል ወረቀት እየተበተነ እንደነበረ ተረጋገጧል፤ “አረንጓዴ ሽብር” የሚል በነጭ ወረቀት የተባዛ እና የአንድነትን የስልክ ቁጥር የያዘ በራሪ ወረቀት እየተበተነ መሆኑ ታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የበተነው በራሪ ወረቀቶች ቢጫና ቀይ ብቻ ናቸው፡፡ ‪#‎millionsofvoicesforfreedom‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎UDJ‬

 

Bahir dar Demo. 1 Bahir dar Demo. 2 Bahir dar Demo. 3 Bahir dar Demo. 4 Bahir dar Demo. 5 Bahir dar Demo. 6 Bahir dar Demo. 7 Bahir dar Demo. 8 Bahir dar Demo. 9 Bahir dar Demo. 10 Bahir dar Demo. 11 Bahir dar Demons

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *