ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በእሳት እየነደደ ነው

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


(ዘ-ሐበሻ) በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ደብርንርሃን ከተማ ውስጥ የሚገኘው የደብረብርሃን ዩኒቭርሲቲ ውስጥ የ እሳት ቃጠሎ መነሳቱ ተሰማ:: ቃጠሎው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንዳለ ዘ-ሐበሻ ያገኘችው መረጃ የለም::

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተነሳው ቃጠሎ ምንነት እስካሁን ያልታወቀ ቢሆንም እሳቱ እንደተነሳ ለ እሳት አደጋ ቢደወልም የ እሳት አደጋ ሰራተኞች ቶሎ እንዳልመጡና ቀድምው የአጋዚ ወታደሮች ዩኒቨርሲቲውን እንደከበቡት ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

እንደምንጮች ገለጻ ከሆነ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እሳት አደጋውን ለማጥፋት ቢረባረቡም በአንዳንድ ተማሪዎች ላይ የአጋዚ ወታደሮች ካለምንም ምክንያት ድብደባ ፈጽመዋል::

ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድረገጽ ላይ ዘ-ሐበሻ ካገኘችው መረጃ መረዳት እንደተቻለው በዚህ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከአስር ሺህ ያላነሱ ተማሪዎች ይማራሉ::

One Response to ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በእሳት እየነደደ ነው

 1. » በጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ አቶ ኅይለማርያም ደሳለኝ በዚሁ ሳምንት ቁጥራቸው ፱ሺህ የሚደርሱ ታዳሾችን አስመረኩ ሲሉ ነበር። __የተሃድሶው መፈክር፡ መሪ ቃል “NEVER AGAIN! አይደገምም! ነው ብለዋል።” ለመሆኑ የማይደገመው ምን ይሆን? ተመልሳችሁ ተይዛችሁ እራሳቸሁን ከመላጨት ከተሃድሶ የራስ መናወጥ አይድረስባችሁ! ማለት ይሆን? የተቻላችሁን ጥያቄ ሁሉ ጠይቁ ቀውጡት ዳግም አትያዙ ማለታቸው ነው? ይህ በኤሌትሪክ ግጭት ተነሳ የተባለለት እሳት ግልገል ግቤ፫ መመረቁን ሰምቶ ፈንድቆ ይሆን?
  __ ግን ይህ ግራና ቅኝ መሳሪያ አንግቦ፡ እጁን ኪሱ ከቶ ቆሞ የሀገር ንብረት ሲውደም የሚመለከተው ወታደር የእሱ ክልላዊ መንግስት ስላልሆነ እሳት እየሞቀ ነው?ያልይህ እሳት ካለቀ የመጣው የማዘጋጃ ቤት መኪና ፊልም ቀራጾች ይዞ መጥቶ ነው?
  _ ለነገሩ የሀገራችን ፕሬዘዳንት(ርዕሰ ብሔር) ሀገር በተቃውሞ ሲቀልጥ፡ ህዝብ ሲሸበር፡ እንደስልጣናቸው ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የባለሥልጣን አካላት፡መምህራን፡የሃይማኖት መሪዎችና የመከላከያ ሠራዊት ኅላፊዎች ሰብስበው ከማወያየትና መፍትሄ ከማፈላለግ፡ ንብርት ሲወድም፡ የድሃ ልጅ ሲሞት፡ አድፍጠው ተቀምጠው በፓርላማ በጥልቅ ከፎለሉ በኋላ የድንገተኛ አዋጅ አሳወጀው የተቃጠሉ ተቋማትን አመድ ሊጎብኙ ሄዱ፡ ጭራሽም ኢንቨስተር ለማፈላለግ ጥሊያን ሄደው ለዚሁ ሥራቸው ሲሸለሙ ሰነበቱ፡
  __ ግን የአንድ ሀገር ፕሬዘዳንት ሥልጣንና ኅላፊነት በሀገሩ ያለው የሕዝብ ንብረት በተቃውሞ ሲቃጠል፡ ቤተሰብ ሲበተን፡ ኢኮኖሚ ሲሽመደመድ እያየ፡ የሀገሩ ዜጋው እንደከብት በጭስ ደንበሮ ገደል ሲግባ እያየ፡ የቀጥታ ንግድ በማፈላለግ የሚቃትት ርዕሰ ብሔር ተሃድሶ አያስፈልገውምን?እውነትም ልዩ ነን!መከከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ጎን ቆሞ ፎቶ መነሳት ገና በ፳ሺህ ፳ አልተገኘም!!አይደገምም!!

  በለው!
  December 24, 2016 at 3:29 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.