በአምቦ ከተማ የሥራ ማቆም አድማ እየተደረገ ነው * መኪኖች ቆመዋል * ወደሌሎች ከተሞች መሄድ አይቻልም

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

አምቦ የአውቶቡስ መናኸሪያ እንዲህ ተጨናንቋል::

(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት መራሹ የኢሕአዴግ መንግስት በሕዝብ ላይ የጫነውን አግባብ ያልሆነ ግብር በመቃወም በአምቦ የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል ወደ ሌሎች ከተሞችም እየተዛመተ ባለበት በዚህ ወቅት በዛሬው ዕለት በአምቦ ከተማ ሱቆች ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸውና ትራንስፖርትም መቋረጡ ተሰማ::

የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአምቦ እንዳደረሱን መረጃ ከሆነ የሥራ ማቆም አድማው ከጠዋት የጀመረ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ነው::

መኪኖችም ሥራ በማቆማቸው በአሁኑ ወቅት ከአምቦ ወደ ሌሎች ከተሞች የሚሄዱ ሰዎች መነሃሪያዎችን አጨናንቀውታል:: ምንም ዓይነት የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ የትም ከተሞች እንደማይሄዱ የገለጹት ምንጮች አምቦ ከአውቶቡስ ተራው ውጭ ሌላው ቦታ ጭር ብላለች ብለዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<