በወሊሶ ሕዝባዊ አመጽ ተቀጣጠለ * መኪኖች ተሰባበሩ * ንግድ ቤቶች ተዘጋግተዋል

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

(ዘ-ሐበሻ) በአምቦ በድጋሚ የተጀመረው ሕዝባዊ አመጽ ወደ ሌሎች ከተሞችም በመዛመት በወሊሶ ከተማ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በህዝባዊ አመጽ ስትናወጥ መዋሏ ተዘገበ::

በወሊሶ ከተማ መንግስት አላግባብ የጣለውን ግብር በመቃወም የሥራ ማቆም አድማ እንደሚደረግ እንደዚሁም የትራንስፖርት አገግሎት እንደሚቋረጥ በሕዝቡ በተበተነ መረጃ ሕዝቡ ሲነገረው የቆየ ሲሆን ሁሉም ንግድ ቤቶች ሲዘጉ አንዳንድ ተሽከርካሪዎች ግን ሲያሸከረክሩ በመገኘታቸው ሕዝቡ በመኪና በመውገር እንደሰባበራቸው መረጃዎች ጠቁሟል::

በወሊሶ ሰላማዊ ሰልፍና እንደዚሁም በንብረቶች ላይ ጥቃት እንደተፈጸመ የሚገልጹት ምንጮቻችን ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ተዘጋግታ በአጋዚ ሠራዊት መወረሯንም ገልጸዋል::

እንደምንጮች ገለጻ መንግስት በሕዝቡ ላይ የጣለውን አግባብ ያልሆነ ግብር ካላነሳ ሕዝባዊው አመጽ ይቀጥላል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<