Hiber Radio: ባህር ዳር ውጥረት ነግሷል፣ ወጣቶች ለነጻነት ትግል ዛሬም መሳሪያ አንስተው በረሃ መውረዳቸው ተገለጸ፣የናይጄሪያዊው ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ400 በላይ ኢትዩጵያኖችን አባረረ

Filed under: News Feature,ህብር ሬዲዮ,የዕለቱ ዜናዎች |

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 30 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመታወጁ 10 ዓመት በፊት በአገሪቱ ከምርጫ 97 በሁዋላ የሆነውን ማየት ያስፈልጋል። ሕዝቡ በጸረ ሽብር አዋጁ፣በአፈናው፣በመያድ አዋጁ በየትኛውም መንገድ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ሀሳቡን እንዳይገልጽ የተደረገበት ገደብ አድጎ አፈና ሲበዛ በአደባባይ ለተቃውሞ ለዚያ የተሰጠው ምላሽ ተጨማሪ አፈና ሲሆን ወደ አመጽና ብጥብጥ አድጓል …ዛሬም የተለወጠ ነገር የለም የተለመደ አፈና ካለ ስርዓቱ ራሱ ለመለወጥ ካልፈለገ ሕዝቡ ስርዓቱን …> የአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህሩና ጦማሪው ስዩም ተሾመ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ያድምጡት)

<…በባህር ዳር በአንድ ቀን የፈሰሰው የንዩሃን ደም የሚረሳ አይደለም ሕዝቡ ሰማዕታቱን ሲያስብ አደራቸውን መርሳት የለበትም…የለውጥ ፈላጊው ተቃዋሚ እርምጃን በተለይ የእውነተኛ ትብብር አለመኖር አንዱ ከአንዱ ጋር ተባብሮ ያለመስራቱን በተመለከተ በተለይ ሚዲያው ግልጽ ውይይት የሚደረግበትን የህዝቡ ትግል በእውነት የሚደገፍበትን ለለውጡ የሚደረገው እንቅስቃሴ ትርጉም ያለው እንዲሆን ሀላፊነት ያለባችሁ ይመስለኛል… > አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጠን ማብራሪያ(ቀሪውን ያድምጡት)

የኢትዮጵያዊቷ አትሌት አሳዛኝ የባህር ማዶ ኑሮ ሲፈተሽ

“እንደ አሮጌ ቁና ተጣልኩኝ፣እንደ ባሪያ ነበር የተቆጠርኩት” (ልዩ ዘገባ)

<…በደህነት መ/ቤት ውስጥ የነበሩ ሁለት የትግራይ ተወላጆች ተጋጩ ፤የግጭቱ መነሻ አፋር የኔ የጨው ማምረቻ አካባቢ እሱም ከፍቷል ያ አካባቢ የኔ ነው ለአፋሮቹም ነግሬያቸዋለሁ የሚል ነው።አፋሮቹ በጨው ላይ ስልጣን ሳይኖራቸው ሁለቱ የኔ ግዛት ነው በሚል ይጣሉ ነበር። የሙስናው ዘመቻ እነሱን አይነካም ሌላውን ለማጥቂያ ካልሆነ…> የቀድሞው የአማራ ክልል የደህነት ሀላፊ አቶ አያሌው መንገሻ ከሰጡት ሰፋ ያለ ማብራሪያ(ክፍል ሁለት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም መልስ ያላገኘው ሕዝብ ተመሳሳይ ተቃውሞና አመጹን ይቀጥላል ተባለ

ወጣቶች ለነጻነት ትግል ዛሬም መሳሪያ አንስተው በረሃ መውረዳቸው ተገለጸ

ኢህአዲግ በህዝቡ ላይ ጥሎት የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተንስቷል ቢልም የህጉ ሰለባዎች ዛሬም እየማቀቁ ይገኛሉ

በባህር ዳር በአጋዚ በግፍ የተገደሉ ሰማዕታትን ለማሰብ የተጠራውን አድማ ተከትሎ ውጥረት ነግሷል

ከቦንቡ ፍንዳታዎች ጀርባ የሕወሃት ደህነቶች ተጠርጥረዋል

ግዙፉ የናይጄሪያዊው ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ400 በላይ ኢትዩጵያኖችን ያለ ስራ ዋስትና አባረራቸው

“መስራት እየቻልን በጠባብ ፓለቲካ ሳቢያ ውንብድና ተፈጽሞብናል”የእርምጃው ሰለባዎች አቤቱታ በከፊል ሲነበብ

የኢህአዲግ አገዛዝ በ አ/አ በሰሜን ኮሪያ ዲፕሎማቶች እና ወታደራዊ ባለሙያዎች ላይ ቁጥጥር ማድረግ ጀመረ

ኢህአዲግ ጦሩን ቁልፍ ወደ ሆነች የሶማሊያ ግዛትሰሞኑን ላከ

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በድንበር ምክንያት ግጭቶች መበራከታቸውን የዶ/ር በየነ ጴጥሮስ ፓርቲ ገለጸ

ሰማዕታቱ ሲታሰቡ የተነሱለት ዓላማ ሊታወስ እንደሚገባ ተገለጸ

በሆድ እቃው ውስጥ አደንዛዥ እጽ ሸሽጎ ለማለፍ የሞከረ ተጓዥ በኢትዬጵያ አየሮፕላን ውስጥ መሞቱ አነጋጋሪ ሆነ፣

አትዬጵያኖችን በህገውጥ መንገድ ሲያሸገገር የነበር ግለስብ ኬኔያ ውስጥ ህይወቱ በጠፋ ወገናችን ጉዳይ በፓሊስ አየተፈለገ ይገኛል

እና ሌሎችም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.