በባህርዳር የተደረገውን ሕዝባዊ አድማ ባልተባበረው ካሪቡ ካፌ ዛሬ ቦምብ ፈነዳ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |
974 Shares

(ዘ-ሐበሻ) የነሐሴ 1 ቀን በሕወሓት መራሹ መንግስት የደረሰውን ጭፍጨፋ ለማሰብ የተጠራውን የሥራ ማቆም አድማ ሳይተባበር ካፌውን ከፍቶ ሲሰራ ነበር በተባለው የባህርዳሩ ካሪቡ ካፌ ዛሬ የቦምብ ፍንዳታ መደረሱ ተሰማ::

ከምሽቱ 2:50 አካባቢ ደረሰ የተባለው ይኸው የቦምብ ፈንዳታ በቀበሌ አራት ልዩ ቦታው ሎተሪ ቤት ፊት ለፊት ካሪቡ ካፌ እና ዋዜማ ጃምቦ ሀውስ መካከል ነው::

በዚህ የቦምብ ፍንዳታ በሰዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት እያጣራን ነው:: እስካሁን ሁለት ሰዎች ሞተዋል የሚል መረጃ ቢደርሰንም ጉዳቱ ከዚያም በላይ ነው እየተባለ ነው::

ቀደም ሲል በአማራ ተጋድሎ አስተባባሪዎች አማካኝነት በተበተነ ወረቀት ” የአማራ ሰማዕቶችን ቀን ለመዘከር በባህር ዳር የተጠራውን አድማ አሻፈረኝ ብለው ከስርዓቱ ጋር በመወገን ድርጅታቸውን ከፍተው ሥራ ሲሰሩ ከነበሩት ካሪቡ ካፌ አንዱ ነው።” የሚል ማስጠንቀቂያ ተበትኖ ነበር::

በባህርዳር በርካታ ነጋዴዎች ንግዳቸውን ዘግተው በአድማ ተሳትፈዋል በሚል መታሰራቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

 

ለቦምቡ ፍንዳታ ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም::

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *