ታላቋ ትግራይን እንድለማመድ የተለቀቀው ካርታና የኢቢሲ ይቅርታ | ቬሮኒካ መላኩ

Filed under: News Feature,ነፃ አስተያየቶች |

1~የEBC ን ውሃ የማያነሳ ማስተባበያና ይቅርታ አነበብኩት ። ፈረንጅ ሲተርት እንደዚህ ይላል “Fool me once, shame on you; Fool me twice, shame on me”…( አንድዬ ካታለልከኝ በአንተ አፍራለሁኝ ። ለሁለተኛ ጊዜ ካታለልከኝ ግን በራሴ ቂልነት አፍራለሁኝ ።) ይላል።

በእኔ በኩል EBC የሚያታልለው ንቃተ ህሊና ባለቤት ስላልሆንኩኝ “ይቅርታው ” ይለፈኝ።

2 ~ EBC የሚባለው ተቋም የራሱ የህውሃት እንደሆነ የታወቀ ነው። እንደ ራሱ ንብረት ሲጠቀምበት ነበር ። ፖሊሲውን ያስፋፋበታል። ማኒፌስቶውን ያራምድበታል። አማራን ይኮንንበታል።
በሌላ በኩል EBC ን ማመስገን ይገባል እንደዚህ ያለ ስሜት ኮርኩሮ የሚያቃጥል ድብቅ ሴራ እያቀረበ የደነዘዙ አማሮችን ቀስቅሶ ወደ አማራነት ካምፕ እንድቀላቀሉ ስለአነቃልን መመስገን አለበት።
ለማንኛውም ስህተቱ የተሰራው በፌስቡክ ሳይሆን በቴሌቪዥን ስርጭት ላይ በመሆኑ ይቅርታውም መጠየቅ ያለበት በቴሌቪዥን እንጅ ከጠቅላላው ህዝብ 1% የማይሞላ ህዝብ በሚጠቀምበት በፌስቡክ አይደለም።

3~ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተተክሎ አማራ ህዝብ ውስጥ የሚቀበር የ Time bomb ፋብሪካ ቶሎ ካልመከነ አማራ በአገሩ Homeless መሆኑ የማይቀር ነው ።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የመምህርነትና የሰራተኝነት ጭምብል አጠልቆ አዲስ የፖለቲካ መልክአ ምድር ለመፍጠር ፕሮጄክት ቀርፆ አማራን ከባድና ሊወጣው የሚያስቸግር አደጋ ከመደቀኑ በፊት እንደት ማስቀረት እንደሚቻል ማሰብ አለብን።

4 ~የዚህ Time bomb ፋብሪካው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን የቦምቡ ማፈንጃ እና መቆጣጠሪያ ሪሞት ኮንትሮል ደሞ የሚመረተው መቀሌ ነው።
አማራ አፍንጫህ ስር መሽጎ “የቦምቦች ሁሉ እናት ” እያመረተ የሚቀብርብህን “መርስኔሪ ” ቶሎ መፍትሄ ካልሰጠህው ማለቅህ ነው። እኛ አሁንም ተኝተናል እነሱ ግን 7ቱንም ቀናት እና 24 ሰአታት አማራን ለማጥፋት እየሰሩ ነው።

5~ አማራ ሆይ በየአመቱ ፣ በየወሩ ፣ በየሳምንቱ በየቀኑ ፣ በየሰአቱ ፣ በየደቂቃው እና በየሰከንዱ እየተሰረቀ እና እየተዘረፈ ያለውን ማንነታችንን ፣ መሬታችንና ርስታችንንርስታችንን ለማስመለስ በአንድ ላይ ካልቆምን መጥፋታችን ነው።

5 Responses to ታላቋ ትግራይን እንድለማመድ የተለቀቀው ካርታና የኢቢሲ ይቅርታ | ቬሮኒካ መላኩ

 1. God bless the Amharan people. God give the power for the people of Amara to defend them selfves from the fasciest gangster tplf.

  nabil
  August 27, 2017 at 2:22 pm
  Reply

 2. zim belew abo !

  be Amara tagay sim le amist5 tekefaflew eyetebalu new

  weyane sayhed yesiltan shimeya !!

  yebilagn le Amara!!

  bertu gifu malet , Hager bet yalewin Amara new ! ::

  Seyfu
  August 27, 2017 at 6:52 pm
  Reply

 3. fantastic illiterates’ drama
  save in your document and your soft ware mind. something is coming soon!11

  hassan
  August 28, 2017 at 6:04 am
  Reply

 4. ወያኔ ሃገር ማፍረስ የጀመረው ገና በበረሃ እያለ ነው። ለወያኔ ህብረት፤ ውህደትና አንድነት ጭራሽ የማይዋጥለት እውነት ነው። ዛሬ በዘርና በጎሳ የከለላትን ሃገር ለራሱ እንዳመቸ ሲፈነጥዝባት ዘመናት ተቆጥሮአል። የሚገርመው ግን ጊዜው ሲመሽ እንኳን ጨለማን ከብርሃን መለየት አለመቻላቸው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን ከተፋው ቆይቷል። ያው በታጠቀው መሳሪያ እያስፈራራና እያፈነ ዛሬም እንደትላንቱ እኖራለሁ ብሎ ማሰቡ ግን ሞኝነት ነው። በባህርዳር በወያኔ አነጣጣሪ ተኳሾች ወደ ሥራ ስትሄድ ከሞተችው ሴት ቦርሳ የተገኘ ጽሁፍ እንዲህ ይላል።
  ፈጣሪ ጥሩ ነው ዘመን ያሻግራል
  ለእኔም ቀን ወቶልኝ አልፎልኝ በኑሮ
  እናቴን አባቴን እንካችሁ የምለው
  ጊዜው መቼ ይሆን ጥቂቱ ተርቦ
  ብዙው ጠግቦ እሚያድረው?
  ራሷ በጥይት ተቦድሶ፤ ቡናማ ቦርሳዋ አጠገብዋ ሰው ሆን ብሎ እንዳስቀመጠው እስከሬኗን የሚይይ ዓይን ያለው ፍጡር ይመስላል። ፎቶው በብዙ ድህረ ገጾች ላይ ሰውን ያላቀሰ ነው። ወያኔ ዲሞክራሲን አያውቃትም። ዛሬ በሃገር ውስጥ መጽሃፍ ጽፈው ላሳታሚ ከሰጡ በህዋላ አሳታሚውን በማስፈራራት ህትምት እንዲቆም ያደርጋሉ፤ ከባንክ ገንዘብ ይዘርፋሉ። በጥቁር ገቢያ የዶላር ለዋጮች በሙሉ የወያኔ የድብቅ ሰራተኞች ናቸው። በንግድ ዓለም የተቃረናቸውን ከውድድር ያስወጣሉ፤ ያፍናሉ፤ ይገድላሉ። በዚህ ዓመት ብቻ የአሜሪካ መንግስት ስድስት ጊዜ ዜጎቿ በኢትዮጵያ በሚዘዋወሩበት ሥፍራ ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያረጉ ይመክራል። እንደ ፈሳሽ ውሃ በፈለገው ጊዜ ወያኔ የሚቆልፈው የኢንተርኔት አገልግሎት ሰው ለሰው እንዳይረዳዳ ሆን ተብሎ የሚደረግ አፍራሽ የወያኔ ሴራ ነው።

  ታላቋ ትግራይ የወያኔ ህልም እንጂ እውነትነት አይኖረውም። ህልማቸው በአለም መንግሥታት ተቀባይነት የምይኖረው፤ ቀሪውን የኢትዮጵያ ህዝብ ለጦርነት የሚያዘጋጅ ነው። እርስ በርስ የሚያስተላልቅ ህልም ነው። ኢትዮጵያ ፈርሳ ትግራይ አትኖርም። ለዘመናት የአማራን ህብረተሰብ እንደ ቀንደኛ ጠላትነት የፈረጀው ወያኔ አሁንም በጎንደር ቅማንት ለራሱ ይሁን እያለ የሚያድበሰብሰው የአማራን ህዝብ ለመከፋፈል እንጂ ሌላ እይታ የለውም። በኤቢሲ የታየውም ካርታ ትክክለኛ ወያኔ የነደፈውን ሴራ ያሳያል እንጂ ማስተባበያ አያስፈልገውም። ወያኔ እኮ ደንቆሮ ነው። አባይን ትግራይ ውስጥ ነው ብሎ መጽሃፍ እንዲጻፍ ያደረገ ጭፍን ድርጅት። እንደሚታወቀው የአባይም ወደ ትግራይ በካርታ ላይ መጠቃለል በስህተት ነው ተብሎ ነው የታለፈው።
  ዘፋኞች የሙዚቃ ድግሳቸውን ለማቅረብ የማይፈቀድበት፤ የመሰብሰብና የመናገር ነጻነት የተነፈገበት፤ በሙስና ስም ሲበሉ ያዮትን እንጂ የበሉትን የማያስር፤ በዘር ችርቻሮ የከበረው የጠባብ ብሄርተኛው ቁንጮ ወያኔ የሮም አወዳደቅ ሲወድቅ ይታየኛል። ዛሬ በፀረ-ሽብር በሙስና እያመካኘ በሃገሪቱ እስር ቤቶች ያገታቸው የወያኔን ድብቅና ይፋ ሴራ የተጋፈጡትን ነው። ሃገር ማለት ለወያኔ ትግራይ ብቻ ነው። የለማው፤ የተሻለ ቀለም መሸመቻ የትምህርት ተቋማት የቆሙለት ለትግራይ ህዝብ ብቻ ነው። ሌላው ፍርፋሪ ለቃሚ ነው። በወያኔው አለቃ ሞት የተነሳ ወያኔ የባለ ብዙ አለቆችና የአዕላፍ ነጭ ለባሾች ስብስብ በመሆኑ መልህቅ እንደለላት መርከብ አቅጣጫ አልባ ነው የሚጓዙት። ጠ/ሚ የይስሙላ፤ ምክትል ጠ/ሚ በጥፊ በወያኔ የሚመታ (በዶ/ር ደብረጽዮን)፤ ጠበንጃ አንጋቹ በወታደርነት ስም የሚዘርፍና ህዝባችንን በሜዳ የሚረሽን የጨካኞች ስብስብ ነው። ወያኔ የጎንደርን ቆላማ ክፍል ለሱዳንና ለራሱ እየሸራረፈ የሚወስደውም የአማራን ህዝብ ለማበርክከ ነው። ሱዳንን አቆላምጦ ካልያዘ በዚያ በኩል የሚገቡ የተቃዋሚ ድርጅቶች ወያኔን በቀላሉ እንደሚያጠፉት ያውቃል። ምንም ይሁን ምንም ወያኔ ለፈጸመው ሃገር አፍራሽ ሥራው ዋጋ እንደሚያገኝ አምናለሁ። ጊዜው እየቀረበ ነው። ጀሮ ያለው ይስማ!!

  Tesfa
  August 29, 2017 at 4:03 am
  Reply

 5. እነ ሞረሽ፦ ዕብዱ ተክሌ ይሻው ኣታላዮች ደምስ በለጠ፣ ሙሉቀን ተስፋው፣ምን ዓይነት ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብየ ሳስብ ሳሰላስል
  ፩ ከልክ በላይ ፈሪ
  ፪ በፖለቲካ ነግዶ በኣቋራጭ የገንዘብ ሆነ የስልጣን ጥቅም ማግኘት
  ፫ በማይረዱት እና ስለ ፖለቲካ ትግል በቂ ዝንባሌ ሳይኖራቸው እና ሳይገነዘቡት እየተንቦጫረቁ የደርግን 17 ዓመታት እና የውያኔን 26 ዓመታት በድምሩ 43 ዓመታት ሌላ 43 ቢጨምርም ግድ የማይሰጣቸው።
  ብእግር ኳስ ጨዋታ ኣንድም ተከፍለዋቸው ወይም በችሎታ ማነስ በገዛ ቡዱናቸዉ ግብ የሚያገቡና ጨዋታውን የሚያደናቅፉ ተጫውቾች ብዙ ጊዜ ተከስተዋል ታድያ እነ ሞረሽ ከዚህ ምንድነው የሚለያቸው።

  Gechu
  August 29, 2017 at 9:04 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<