የተነገረው ሁሉ ግን ትንቢት አልነበረም! * የጎንደር ድንበርን ገፍቶ ትግራይ ማስፋፋቱ ለኢትዮጵያችን ይጠቅም ይሆን ? – ነብዩ ሲራክ

Filed under: News Feature |

የማለዳው ወግ … የተነገረው ሁሉ ግን ትንቢት አልነበረም !
=================================
ከወራት በፊት በመማሪያ መጽሐፍቱ የጎንደር ራስ ዳሸን ወደ ትግራይ ክልል ተደረገ ፤ ሀገሬው ጉዳዩን ተመልክቶ እየተቀባበለ እያነሳ ሲጥለው እውነትና እውሸት ተፈጠጡ። እውነቱን መካድ አይቻልምና ከብዙ አመታት በኋላ ” ስህተት ነው ተስተካከለ ” ተባለ ። ዝም አልን …

በዚያው ሰሞን የወሎው ላሊበላ በቱሪዝም በመላው አለም የተሰራጨ ማስታወቂያ ላይ ታላቁ የላሊበላን አብያተ ክርስትያን የትግራይ እንደሆነ ነገረን ። ይህም ብዙ ጩኽት ፣ ብዙ ዋይ ዋይታ ፣ ብዙ ትዝብትና ሽሙጥ ካስከተለ በኋላ ” የፈረንጁ አነባበብ ነው ፣ በስህተት ነው ተስተካከለ ” ተባለ ። ስለኢትዮጵያ ይሁን ተባፀ ፣ ዝም ጭጭ ተባለ ፣ ታለፈ !

ከዚህ ሁሉ የማያልቅ “ስህተት ” በኋላ በያዝነው ሳምንት ሌላ “ስህተት ” የተባለ ጉድ ሰማን ፣ አየን ። ጉድም ሳይሆን መርዶ ነበር :( ጎንደርን ከሱዳን ድንበር ለያይቶ ፣ ትግራይን ከሱዳን ድንበር አጠጋግተው አሳዩን ፣ ይህን የሌለ ድንበር ለትግራይ ያጎናጸፋትን ካርታ ያየነው በመንግስት ቴሌቪዥን ነበር ።… ካየነ በኋላ ይህ መሰሉ “ስህተት” እንዳልሆነ ደግሞ ቀድሞውኑ የተስፋፊውን ወገን ክፋት የሚያውቁት ደጋግመው ሲነግሩን ያልሰማን ለማመን ተገደድን ። አዘንን :(

በያዝነው ሳምንት ነሐሴ 18 2009 ይፋ የሆነው ይህ ካርታ ጎንደር አግልሎ ትግራይን እስከ ቤኒሻንጉል አስፋፍቶና ከሱዳን ጋር ድንበር ያጎናጸፈው ካርታ ደግሞ እነሆ ዛሬ እንደገና የቀረበው በስህተት መሆኑ ተነገረ :(

መንግስት ” ስህተት ” እያለ የደጋገመው ሸፍጥ ከዚህ ቀደም የተነገረ ነበር ፣ እናም የተነገረው ትንቢት አልነበረም ። አሁንም ይቀጥላል … ከቶ የወሎን ላሊበላ ወስዶ ፣ የጎንደር ድንበርን ገፍቶ ትግራይን ማስፋፋቱ ለኢትዮጵያችን ይጠቅም ይሆን አጀብ ! የጉድ ሃገር :( መናገር የምፈልገው ሁሉ በአንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ተገለጿልና የምጨምረው የለም !

ወዳጆቸ ማሳሰቢያ !
============= ” ስህተት ” በሚል ተደጋግሞ የሰማነውና ያየነው ቀድሞ የተፈራ ህልም በህብረትና በአንድነት ከቀረው ኢትዮጵያ ጋር አብሮ የኖረውን የትግራይ ህዝብ ፍላጎት ይወካላል አልልም ። ስለዚህ ከዚህ በላይ ባቀረብኩት መረጃ ስር ይቅርታ ከተጠየቀበት ካርታና ከተዘማጅ ጉዳይ ባለፈ ዘር ተኮር ጥላቻን የያዘ ማንኛውንም አስተያየት እንደማላስተናግድ በአክብሮት አሳውቃለሁ !
ኢትዮጵያን ከከፋፋዮች መሰሪ ተንኮል ይጠብቃት !

ነቢዩ ሲራክ
ነሐሴ 22 ቀን 2009

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<