በምስራቅ ሸዋ ወለንጪቴ ከተማ ሁለት ወጣቶችን በጥይት አቁስሏል የተባለ የከተማው ነዋሪ ሰላይ በሕዝብ ተገደለ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


(ዘ-ሐበሻ) ትናንት በምስራቅ ሸዋ ቦሰት ወረዳ ወለጪቴ ከተማ ቀበሌ 01 በተለምዶ ሸዋ በር ተብሎ በሚጠራው ቦታ 2 ወጣቶች በጥይት መመታቸውን ተከትሎ ሕዝቡ በወሰደው እርምጃ አንድ የከተማውን ሰላይ ገደለ::

በወለንጪቴ ከተማ በነበረው የሕዝብ ተቃውሞ ላይ በመገኘት 2 የኦሮሞ ተወላጅ ወጣቶችን አቁስሏል የተባለውና ይኸው የከተማው ሰላይና ወታደር ገብረመስቀል በህዝቡ እርምጃ ሊወሰድበት እንደቻለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል::

እንደምንጮቹ ገለጻ በከተማው ሕዝቡን በመሰለልና ለመንግስት አሳልፎ በመስጠት ይታወቃል የተባለው ገብረመስቀል በትናንትናው ዕለት ወጣቶቹን በጥይት መትቶ አቁስሏቸዋል በሚል በአካባቢው ነዋሪ ጥርስ ተነክሶበት የነበረ ሲሆን ወዲያውኑ እርምጃ እንደተወሰደበት ነው የተዘገበው::

One Response to በምስራቅ ሸዋ ወለንጪቴ ከተማ ሁለት ወጣቶችን በጥይት አቁስሏል የተባለ የከተማው ነዋሪ ሰላይ በሕዝብ ተገደለ

  1. Essai, essai!! Wollad be debab tehid’. A wonderful news. That is what needs to be done to the enemies of the people.
    Glory be to the sons and daughters of our land for having dealt with the TPLF skunk.

    Z'nnah
    September 11, 2017 at 4:25 am
    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<