የቅማንት ምርጫ ውጤት፣ በኦሮሞና በሶማሌ መካከል ለተነሳው ግጭት፣ ሕወሃት፣የተዘጋው የአህያ ቄራ ይከፈትልን መባሉ፣ የቴዲ አፍሮ ጉዳይ፣ የኦብነግና የኦፌኮ መሪዎች የጋራ ጥሪ ሌሎችም ዜናዎች

Filed under: News Feature,ህብር ሬዲዮ,የዕለቱ ዜናዎች |

የህብር ሬዲዮ መስከረም 7 ቀን 2010 ፕሮግራም

<...አብሮ በኖረው የኦሮሞና የሶማሌ ህዝብ መካከል እሳት ጭረው ሕወሃቶች ቆመው ማየት ብቻ ሳይሆን ባልተጠሩበት የቅማንት ጉዳይ ቀድመው ሰራዊት ሲያዘምቱ እዚህ ግን ሰራዊቱ ዳር ቆሞ እንዲያይ አድርገዋል...የጎሳ ፌዴራሊዝም መጨረሻው ይህን ችግር ያስከትላል ክልል የመጣው ከደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ስርዓት ነው።ከልሎ ከማስተዳደር ለመከፋፈል...> ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ በወቅታዊ ጉዳይ ከህብር ጋር ካደረገው ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ (ክፍል አንድ)

<...በዚህ ምርጫ ያሸነፈው የአማራና የቅማንት ሕዝብ ነው። አብረን እንደኖርን አንለያይም ብሎ ድምጹን ሰጥቶ በነባሩ አስተዳደር ስር ለመቆየት በአንድ ጎንደሬነቱ ለመኖር እንዳሰቡት ሳይከፍሉት ቀርተዋል...> አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ ስለ ሕዝበ ውሳኔው ከሰጠው አስተያየት የተወሰደ(ቀሪውን አድምጡት)

<...የዚህ ሁሉ ችግር ምንጩ ወያኔ ሆን ብሎ አብሮ ነኖረው የሶማሌና የኦሮሞ ሕዝብ መካከል የቻረው እሳት ።የዚህ ችግር መነሻው ወያኔ ሴራ ነው... > አቶ ሐሰን አብዱላሂ የኦብነግ ስራ አስፈጻሚና የኮሚኒኬሽን ሀላፊ በወቅታዊ ጉዳይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት)

<...ሕወሓቶች ሕዝቡን እስር በእርስ አጋጭተን የፈለግነውን እናገኛለን ብለው ራሳቸው ከጀርባ እሳት ጭረው መልሰው እንደ ገለልተኛ ዳር የሚያዩት ወያኔዎቹ ናቸው። ከተጠያቂነት አያመልጡም ሕዝቡ ኦሮሞና ሱማሌ ብቻሳይሆን ሁሉም በጋራ ለችግሩ መፍትሄ መፈለግ አለበት።እነሱ ያሰቡት ጥፋት ይህ ብቻ አይደለም...> አቶ ነጌሳ ኦዶ የኦፌኮ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ቡንድ ሊቀመንበር በወቅታዊ ጉዳይ ከሰጡን ማብራሪአ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

በኦሮሚያ እና በኢትዮ ሶማሊያ ተወላጆች መካከል ሰሞኑን የተፈጥረው እልቂት በአለም ሚዲያዎች ዘንድ ሲቃኝ(ልዩ ዘገባ)
“ባለቤቴ ለምን ይህንን አሳዛኝ ጉዳት እንዳደረሰብኝ አልገባኝም”የኢትዮጵያዊቷ ሰቆቃ ከባንኮክ ሆስፒታል እስከ አዲስ አበባ (ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በሶማሌና ኦሮሞ መካከል አስቀድሞ ግጭት አናስነሳም ያሉ 17 የሶማሌ የአገር ሽማግሌዎች መታሰራቸው ተገለጸ

ግጭቱ ሆን ተብሎ በሕወሓት መቀስቀሱን የኦብነግና የኦፌኮ መሪዎች በጋራ ገለጹ

ሕዝቡ ህወሃት ያቀደውን የህዝበ ውሳኔ ሴራ በምርጫው አሸነፈ

ውጥረት ነግሷል

ደ.ዘይት(ቢሾፍቱ ) ውስጥ ስራውን ጀምሮ የተዘጋው የአህዮች ቄራ ዳግም እንዲከፈት ለአቶ ሐይለማሪያም ደሳለኝ ጥሪ ቀረበ

“ስራችንን ስንጀምር ማንም የከለከለን አካል አልነበረም”የቻይናውየአህዪች ኩባንያ የተማጽኖ ደብዳቤ

ኦነግ ለሰሞኑ የወገኖቻችን እልቂት መንስኤ የሆነው በጎረቤት ሶማሊያ የሚገኘው ማሰልጠኛ እንዲዘጋ ጠየቀ፣”ከግጭቱ ጀርባ ያሉ ሀይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ “የኦነግ ኮሚኒኬ

አርቲስት ቴዲ አፍሮ በህዝቡ ዘንድ የሚወደድ፤ በአገዛዙ ግን የሚጠላ ታላቅ ሰው ነው ተባለ

እና ሌሎችም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<