ዕድሜ ሲገፋ ውበትዎን መጠበቂያ 4 መንገዶች

Filed under: News Feature,ጤና |

የዕድሜ መግፋት የውበት መርገፊያ ምክንያት ሊሆን አይገባም፡፡ ይሄን መመሪያ ትክክል መሆኑን ያሳዩንና ዕድሜ ዘመናቸውን የነበራቸውን ውበት አስጠብቀው የዘለቁ ሰዎች አሉ፡፡ አሁኑኑ ታዲያ በሰውነት ላይ እርምጃ መውሰድ በመጀመር ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ማቆየት ይቻላል፡፡

ዓለም አቀፍ ሞዴል ሊያ ከበደ ግርማሞገስ ካላቸው ኢትዮጵያውያን ዝነኛ ሰዎች መካከል አንዷ ናት::

1. የፀሐይ ቃጠሎን መከላከል
ሰውነት ለፀሐይ ሲጋለጥ ለቆዳ ካንሰር እንደሚያመጣ እንዲሁም ቆዳንም እንደሚያበላሽ ይታመናል፡፡ ቆዳ በፀሐይ ሲጠቃ የቆዳ መበሳሳት፣ መጨማደድ፣ ለመፍታታት መቸገር ሁሉ ይከሰታል፡፡
ከፀሐይ የሚወጣን ጉዳት ታዲያ
– በዋናነት ከ4-8 ሰዓት ድረስ የሚኖረውን ጉልበተኛ ፀሐይ ውስጥ በተቻለ መጠን አለመንቀሳቀስ
– የፀሐይ መከላከያ ቅባቶችን መጠቀም
– ጥላ ወይም መከላከያ ልብሶችን መጠቀም ናቸው
2. አለማጨስ
ማጨስ በህይወት የመኖር ዕድል ብቻ አይደለም የሚቀንሰው መጥፎ ገጽታ እና መጥፎ ሽታንም ያላብሳል፡፡ እንዲሁም ቆዳንም በተለያዩ ደረጃዎች ይጎዳል፡፡
3. ብዙ ውሃ መጠጣት
ብዙ ውሃ መጠጣት ቆዳ እንደለሰለሰ እና እንደተፍታታ እንዲቆይ ይረዳዋል፡፡ ገፅታም የተሻለ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ በቀን ውስጥ ታዲያ 2 ሊትር ፈሳሽ ነገር መጠቀማችን መዘንጋት የለብንም፡፡
4. የጥሩ ቅርጽ ባለቤት መሆን
የጥሩ ቅርፅ ባለቤትነትን የአካል ብቃትን እንቅስቃሴን አዘውትሮ በመስራት፣ ዮጋን እና መሰል የትኩረት መሰብሰቢያ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የእራስ መተማመኑን ብሎም አካላዊ መስህቡን ማቆየት ይቻላል፡፡
5. በቂ ካልሲየም መውሰድ
ብዙ የካልስየም ንጥረ ነገር ያላቸውን ምግቦችና ፈሳሽ ነገሮች በመውሰድ እንዲሁ ውበትንና ጥንካሬ ማቆየት ይቻላል፡፡

zehabesha.com

One Response to ዕድሜ ሲገፋ ውበትዎን መጠበቂያ 4 መንገዶች

  1. We need Head and Brain Health and money we dont care about beauty

    Belay Zeleke
    September 19, 2017 at 3:15 pm
    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.