ከደህንነት ባለስልጣኑ ለአዜብ መስፍን የተሰጠ ምላሽ | የሰሜን ጎንደር ውጥረት | የእሬቻ በዓል | ቅማንት | ሳሞራ የኑስ | ቴዲ አፍሮ | ግብጽና አባይ ሌሎችም

Filed under: News Feature,ህብር ሬዲዮ,የዕለቱ ዜናዎች |

የህብር ሬዲዮ መስከረም 14 ቀን 2010 ፕሮግራም

<...የጉሊት ነጋዴዎች በላባቸው የሚያድሩ የዕለት ኑሯቸውን ለማሸነፍ የሚደክሙ እንጂ እንደነሱ የሕወሓት ባለስልጣናትና ቤተሰቦች አየር በአየር የሕዝብና የአገር ሀብት ዘርፈው በአንድ ቀን ጀምበር ሚሊየነርና ቢሊየነር አልሆኑም...አዜብም ሆነች ሌሎቹ የሕወሓት ባላስልጣናት ውሸት በመናገራቸው ልንገረም አይገባም ።ውሸት ባህላቸው ነው። ከዚህ ይልቅ በ1984 የአዜብ መስፍን ሙስና ይጣራ ተብሎ ኮሚቴ ተቋቁሞ ነበር። ከእነዚያ ኮሚቴዎች አንዱ ሲታሰር የቀሩት ግን ...> አቶ አያሌው መንገሻ የቀድሞው የደህነት ሹም ስለ አዜብ መስፍን የሰሞኑ <<ሀፍት የለኝም>> ማለት ጉዳይ ከህብር ጋር ካደረጉት ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ(ክፍል አንድ)

የሰማያዊና የመኢአድ የወቅቱ መሪዎች በቅርቡ ከአገር ቤት መጥተዋል። በፓርቲዎቹ ውስጥ የሚነሱትን ጉዳዮች ጨምሮ ስለ ውጭ አገር ጉዟቸው የሰጡትን ምላሽ ያካተትንበት በወቅታዊ ጉዳይ ከዶ/ር በዛብህ ደምሴና ከአቶ የሺዋስ አሰፋ ጋር ተወያይተናል (ክፍል አንድን ያድምጡት)

እንግሊዝ ሰሞኑን ከግዛቷ እንዲወጣ ያስገደድችው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ህይወቱን ያጣበት ሁናቴ እና የማህበረሰቡ ቅሬታ ሲዳሰስ(ልዩ ጥንቅር)
ማር እስከ ጧፍ ክሊፕ ፣በድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን በአገር ቤት መከልከል ላይ ቀረቡ ኣለም አቀፍ ተቃውሞዎች (ከጋዜጠና ክንፉ አሰፋ ጋር ያደረግነው ውይይት የመጨረሻ ክፍል)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የደህነት ባለስልጣኑ ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ቃለ መጠይቅ ምላሽ ሰጡ

በደብረ ታቦር ውጥረት መንገስ

በቅማንት ስም በተደረገ ሕዝበ ውሳኔ የተጭበረበረው የአንድ ቀበሌ ምርጫ አስነሳው ተቃውሞ

የሕወሓት/ኢህአዲግ በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ላይ ያወጣው ማስጠንቀቂያ

የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ጥያቄ

የኢህአዲጉ ጄ/ል በዓለም 10ሺህኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ማእረግ ተቀበሉ

የህንዱ ካራቱሪ ኩባንያ” ከኢትዩጵያ ከመውጣቴ በፊት ካሳ ይከፈለኝ”ሲል ለአቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጥያቄ አቀረበ

ግብጽና በአወዛጋቢው የህዳሴ ግድብ

እና ሌሎችም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<