የሕወሓት ደህንነት የኦህዴድ ባለስልጣናትን አስጠነቀቀ | መልቀቂያ ያስገቡ ባለስልጣናትን በሽምግልናም በማስፈራሪያም እያጣደፋቸው ነው

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

(ዘ-ሐበሻ) የኢህአዴግ አባል የሆነው ኦህዴድ አመራር ለሕወሃት አልታዘዝም ማለቱን ተከትሎ ድርጅቱ በደህንነቱ በኩል የኦህዴድ ባለስልጣናትን እያስፈራራ ሲሆን በሌላ በኩልም በሽምግልና ወጥሮ እንደያዛቸው የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

በኦሮሚያ ክልል ያለው የሕዝብ አልገዛም ባይነትና የኦነግ ባንዲራ በየተቃውሞውና ሕዝባዊ በዓላት ላይ እየታየ ባለበት በዚህ ወቅት የአባዱላ ገመዳን መልቀቂያ ማስገባት ተከትሎ ተጨማሪ የኦህዴድ አባል የሆኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባው ሕወሓት መልቀቂያ ያስገቡትን ባለስልጣናት ከኦነግ እና ከሙስና ጋር አያይዘን እንከሳችኋለን የሚል ማስፈራሪያ እየሰጠ ለማሸማቀቅ እየሞከረ ሲሆን በሌላ በኩልም የድርጅቱን የቆዩ ታጋዮችን ሽምግና በመላክ ጉዳዩን እንዲያረጋጉ እያስገደደ መሆኑን ገልጸውልናል::

የሕወሓት ደህንነት አባዱላ ገመዳ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በአማርኛና በኦሮሚኛ ቋንቋዎች የማረጋጊያ መግለጫ እንዲሰጡ አስገድዶ እንዳቀረባቸው የሚገልጹት ምንጮች እርሳቸውን ተከትሎ መልቀቂያ አስገብተው የነበሩ እንደ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመና ሌሎችንም ባለስልጣናት ጉዳያቸውን በማስፈራሪያና በሽምግልና እንዲስቡ እያስገደደ ነው ብለውናል::

በተያያዘ ዜና ሕብር ራድዮ በሁለት የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የግድያ ሙከራ መደረጉን ዘግቧል::

ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን እያሰባሰበች ለሕዝብ ታቀርባለች::

One Response to የሕወሓት ደህንነት የኦህዴድ ባለስልጣናትን አስጠነቀቀ | መልቀቂያ ያስገቡ ባለስልጣናትን በሽምግልናም በማስፈራሪያም እያጣደፋቸው ነው

  1. Are we gonna have the socalled federal govt without opdo?

    Zemen
    October 10, 2017 at 5:58 am
    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<