የብአዴን መደንገጥ ስለምንድን ነው?

Filed under: News Feature,ነፃ አስተያየቶች |

ከሙሉቀን ተስፋው

ከፍተኛ መደናገጥና እርስ በእርስ አለመተማመን የሰሞኑ የብአዴን ሰዎች መለያ ሆኗል፡፡ የአባ ዱላ ሥራ መልቀቅ ከኦሕዴድ ይልቅ ለብአዴን ራስ ምታት የሆነ ነው የሚመስለው፡፡ በረከት ስምኦን በራሱ ገለል በማለቱ የታችኛውና መካከለኛው የብአዴን አመራር ደስተኛ ሆኗል ሆኖም ግን የአባዱላ ጉዳይ ስለምን እንዳስደነገጣቸው ብዙም ግልጽ ባይሆንም አንዳንድ ጥርጣሬዎች ግን አሉ፡፡

እንደደረሰን መረጃ ከሆነ ብአዴንንና ደኢሕዴግን የነጠለ የሕወሓትና የኦሕዴድ ሰዎች ስብሰባ ከተደረገ በኋላ የአባ ዱላ መልቀቂያ ማስገባት የብአዴን ሰዎች የሚይዙትን የሚጨብጡትን አሳጥቷቸዋል፡፡ ሕወሓት ከኦሕዴድ ጋር ስብሰባ ካደረጉ በኋላ የብአዴን ሰዎች ስለስብሰባው ፍንጭ ለማግኘት ቢጥሩም አልተሳካላቸውም፡፡

 

አባ ዱላ የሕዝቤና የድርጅቴ ክብር ሲነካ ዝም ብዬ ማየት አልቻልኩም በማለት የተናገረው ለብዙዎች የተዋጠ ጉዳይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም አባ ዱላ የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳደር በነበረበት ጊዜ በርካታ ነገሮችን ቢያከናውንም የለየለት የመሬት ነጋዴ ሆኖ ነው የቆየው፡፡ አባ ዱላ ግላዊ ባሕሪውም ለመታዘዝ የሚመች ሰው እንደሆነ አብረውት የታገሉት ያውቃሉ፡፡ በሕወሓት የአሠራር ልምድ ደግሞ የሚያስጠይቅ ወንጀል ወይም ሙስና ያለበት ሰው እየታዘዘ ይቀጥላል እንጅ ክብሬ ተነካ ወዘተረፈ የመሳሰሉ ጥያቄዎችን አያነሳም፡፡ አባ ዱላ በግልጽ ተቃውሞውን እንዲያነሳ የተደረገበት ምክንያት አለ፤ ያ ምክንያት ግን ለብዙዎች ግልጽ አልተደረገም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<