ሰበር ዜና: የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ታመው ሆስፒታል ዋሉ * የምግብ መመረዝ ነው ተብሏል

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ ታመው ሆስፒታል መዋላቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ:: የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት አቶ ለማ ህመማቸው የምግብ መመረዝ ሳይሆን እንደማይቀር እየተነገረ ነው::

ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ በምግብ መመረዝ ሕይወታቸው ማለፉ አይዘነጋም::

ባለፈው ሳምንት በሁለት የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ላይ ከሕወሓት ደህንነቶች የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር በተለያዩ ሚዲያዎች መዘገቡ አይዘነጋም:::

አቶ ለማ መገርሳ በህመም ላይ ያሉ ሲሆን ምናልባትም ሕወሓት የሚቆጣጠራቸው ሚድያዎች የርሳቸውን የቆዩ ቭዲዮች በማሳየት የተለያዩ ልማታዊ ዜናዎችን እንደሚሰሩና ደህና መሆናቸውን ለማሳየት እንደሚሞክሩ ሲሉ እነዚሁ ምንጮች አስታውቀውናል::

የአቶ ለማ መገርሳን ጤንነት ምንጮቻችን ተከታትለው ያለውን ነገር እንደሚያሳውቁን ቃል ገብተውልናል – እንደደረሰን እናቀርበዋለን::

ብዙዎች በአድናቆት ያዩትና የሕወሃት ሰዎችን ያስቆጣው የለማ መገርሳ የሰሞኑ ንግግር እዚህ ይገኛል – ይጫኑት::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦህዴድ “ተወዳጁ እና እጅግ የተከበሩት የኦሮሚያ ብዬራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሣ የት ጠፉ?”በሚል ር ዕስ በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን አስነብቧል::

” ተወዳጁ እና እጅግ የተከበሩት የኦሮሚያ ብዬራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሣ የት ጠፉ?
እያላችሁ ከልብ በመነጨ የመሳሳት ስሜት ስትጠይቁን ለነበራችሁ ወዳጆቻችን ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የኦህደድ ማዕከላዊ ጽ/ቤት ሃላፊ ክቡር ፕሬዝዳንታችን ለስራ ጉዳይ ወደ ውጭ እንደሄዱና ምንም ችግር እንዳልገጠማቸው የተናገሩትን ወደናንተ ማድረሣችን ይታወሳል።
ዛሬ ደግሞ ተወዳጁ መሪ የሄዱበትን ስራ አጠናቀው ፊንፊኔ ገብተዋል።
የኦሮሚያ ተሃድሶ መሪ እና የጀመርነው ሁሉን አቀፍ ለውጥ መሀንዲስ ክቡር አቶ ለማ እንኳን ደህና መጡ ። እንኳንም ደስ አለን!።”

ይህ ባልተለመደ መልኩ የወጣው የኦህዴድ ጽሁፍ አነጋጋሪ ሆኗል:: ከበስተጀርባው ከባድ ነገር እንዳለ የሚያሳይ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በርክተዋል:::

6 Responses to ሰበር ዜና: የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ታመው ሆስፒታል ዋሉ * የምግብ መመረዝ ነው ተብሏል

 1. Lemma is part of EPRDF oppersive machine. What we need is a total regime change not Gemeda replace my lemma. OPDF is still part of TPLF/Woayane. We do not want cosmetic change. TPLF and its party need to go. DOWN DOWN WOYANE.

  Teka Hebret
  October 16, 2017 at 2:12 pm
  Reply

 2. Please
  tag
  me
  when
  u
  post,u
  give
  interesting
  info.i
  like
  ze
  habesha

  Mule
  October 16, 2017 at 3:25 pm
  Reply

 3. አይ ለማ! ለማ! ለማ!
  ጭራሽ የማይታማ!
  ለህዝባችን የቆመ እንደ ማማ
  ኧረ! ለሆስፒታል ታማ??
  በሽታም አይነካውም አትማ!!!
  ያገር ልጅ ሃገር በቀል
  ለማ መገርሳ የወንዝ ቅጠል
  በሽታም አይነካውም ዝም በል!!1

  Mulugeta Andargie
  October 16, 2017 at 7:13 pm
  Reply

 4. STRONG MEN FINALY CHANGE THEMSELVES IN TO DICTATORS .
  ETHIOPIA NEEDS SYSTEM NOT PERSONALITY CULT .

  ANY ONE WHO AGGRANDIZES ON SELF BEYOND SYSTEM MUST NOT BE ALLOWED AT ALL .

  WE NEED VIABLE FEDERAL SYSTEM THAT WORKES REGARDLESS OF WHO THE PRESIDENT OR PM IS .

  ONLY FOOLS LOVE TO WORSHIP INDIVIDUALS !
  THE WISE WORK ON UNSHAKALE SYSTEM REGARDLESS OF WHO IS ELECTED !!

  I AM A BIG FAN OF LEMMA THOUGH !!! BENEFIT YOUR PEOPLE AND THAT WILL DRY THE LIE MACHINE OF TOXIC DIASPORA

  nana
  October 17, 2017 at 8:39 am
  Reply

 5. Nefsachewun Yimar. ye temeteze yemote malet newu. kaltemerezu yichin mastawesha serizuling.

  Selam LeAlem
  October 18, 2017 at 1:20 pm
  Reply

 6. እኛ ኢትዮጵያውያን አሽቃባጭ፣አለቅላቂ፣ተልመጥማጭ….ወዘተን ባህሪ እንደ ኩታ ተላብሰናል።ይህ ፍፁም ተልካሻነት ነው።በራስ የመተማመን አቅምን ያኮላሻል።
  አቶ ለማ ምን ሰርተዋል ይህ ሁሉ አድናቆት።ደግሞም እኮ ቢሰራ ለራሱ ለኑሮው ነው።ግን ምን ተሰራ??????አንተዛዘብ።

  ጋምብሬ
  October 19, 2017 at 3:23 am
  Reply

Leave a Reply to ጋምብሬ Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.