በቤኒሻንጉል ልዩ ኃይል ፖሊስ እገዛ ከ50 በላይ ዐማሮች ሲገደሉ ወደ 400 የሚሆኑ ቤቶች ተቃጥለዋል፤

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

(ከአዘጋጁ: ይህ የቤንሻንጉል በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው እልቂት ከመከሰቱ አስቀድሞ ከአራት ቀን በፊት ሕወሓት በተለያዩ ቦታዎች የዘር ግጭቶችን ለማስነሳት እየሰራ መሆኑንና አንዱ ቦታም ቤንሻንጉል መሆኑን ከደህነንት የደረሰንን መረጃ በሰበር ዜና ዘ-ሐበሻ ላይ ማቅረባችን አይዘነጋም:: ሰበር መረጃውን ላላያችሁት እዚህ ጋር ይጫኑ)

ከሙሉቀን ተስፋው

ችግሩ የተፈጠረበት ቦታ- ከማሽ ዞን፣ በሎጅጋንፎይ ወረዳ፣ በሎደዴሳ ቀበሌ

ቀን፤ ከጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ

መነሻ ምክንያት፤ የክልሉ ልዩ ኃይልና በወረዳው አመራሮች አስተባባሪነት የዐማሮችን ንብረት መዝረፍ እየተለመደ እንደመጣና በዚህም ምክንያት አልፎ አልፎ ግጭት ይፈጠር ነበር፡፡ በሎንደዴሳ ቀበሌ የዐማራ ንብረት ለማውደም የሄደ የጉምዝ ተወላጅና ባለንብረቱ ሰው መካከል ጠብ ተነሳ፡፡ በዚህ መካከል ሊዘርፍ የሄደው ሰው ይሞታል፡፡ ይህን ጊዜ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ምትኩ ኖኖ እና ወ/ሮ ጥሩነሽ እንዴት ዐማራ የእኛን ሰው ይገድላል! በሚል ቁጭት የልዩ ኃይል ፖሊሱን በማስተባበር በዐማሮች ላይ ጀምላ ጥቃት መድረስ ጀመረ፡፡

ውጤቱ- በቀበሌው ከ2000 በላይ አባውራዎች ሲኖሩ አብዛኛዎቹ ከሳር የተሠሩ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲቃጠሉ የቆርቆሮ ጣራ ያላቸው ብቻ ናቸው የተረፉት፡፡ በዚህም ከ400 በላይ የሚሆኑ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡

የሰው ሕይወት፤ የተለያዩ ሰዎች የተለያየ ቁጥር ቢናገሩም እስካሁን ከ50 በላይ ሰው እንዳለቀ ያነጋገርናቸው ገልጸውልናል፡፡ አስከሬን በየቦታው ወዳድቆ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን አልተነሳም፡፡ አስከሬን ለማንሳት የሄዱ ሰዎች ተከልክለዋል፡፡ በጅምላ በጉድጓድ የተከማቸ አስከሬንም እንዳለ ተናግረዋል፡፡ መትረፍ የሚችሉ ሰዎች ከአስከሬን ጋር አብረው በአንድ ጉድጓድ በመጠራቀማቸው ሕይወታቸው እንዳለፈም ተናግረዋል፡፡ አቶ አልማው የተባለ የቀበሌው ነዋሪ በሕይወት ከአስከሬን ጋር ወደ ጉድጓድ በመጣሉ አብሮ ሊሞት እንደቻለ ምስክሮች ገልጸዋል፡፡

ከ300 የሚበልጡ ሕጻናትና ሴቶች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም፡፡ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ወደ አካባቢው የደረሰ ቢሆንም የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ምትኩ ኖኖ ከእኛ አቅም በላይ አልሆነም እያለ እየመለሰ እንደሆነም ነግረውናል፡፡

ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አስከሬኖች አልተነሱም፡፡ የሞቱት ሰዎች ቁጥርም ሊያሻቅብ እንደሚችል ነግረውናል፡፡

አሁን በደረሰ መረጃ

እስካሁን 17 አስሬኖች ተነስተልዋል
~ሜዳ ላይ 7
~ከውኃ ውስጥ የተጨመሩ 2
~ጉድጓድ የተጨመሩ 3
~ ጥሻ ውስጥ 5 አስከሬኖች ተለቅሟል።
የሚከተሉትን ሰዎች አስከሬን አንድ ሰው የለቀማቸው ናቸው።
1. 1 ምነችል ሙሉ
2. ይቻላል ወርቄ
3. ዘላለም ይከበር
4. አትርሳው ቻሌ
5. ጌታቸው እንይ
6. አንዱአለም
7. አልማው

3 Responses to በቤኒሻንጉል ልዩ ኃይል ፖሊስ እገዛ ከ50 በላይ ዐማሮች ሲገደሉ ወደ 400 የሚሆኑ ቤቶች ተቃጥለዋል፤

 1. How it could be again, again and again?

  Libargie Demelash
  October 28, 2017 at 10:38 am
  Reply

 2. Have a people of Amhara leader?

  Libargie Demelash
  October 28, 2017 at 10:43 am
  Reply

  • Leaders? No, Amhara has got no leaders but naive followers! Amhara elites are too busy talking about the non existance Ethiopian unity while their poor people are been displaced, kicked out, and massacred in every part of the country.

   Poor Amhara!

   Danny
   October 29, 2017 at 12:00 am
   Reply

Leave a Reply to Danny Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<