የአዲስ አበባ አስተዳደር የእውቁን ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን የሙዚቃ ኮንሰርት አገደ

Filed under: News Feature,ኪነ-ጥበባዊ ዜና,የዕለቱ ዜናዎች |

(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ ጅራ የተሰኘ ነጠላ ዜማውን የለቀቀውና በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ምርጥ ድምጻውያን መካከል በቀዳሚዎቹ መካከል ስሙ የሚጠራው ሃጫሉ ሁንዴሳ በአዲስ አበባ ሊያደርገው የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት ልክ እንደ ቴዲ አፍሮ መታገዱ ተሰማ::

በአዲስ አበባ ባለፉት 2 ወራት ውስጥ ሁለት ትላልቅ ኮንሰርቶች የተደረጉ ሲሆን ልክ እንደ ቴዲ አፍሮ ሁሉ የሃጫሉ ሁንዴሳም ኮንሰርት መታገዱ እያነጋገረ ነው::

ከሃገር ቤት የሚተላለፈው ኢትዮፒካሊንክ የራድዮ ፕሮግራም በዝርዝር የዘገበውን ይመልከቱት::

4 Responses to የአዲስ አበባ አስተዳደር የእውቁን ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን የሙዚቃ ኮንሰርት አገደ

 1. አንዳንዴ ሁሉንም ነገር መቃወም አለብን ወይ እላለሁ።

  ምድረ ገንጣይ አስገጣይ መደገፍ አለብን እንዴ?
  የብሄር ብሄረሰብ ብሄረተኛ የሚባሉት አላማቸው የተፈጥሮ ሃብት ሽሚያ ነው።
  የተፈጥሮ ሃብትና መሬትን ለመቆራመት ከምሯሯጥ ጋር ሁሉ እንጨፍር?

  ኢትዮጵያ የሚሉት ከተከለከሉ እነዝህ በብሄር የሚጨፍሩት መከልከላቸው ያስደስታል እንጂ!

  Misrak
  December 3, 2017 at 3:37 am
  Reply

  • Misrak እንደ አንቺ ያለ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ናቸው ሕዝብን ወደመገንጠል ጥያቄ እንዲያመራ የሚገፋፉት!!!

   Add Adama
   December 3, 2017 at 6:45 am
   Reply

   • አስቸጋሪው ጉዳይ ብሄር የሚባለው አንድ አይነት ህዝብና አንድ አይነት ፍላጎት ያለው ተብሎ ሲቀርብ ነው። ብሄር ግን በተለያየ መልኩ የተከፋፈለ ማህበረስብ – በክልልና ባልተመጣጠነ የሃብት ክፍፍል በተለይም በመደብ የተከፋፈለ ነው። የግጭቶች መነሻ የሰላም አለመኖር ምክንያትም ይኽው የሃብት ክፍፍል ስለሆነ መሸፋፈኑ ጊዜያዊ ጥቅም ያስገኛል እንጂ ዘላቂ አይሆንም በተለይ እንደ አገራችን የብሄሮች ስብጥር በጣም የተዛባ በሆነበት ምድር። ደግሞ ኦሮሞ እሱ በፈጠራት ኢትዮጵያ እንዴት ብሎ ነው የሚገነጠለው?

    Misrak
    December 6, 2017 at 11:10 am
    Reply

 2. megantalim bihonen hige mengistawi mafti new, yeoromo hizib gin lerasu yeganabawun agar tito yemegantali hasab yelewum. yehachulunim hone yetedy konsert maninim masdaset alneberebetim. oromo hizib befiqir be tolerance yetawoke talaq ye east Africa hizib new. inde mitasibut aydelem.

  bek
  December 4, 2017 at 8:28 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.