በአዲስ አበባ ነገ ሊደረግ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የቡና ጨዋታ በጸጥታ ስጋት ተራዘመ | ሌሎች ሁለት ጨዋታዎችም ተራዝመዋል

Filed under: News Feature,ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች |


(ዘ-ሐበሻ) በሕዝባዊው አመጽ የተነሳ በጸጥታ ስጋት ውስጥ የሚገኘው የአድዋው ሕወሓት መራሹ መንግስት ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊደረግ የነበረው የመከላከያና የሃዋሳ ከነማ ፣ የኢትዮ-ኤሌክትሪክና የጅማ አባጅፋር እንዲሁም ነገ እሁድ ሊደረግ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ግጥሚያ ጨዋታው የሚደረግበት ቀን እንዲራዘም አደረገ::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደዘገቡት በአዲስ አበባ ከተማ በጸጥታ ስጋት ውስጥ የገባው የአድዋው መንግስት በሥራ ቀናት ቢደረጉ ብዙ ሰው ስታዲየም ላይገባ ይችላል በሚል ቅዳሜና እሁድ የሚደረጉት ጨዋታዎች ወደ ሰኞና ማክሰኞ ተዘዋውረዋል:

በዚህም መሠረት ዛሬ ቅዳሜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊደረግ የነበረው የመከላከያና የሃዋሳ ከነማ እንዲሁም የኢትዮ-ኤሌክትሪክና የጅማ አባጅፋር ጨዋታዎች ወደ ሰኞ ታህሳስ 2 ሲዘዋወሩ ነገ እሁድ ሊደረግ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ወደ ማክሰኞ ታህሳስ 3 መዘዋወሩን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል::

የአድዋው ሕወሓት መንግስት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በጸጥታ ስጋቶች ተወጥሮ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ሲዘገብ መቆየቱ አይዘነጋም::

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.