ሃጫሉ ሁንዴሳ ታሪክ ሠራ

Filed under: News Feature,ኪነ-ጥበባዊ ዜና,የዕለቱ ዜናዎች |

(ዘ-ሐበሻ) ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉትን ወገኖች ለመርዳት በኦሮሞ ሙዚቀኞች ማህበር የተዘጋጀው “ወገን ለወገን” የሙዚቃ ኮንሰርት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ሲደረግ የግሉን ኮንሰርት በጊዮን ሆቴል እንዳያካሂድ የተከለከለው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ መድረክ ላይ የሕዝብን ብሶት በሙዚቃው ሲያሰማ ዋለ::

በቃሊቲና ቂሊንጦና እስር ቤት እየማቀቁ ያሉትን የሕሊና እስረኞች የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ አባዱላ ገመዳ ፊት ለፊት በተቀመጡበት በዘፈኑ አስታውሷቸዋል::

ሃጫሉ በኦሮሚኛ ዘፈኑ መድረክ ላይ ያቀረበው ወደ አማርኛ ሲተረጎም:-

“ሸልል ሸልል ይሉኛል ምኑን ልሸልል እኔ
ቂልንጦ አይደለም ወይ…
ቃሊቲ አይደለም ወይ….
ከርቸሌ አይደለም ወይ…
ሸልሎ የማይጠግበዉ የሚገኝ ወገኔ፡፡

የፈረሶቻችንን ዝና፣
የጀግኖቻችንን ዝና
አድዋ መቀሌ ይንገረና!
አብሮ መኖር ይሻል ብለን…
መከባበር ይሻል ብለን…
እስከዛሬ ታግሰናል…
ከእንግዲህ ግን ይበቃናል”

Geerar geerar naan jeettu
Maalan geerara
Dhiri geerare hinqufne
Hidhaa Qaaliti jira
Dhiri geerare hinqufne
Hidhaa Qilinxxo jira
Dhiri geerare hinqufne
Hidhaa Karchalle (Karchalle Ambo) jira

ብዙዎች “ታሪክ ሠራ” እያሉ በአድናቆት የተመለከቱትን የሃጫሉን የዛሬ የመድረክ ውሎ ይመልከቱት::

7 Responses to ሃጫሉ ሁንዴሳ ታሪክ ሠራ

 1. ጎበዝ። አሱ ታሪክ የሰራ ይመስላል እኔ የሚታየኝ ኣደጋ ነው። የህዝቡ ወኔ ብሔረተኝነትን ያተኮረ ነው አኮ።
  ዓማራም ጉራገም ዎላዪታም ቲግረም ኮንሶም ጋምበላም

  ኣብረን ነው የተበደልነው። የውቀጠን ወያኔ ነው።

  Michael zenebe
  December 9, 2017 at 5:52 pm
  Reply

  • antes min Sera ?, sewun kemeweks esti biyans arungade bicha keyun sendek alaman be meskel adebaby sikel Wendi kehonk anteh shintam, esti biyans wedeh hageri gibana tekawem ,hachalu mech gosa leyito tenagere hulachin tegodtenal aleh enj proud of hache,gedal giba midra shintam weregna

   eyita
   December 12, 2017 at 7:24 am
   Reply

 2. Semtehal wedi megersa..semtehal we do Gemeda..Thats it.Magnificient Hachalu my man! Geletumma..

  Seare
  December 9, 2017 at 10:07 pm
  Reply

 3. ye eske zarew adega altayehim neber ? sile rasu, sile oromo, sile hizbu new … ha caalu yalew…. sile lelaw minim alalem

  amaraw
  December 10, 2017 at 12:35 am
  Reply

 4. አጫሉ ደፋርና የተሰማውን የሚገልፅ ዘፋኝ ነው።አምቦ ሁለተኛ ደረጃ ሲማር ለእስር ሁሉ ተዳርጎ ነበር።በወቅቱ የወጣለት አፍቃሪ ኦነግ ነበር።እድሜ አስተምሮት ኢትዮጵያዊነትን ተላብሷል።እነ ፕሮ.ሕዝቅዔል እና ጁሀር መሀመድ ከአጫሉ መማር አለባቸው።አጫሉ እድሜ ይስጥህ ማለት እፈልጋለሁ።እስኪ ሙሉ ዘፈኑን ተርጉሙልን።ብራቮ አጫሉ ሁንዴሳ የአምቦ 06 ልጅ።

  ጋምብሬ
  December 10, 2017 at 1:23 am
  Reply

 5. እኔ ያልግባኝ ህዝቡ እንዴት ቢሆንልህ ነበር ብሄርተኝነት አላሳየም የምትለው ?ተክዞ መቀመጥ ነበረበት ? እስቲ ንገረኝ

  jema
  December 10, 2017 at 10:34 am
  Reply

 6. Narrow minded, un civilized ,inferiority complex riddend , silly boy

  RACIST RAT

  the lion is awake
  December 11, 2017 at 11:46 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<