21ኛው በአውስትራሊያ የኢትዮጲያውያን የስፖርትና የባህል ቶርናመንት ከዲሴምበር 26 – 30 ባሉት ቀናት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል

Filed under: News Feature,ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች |

21ኛው በአውስትራሊያ የኢትዮጲያውያን የስፖርትና የባህል ቶርናመንት ከ December 26 እስከ 30 ባሉት ቀናት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል።
በዚህ ታላቅ የኢትዮጲያዊያን ሳምንት፣
ባለብዙ ቀለሙ ባህላችን በስፋት ይንፀባረቃል!
አንድነትና ፍቅር በስፋት ይቀነቀናል!
ኢትዮጲያዊነት ይዜማል ይንቆረቆራል!
የነፃነታችን እና የኩራታችን ምልክት የሆነችው ሰንደቅ አላማችን ከፍ ብላ ትውለበለባለች!

ከቪቶሪያ፣ ከ ኒውሳውዌልስ፣ ከኩዊንስላንድ፣ ከሳውዝ አውስትራሊያ እና ከታስማኒያ በሚወከሉ በርካታ ቡድኖች መሀል የእግር ኳስ ውድድሮች የሚደረጉ ሲሆን December 28 በሚከበረው የኢትዮጲያ ቀን ድል ያለ የሙዚቃ ዝግጅት፣ የግጥም ውድድር፣ መነባንቦች እንዲሁም የተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶች ይቀርባሉ። በመዝጊያው እለትም ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት ተዘጋጅቷል።

ስለሆነም ሜልበርንና አካባቢዋ የምትገኙ ኢትዮጲያዊያን በሙሉ የዚህ ታላቅ ቶርናመት ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ በማክበር ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የዝግጅቱ ቦታ: 19 Carrington Dr
Albion
ሲሆን ዝግጅቱ በሁሉም ቀናት ከጠዋቱ 10am እስከ ምሽቱ 10 Pm ይሆናል።

በቪክቶሪያ የኢትዮጲያውያን ማህበረሰብ ማህበር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<