መዝናኛ: አርቲስት ትንሳኤ ብርሃኔ (አቡሽ) በሰይፉ ሾው የደበቃት ምስጢር

Filed under: News Feature,ኪነ-ጥበባዊ ዜና |

በዘመን ድራማ ነባራዊ እውነታን የሚያንጸባርቅ አንድ ትእይንተ-ገቢር አለ። ወጣት የምታሳደድው አሮጊት ወይንም አሮጊት እያሳደደ የሚቀፍል ወጣት። ብቻ ሁለቱም ይፈላለጋሉ። እስዋ ለዝሙት ስትፈልገው፣ እሱ ደግሞ ለገንዘብ ይፈልጋታል። አሮጊትዋ ወሽማው ጥርስዋን ከብርጭቆ አውጥታ ድድዋ ላይ ስታጠልቀው የሚያሳይ አንድ ገቢር አለ። ወጣቱ አቡሽ ይህንን አይቶ ይጸየፍና ይሸሻታል።

የምናቡ አለም ትወና የአቡሽ ካራክተር ውስጡ እንደገባና እንደተዋሃደው በቃለ-ምልልሱ ተናግሯል አርቲስት ትንሳኤ። በኪነ ጥበብ ይህ መዋሃድ አንድ መልካም ነገር ነው።

አርቲስት ትንሳኤ ባህር ተሻግሮ ሆላንድ ድረስ የመጣው አሮጊት አግብቶ መሆኑ፣ ይህ ወጣት የምናቡን አለም በገሃዱ አለም ላይም እንደኖረው አሳይቶናል።

“ዋናው ቻፓ ነው” ብሎናል የዘመን ድራማው ተዋናይ፣ ወጣት ትንሳኤ ብርሃኔ። ይህ ልጅ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር በኢ.ቢ.ኤስ. የነበረው ቆይታ ድንቅ ነው። በቃለ-ምልልሱም ሆነ በድራማ ስራው መደነቅ ቢያንሰው እንጂ አይበዛበትም።

ትንሽ ቅር የሚያሰኘው ስለ ሆላንድዋ ሚስቱ ጉዳይ የተናገረው ነው። ሆላንድን ሄጄ ሶስት ወር ቆይቼ መጣሁ። ካለ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰበትን እንደ ምክንያት ያቀረበው የወንድ ለወንድ መሳሳም፣ የሴት ለሴት ጋብቻና የሃሺሹ ነገር ነው።

ይህ ጉዳይ ባይነሳበት ይሻል እንደነበር ምላሹ ያሳብቃል። “ምን ያደርጋል… ተወው” እያለ ጥያቄዋን ዘልሎ ለማለፍም ፈልጎ፤ ግን አልቻለም። ሰይፉም ቢሆን ረገጥ አርጎ ይጠይቅ እንጂ መረጃው በእጁ የለም። እንደ ጋዘጠኛ የቤት ስራውን አስቀድሞ የሰራ አይመስልም። ወይንም ማንሳት ሳይፈልግ ቀርቶ ይሆናል።

ሰየታደሉ ሰዎች ህልማቸውን ይኖራሉ። ይህ ልጅ ግን የምናቡን ህይወት ነበር በሆላንድ የኖረው። በዘመን ድራማ፣ የአቡሽ ገጸ-ባህሪ ሃብታም አሮጊቶችን እያሳድደ፣ በዚያ የሚተዳደር የሹገር ማሚን ካራክተር የሚጫወት ልጅ ነው።

ገና ከጅምሩ “ድራማው ላይ ሴት አሳዳጅ ስለሆንክ ፣ ሚስቴ ፊት አላቆምህም” ብሎት ነበር ሰይፉ ፋንታሁን። ለጫወታ አለ እንጂ ጉዳዩ እንደዚያ አይደለም። ልጁ ማንንም ሴት ሳይሆን ሃብታም አሮጊቶችን ነው የሚያሳድደው።

የአርባ ቀን እድል ሆኖ፣ በምናቡ አለም የሚተውነውን ኑሮ በገሃዱ አለም ይኖር ነበር – በአጭር አማርኛ። ይህ ደግሞ በአጋጣሚ የተከሰተ ላለመሆኑ ማረጋገጫው ራሱ የተናገረው “የቻፓ” ጉዳይ ነው።

የሆላንድዋ ሚስቱ ያለማጋነን የአያቱን እድሜ የተሸከመች አዛውንት ነበረች። እንዳለው ቻፓ አስቦ ካልሆነ በስተቀር እንኳን ለትዳር አብሮ ለመቀመጥ የምትታሰብ ሲትዮ አደለችም። በድራማው ላይ እንደሚታየው ጥርስዋን አውልቃ በብርጭቆ ስታስቀምጥ የተመለከታት ሹገር ማሚው፣ ዘግንናው ሲያመልጥ ይታያል። ድራማው ላይ ላይ ሴትየዋ ምንም እንኳን አስቀያሚ ብትሆንም ቻፓ አላት።

በገሃዱ አለም የገጠመው ግን ከሁለት ያጣሽ ጎመን ነው። የሆላንድዋ የሰማንያ ሚስቱ ቻፓም የላት፣ መልክም የላት። በቅጡ ቤት እንኳን የሌላት የራስታ ተከታይ ፣ የጎዳና ተዳዳሪ አይነት አሮጊት ነበረች። በመንግስት ጡረታ ስለምትተዳደር ባል ከውጭ አግብታ ማምጣት እንኳን አትችልም። አቡሽን አግብታ ለማምጣት ቤልጂየም መሄድና መመዝገብ ነበረባት።

ትንሳኤ እዚህ ተሸውዷል። ሆላንድ ሃገር ሲመጣ የጠበቀውን አላገኘም። ወፍ የለም፣ ቻፓ የለም። አፈርኩብሽ ብሎ እንዳመለጠ ግልጽ ነው። መሸወዱን ግን ባይደብቅ ጥሩ ነበር። ቢያንስ ለሌሎች ትምህርት ይሆናል። ነገሩን ግልጽ ማድረግ ሊያሳፍር ይችላል። ያልሆኑትን ሆኖ ከመታያት ግን ከዚያ ይበልታል። ከሱ ስህተት መቶዎች ይማሩ ነበር።

በቃለ-መጠይቁ ላይ ራስን ዝቅ ማድረግና ዝቅ ብሎ የመስራት ስብዕና ይታይበት ነበር። ታዋቂ ሆኖ ግን በቀድሞ ስራው እንደሚኮራበት መነገሩ ይህንን ስብዕናውን ይመሰክራል። በነካ እጁ በሰማንያ ያገባት ሴትዮ የገጠመውን ጉድ ለሕዝብ ቢያጨውት ኖሮ ምንም አልነበረም።

ከጥበብ ሰው ወይንም ከያኒ ፎግሮ የሚኖር ማለት አይደለም። ወይንም ዝም ብሎ የሚበጠረቅ ሳይሆን፣ የትውልድ ገጸበረከት ነው። ትውልዱ ከሱ ብዙ ይማራል። ስለዚህ ለ እውነት የቆመ፣ አስተማሪ እና ታላቅ ሰብእና ያለው መሆን ይጠበቅበታል።

ለመኖርያ ወረቀት ሲባል በአውሮፓ አሮጊት ማግባት የተለመደ ነው። የአውሮፓ አሮጊቶች በተለይ ኢትዮጵያውያንን ማግባት ይመርጣሉ። ከሌሎች ጋር ሲነጸጸሩ ጨዋ እና ታማኝ ናቸው። ዜግነት እስኪያገኙ አሮጊት ሚስታቸውን በመንከባከብ ወደር የላቸውም። ዜግነት ያገኙ ቀን ግን የሉም። የሌላ ሃገር ተወላጆች ሲትዮዋ እስክትሞት፣ ውርስ ሲጠብቁ ኢትዮጵያውያን ግን ከእስር እንደተፈታ ያመልጣሉ።

ነገርን ነገር ያነሳዋልና በበጋ ወራት አንዱ ወጣት አሮጊት ሚስቱን ጋር ከሱፐር ማርኬት እቃ ገስቶ ሲመለስ፣ አሮጊትዋ አጥወልውሏት ወደቀች። ሙቀቱ እና ውብቀቱ ሲበረታ የሚሞቱ አሮጊቶች ቁጥር ቀላል አይደለም። ታዲያ ልጁ ምን እያለ ቢጮህ ጥሩ ነው?

ያገር ያለ ፓስፖርቴ፣ ፓስፖርቴ ወደቀች..

አይፈረድበትም። ምን ያድርግ። ስምት አመት ጠብቆ አሮጊትዋ ብትሞትበት የፓስፖርቱም ነገር አበቃ! እንደገና ሌላ አሮጊት ይዞ ሊፈጋ?

የአቡሽ ግን ውርስም ቅርስም የሌላት የኔ ብጤ ስለነበረች በግዜ አመለጠ። እዚህ ላይ ጥሩ ቢያደግግም ግን መድረክ ሲያገኝ ግን እውነቱን ቢናገር መልካም ነው።

One Response to መዝናኛ: አርቲስት ትንሳኤ ብርሃኔ (አቡሽ) በሰይፉ ሾው የደበቃት ምስጢር

  1. አንተህ እራሱ ቅናት አስመሰለብህ ወይ ደሞ ሚስትህ ነበረች ለዛ ነው እንጂ አሁን እዚህ ላይ ምን አምቦጣረቀህ ምን አገኘህ እስቲ አሁን ሰይፉም ቀደም ብሎት ሰምቶም ሊሆን ይችል ይሆናል ብለህ ነበር ከሆነም ላሽ ብሎት ይሆናል ባልሰማ ሙድ አንተ ግን ተበጠረቅ በጥራቃ ።

    Sahlu Tedros
    January 5, 2018 at 7:49 pm
    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<