ሳምሶን ማሞ እና ሰላም ተስፋዬ

Filed under: News Feature,ኪነ-ጥበባዊ ዜና |

[ቴዲ አትላንታ]

ሳምሶን ማሞ የማስታወቂያ ባለሙያ ነው፣ አንድ አርቲስት ቁጭ አድርጎ ቃለመጠይቅ ለማድረግ ግን “ሙያው” መሆኑን አላውቅም። እርግጥ ዛሬ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ነገር፣ ዕድሜ ለሞላው ኤፍ ኤም ሬዲዮና ለቴሌቪዥን ሾው ብዛት ይሁን እንጂ፣ ሚዛን ተቀምጦ፣ በመስፈርት የሚገባበት ባለመሆኑ የሚጠይቀው ነገር ድፍረት ብቻ ነው። ከድፍረት ጋር በሆነ ነገር ድምጽን በሬዲዮ ማሰማት! – በማስታወቂያም ቢሆን። ለዚህ ነው ማስታወቂያ ሲሰሩ ድምጻቸውን የምንሰማቸው ብዙዎች፣ ብዙም ሳይቆዩ “የራሳቸው ሾው” የሚኖራቸው።

ለማንኛውም ሳምሶን ማሞ ሰላም ተስፋዬን ሲጠይቃት፣ ምን እንደሚጠይቃት ያሰበም አይመስልም። ሃሳቡ ሁሉ የመጨረሻው “ሰርፕራይዝ” ላይ በመሆኑ ከዚያ በፊት የፈለገውን የመጠየቅ መብት እንዳለውም ሳይቆጥር አልቀረም።

ጥያቄና መልሱ ራሱ ፣ የፖሊስ ምርመራ ነው የሚመስለው። እሷም በጣም ተቆጥባ ነበር የምትመልሰው። ስለምግብ መስራት ችሎታዋ በማፋጠጥ ነው የጀመረው፣ እችላለሁ ብትለውም ፣ ደጋግሞ ደጋግሞ ርግጠኛ ነሽ? ዓይነት ነገር …………. ሊያገባት ያሰበ ሁሉ አስመስለው። ወይ አንደኛውን እዚያው ሽንኩርትና በርበሬ አምጥቶ ሰርተሽ አሳዩኝ ቢላት ሳይሻላት አይቀርም ነበር።

ቀጠለና፣ ዕድሜሽ ስንት ነው? አለ። ዕድሜዋን የግድ ተመልካቹ ማወቅ ያለበት ሁኔታ አልተፈጠረም። ፍጥጫው ምንድነው? ዝም ስትለው ቀጠለና ..”ዕድሜሽን የጠየቅኩሽ ብዙ ፊልም በተለያየ ዓይነት ገጸባህርይ ስለምትሰሪ ያን ሁሉ እንዴት አወቅሽው ብዬ ነው” ሲል አከለበት። ሴተኛ አዳሪ ሆኖ ለመስራት ፣ በውኑ ዓለም ሴተኛ አዳሪ መሆንንኮ አይጠይቅም። ሰካራም ሆኖ ለመተወን “የግድ ጠጥቶ ማወቅ” ግዴታ አይደለም። ወታደር ሆኖ ለመተወን፣ በውኑ ዓለም የግዴታ ወታደር መሆንን አይጠቅይም። ሳሚ እንደዚያ ያሰበ ነው የሚመስለው።

የፊልም ሙያዋን ለማድነቅ ፈለገና የራሱን አስተያየት ሰጥቶ እንደማለፍ ..”..”ለሙያው የተፈጠርሽ (ቦርን አርቲስት) ነሽ ብዬ አስባለሁ፣ ነሽ እንዴ?” ብሎ ቁጭ። እኔማ “አዎ – እናቴ ሆድ ውስጥም እተውን ነበር” ብትለው ደስ ይለኝ ነበር።

ስለ ቤተሰቧ ጠየቃት… ካለመዘጋጀቱ የተነሳ “አባትሽ ደህና ናቸው?” ዓይነት ጥያቄ ነበር ይዞ የመጣው፣ “አባቴ እንኳን በህይወት የለም” አለችው። “ አልደነገጠም .. ኦ . ይቅርታም (sorry) አላለም ..፣ ጭራሽ “እሺ” ብሎ ወደሌላ ጥያቄ ….

ያለ ማስተዛዘን .. ስለ ዝናዋ ቀጠለ. … ጠያቂ መሆኑን ረስቶ ብሶቱን አመጣና “አንዳንዶች ዝነኛ ሲሆኑ አናታችን ላይ ይወጣሉ፣ .. [አትዋሺ ዓይነት ነገር ጨመረበትና] .. ብዙ ጉድ አለ ..፣ ሰው ሲያዩ በጉራ የሚሸሹ ሁሉ አሉ ፣….” ብሎ ከተነተነ በኋላ “አንቺስ?”

“እኔም?” እንድትለው ጠብቆ ነበር? ……. ሰላም ግን ጥሩ መልስ ሰጠች ..፣ እነሱ ቀድመው አናቴ ላይ ካልወጡ በቀር፣ ማንም አድናቆቱን ቢገልጽልኝ አልጠላም፣ ደስ ይለኛል፣ አብሬ ፎቶ መነሳትም እወዳለሁ… አይነት መልስ ሰጠች። እሱ ግን ቀጠለ…. “እኔ ግን ሌሎች ሲሸሹ ነው የማውቀው” ሲል ቀጠለበት። የሆነ ያጋጠመው ነገር እንዳለ ያስገምታል።

ከዚያ ስለ ፍቅር ህይወቷ ቀጠለ። ሰላም ተስፋዬ በቅርቡ ቀለበት አጠለቀች የሚል ብዙ ዜና ተሰምቷል። እሱ እንደ አዲስ “ፍቅረኛ አለሽ?” ሲል ጥያቄ አቀረበ። ይቺን እንኳን ማወቅ ይገባ ነበር። ከዚያማ .. ቀለበት ማድረጓን ከነገረችው በኋላ .. “ትጋባላችሁ? አስባችኋል?” ቀጠለበት … እንዴ ! ቀለበት ካሰሩ በኋላ መጋባት አለመጋባት የነሱና የፈጣሪ ፈቃድ ነው – ማፋጠጥ ምን ማለት ነው?……… “ቀናተኛ ነው?” ሲል ደግሞ ቀጠለ። “በጣም እንጂ፣ እኔማ ምርር ነው ያለኝ” እንድትለው ጠብቆ ይሆን? ፥ በዚህ መች አቆመ ..”ልጅ ትወልዳላችሁ?” አለ ቀጠለና። ወይ ጉድ።

ዋናው ጉዳይ [The fact] የሷ ቀለበት ማሰር ነው፣ ከዚያ ወዲያ ብትጋባ ባትጋባ የግል ጉዳይ ነው። መቼ ነው የምትጋቡት፣ ልጅስ መቼ ነው የምትልወዱት..፣ . እንዲያውም ፣ ቀለበት ያሰረላት ልጅ “ታገባኝ ይሆን? አረጋግጥልኝ፣” ያለው ነው የሚመስልበት።

ከዚያ እሱ የማስታወቂያ የታወቀ ባለሙያ መሆኑን ለራሱ ለማረጋገጥ “የኔን ሙያ ይዤ አሜሪካ ብሄድ፣ ባህር ዳር ቁምጣ አድርጌ የምዝናና እሆን ነበር” ብሎ ሙያው የሚልገውን በአገሩ እንዳላስገኘለት ከጠቀሰ በኋላ፣ እሷን ተመሳሳይ ነገር ጠየቀ .. አንቺስ?

እውነቱን መለሰችለት ..”ከድሮው ይሻላል፣ አሁን አሁን ክፍያውም ፣ ጥቅሙም ጥሩ ነው” .. የሷን መልስ እንደመልስ እንደመቀበል ማፋጠጥ ቀጠለ ..”ምን ይሻላል ትያለሽ፣ ዛሬ እኮ አንድ ሰንደል ፋብሪካ ከፍተሽ ሚሊየነር መሆን ትችያለሽ” ብሎ ቁጭ አለ። እሷ የምታወራው ስለ ፊልም ሙያ .. እሱ ስለ ሰንደል ፋብሪካ። ለነገሩስ ሰንደል ፋብሪካው በነጻ ነው እንዴ የሚከፈተው ..?

ይህን ካለ በኋላ “እስከዛሬ ለማስታወቂያ ስንት እንደሚከፈላት” ጠየቃት። መናገር አልፈለገችም “ጥሩ ተከፍሎኛል ከዚህ በፊት” ብላ አለፈችው።

ወደ መጨረሻው ተጠጋን። እንደ ትንቢት ተናጋሪ በኩራት “በቅርቡ ማግባትሽ አይቀርም – ልጅ መውለድሽም አይቀርም” አለ። በዚህ በተመሰቃቀለ ዓለም፣ ቀለበት ያደርገ ሁሉ ያገባል፣ ይወልዳል ማለት አይደለም። አሁንም ከሷ ባልመጣ ሃሳብ እሱ የሷን የወደፊት ህይወት መተንበይ ቀጠለ። “እግዚር ያውቃል” አለችው – ታዲያ ምን ትበለው? አባባ ታምራትን ወይም ነቢይ እገሌን መሰለ እኮ!

ከዚያ “ስለዳያፐር ማስታወቂያ ስሪ ብትባይስ ትሰሪያለሽ?” አላት፣ “ስንት ይከፈልሽ?” ዓይነት ጥያቄዎችም ደረደረ – ልብ መስቀሉ ይመስላል። እሱ ይህን ሁሉ ዳር ዳር የሚለው የአንድ ሚሊዮን ብር ማስታወቂያ አመጣሁልሽ ለማለት ነው። ግን ያልገባው ነገር ፣ ለማስታወቂያ የሚከፈለውን፣ የማስታወቂያውን ዓይነት ..፣ ወዘተ. ከአማካሪዎቿ ጋር ተማክራ ተነጋግራ መወሰን የምትችል ለመሆኑ ዕድል አልሰጣትም። ምናልባት እሷ “ሁለት ሚሊዮን ይከፈለኝ” ብላ መደራደር ብትፈልግስ? ላይቭ ሾው ላይ አቅርቦ የአንድ ሚሊዮን ብር ስምምነት እዚሁ ይፈጸም ማለት አይከብድም? ነጻ ስጦታ ቢሆን ኖሮ ጥሩ።

እንደሚመስለኝ “ይህን ያህል ብር ከተከፈላት፣ ሰይጣንንም ቢሆን ታስተዋውቃለች” ብሎ የደመደመ ይመስላል። ያለ መደራደር ዕድል “በቃ ትሰሪያለሽ፣ ብሩም ይኸው” .. ከዚያም. ነቢይነቱን በመቀጠልም “በቅርቡም አግብተሽ ስትወልጂ የዳይፐር ወጪ የለብሽም” ሲል አከለበት። ለዚያ ያብቃት እንጂ፣ የዳይፐር ወጪ መች ያሳስባታል?

ማስታወቂያውን ልትሰራው ትችላለች፣ ገንዘቡም ቀላል አይደለም። ግን ባፈራችው ዝና፣ በሙያዋ፣ ትፈጥራለች በሚባለው ተጽዕኖ፣ ምናልባት ኩባንያው ከሰጣት አንድ ሚሊዮን በብዙ ዕጥፍ ልታስገኝ እንደምትችልም ታምኖ የተሰጣት ክፍያ ነው። ሳሚ ከኪሱ እንደሚሰጥ ሁሉ ፣ ልዩ ውለታ እንደዋለላትና እንደ ገና ስጦታ መቁጠሩ ትክክልም አይመስልም። ክፍያው ከሌሎች ሊያስተዋውቁ ከሚችሉ መካከል በችሎታዋ ተመርጣ የተከፈላት መሆኑን አደብዝዞታል።

ለዚህም ይመስላል፣ ትንሽም ይሁን ትልቅ “ሰርፕራይዝ” የሚያስፈነድቃት ሰላም፣ የአንድ ሚሊዮኑ ሰርፕራይዝ ብዙም የደነቃት ያልመሰለው።

[ያው እኔ ብሆን ከፎቅ ላይ ሁሉ ልዝል እችል ነበር . በሚል ታሳቢ]

4 Responses to ሳምሶን ማሞ እና ሰላም ተስፋዬ

 1. tikekleja techete newe,enem programmun temelkechewalehu,samson lekee alneberem,selam wasnot free too

  moshe
  January 9, 2018 at 2:46 am
  Reply

 2. right comment

  moshe
  January 9, 2018 at 2:47 am
  Reply

 3. ዝባዝንኬ የበዛበት ኣሰልቺ ጽሁፍ።።።። ኣንዳንዴ ለ ኣንባቢው ኣስቡለት እንጂ
  እንደዚህ ኣይነት ጽሁፍ ሲበዛ የ ድረ ገጹን ደረጃ እንዳይቀንሰው ተጠንቀቁ

  kebede
  January 9, 2018 at 4:41 am
  Reply

 4. Selam Tesfaye eko Tigre weyane nat !!

  ahun yalbelach meche tibla ???

  demo konjo eyalu yamogisuwatal ,, echin afe sefi Ginbaram Tigre KKKK

  Mot le weyane

  seyfu
  January 9, 2018 at 11:48 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<