አርቲስት መሠረት መብራቴን እንዲህ ጥምድ አድረው የያዟት እነማን ናቸው? (በጽሑፍ እና በቪዲዮ የቀረበ)

Filed under: News Feature,ኪነ-ጥበባዊ ዜና |


ስለ መሰረት መብራቴ የማናውቃቸው ምስጢሮች

የህዝብ ሃብት ሚዘርፉትን ኪራይ ሰብሳቢ ይሏቸዋል። የሃገር ሃብት የሚያሸሹትን ሙሰኞች ይሏቸዋል። ነውር ነገር የሚያደርጉትን ደግሞ አሳዳጊ የበደላቸው እንላቸዋለን። ግለኝነት ተጠናውቷቸው፣ የፈለጉት ነገር ሳይሆን ሲቀር ጥላሸት የሚቀቡትስ ምን አይነት ስም ይሰጣላቸው ይሆን?
ለዛሬ ሹክሹክታ የመረጥንላችሁ ርእስ ስለ ተወዳጅዋ አርቲስት መሰረት መብራቴ ነው። በዩቱብ እና ማህበራዊ ገጾች ላይ ሳያቋርጥ ስሟ ይነሳል። ከሳሾችዋ፣ በባህርይዋም ሆነ በስነ-ምግባርዋ አንዳች መጥፎ ነገር ሊያወጡባት ባይችሉም፣ በሙያዋም ቢሆን እንከን አያገኙባትም። በጠነከረ የክርስትና እምነትዋ ጸንታ መኖርዋና አልበገር ማለትዋ ጥላቻን እንዳፈራች እርግጥ ነው።
ቆንጆና መልከ መልካም ሴት ናት። በውበትዋ የሚማረኩ ጥቂቶች አይደሉም። በድንቅ ትወናዋ እና በማራኪ ስብእናዋ የሚወድዱዋት ቢያመዝኑም፣ የሚቀኑባትም አልጠፉም። ቅናት በተራው ክፋትና ምቀኝነትን ወልዶ እነሆ የአርቲስትዋን ስብእና የሚያጎድፍ ድርጊት በማህበራዊ ደረ-ገጽ እየተሰራ ነው።
ለመሆኑ ከዘመቻው ጀርባ ያሉ አስገራሚ እውነታዎች ምንድናቸው? ይህን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ስለ ተወዳጇ አርቲስት ጥቂት እንበል።
አርቲስት መሰረት መብራቴ የተወለደችው አዲስ አበባ ግቢ ገብርኤል አካባቢ ነው። አንድ ወንድምና ሁለት ታናናሽ እህቶች አሏት። የመጀመሪያ የመድረክ ስራዋ የልብ እሳት ትያትር ሲሆን በተለይ በገበና ተከታታይ ድራማ በሕዝብ ድምጽ ለሽልማት የሚያበቃ ትወናዋን አሳይታለች። መሠረት የድራማና የቴዓትር ሥራ የጀመረችው ቤተክርስትያን (የሰንበት ትምህርት ቤት) ውስጥ የመንፈሳዊ ትያትሮችን በመስራት ነበር።
የሻማ እንባ በተሰኘ የቲቪ ድራማ ወደ ጥበቡ አለም ጎልታ ተቀላቅላለች። በርካታ የመድረክ ስራዎች ላይ በትያትር ቤቶች እና ከሀገር ውጪ ትያትር ተውናለች። ከፊልም አለም ጉዲፈቻ፣ የፍቅር ሽምያ፣ ዜማ ህይወት፣ ንጉስ ናሁ ሰናይ፣ የሞርያም ምድር፣ ቫኬሽን ፍሮም አሜሪካ፣ ሄሮሽማ እና ህርየት የተሰኙ ፊልሞች ላይ ተውናለች። የቲቪ ድራማ ደግሞ ገመና እና በቀናት መካከል የተሰኙት ይጠቀሳሉ።
ለትወናዋ ብቃት እና ለጥበብ መፈጠርዋ የሚመሰክረው ለህዝብ ያቀረበችው ስራዋ ብቻ ነው። ከሚሰጣት ወይንም ከምትወስደው ገጸ-ባህርይ ጋር መዛመድን ተክናዋለች። እብደትን በሚገርም ብቃት ትተውናለች፣ ድህነትን ትመስለዋለች፣ የፍቅር አለም ውስጥ ስትገባም ተመልካቹን ይዞ ጭልጥ የሚያስብል ክህሎት የተላበሰች የጥበብ ፈርጥ ናት።
እዚህ ለመድረስ ግን ብዙ ፈትናዎችን ማለፍዋ ግድ ነበር። ልማታዊ አርቲስት በመሆን እና ባለመሆን የነበረ ትንቅንቅን በአሸናፊነት ብትወጣውም ልማታዊ ያለመሆንዋ ዋጋ እየስከፈላት ነው።
መሲ በተለያዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ትሳተፋለች። የሜሪ ጆይ በጎ ፈቃደኛ ሆና ለግዜዋም ሆነ ለጉልበትዋ ሳትሳሳ እያገለገለች ትገኛለች።
ለአፄ ሚኒሊክና ለማንዴላ ልዩ ፍቅርና አድናቆት አላት። በአንድ ዋቅት ለቀረበላት ቃለ-መጠይቅ አጼ ሚኒሊክን እያሞገሰች ስትናገር ባለግዜዎቹ ደማቸው ፈልቶ እንደነበር ታዝበናል። ከዚያን ግዜ ጀምሮ በክፉ ያዩዋት ጀመር። የአውራምባው ታይምስ ዳዊት ከበደ ሳይቀር በመሲ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ቢከፍትባትም ከነበራት የህዝብ ፍቅር የተነሳ ዘመቻው ግብ ሊመታለት አልቻለም።
የትውልድ ፈርጦች እንዳሉ ሁሉ የትውልድ ዝቃጮችም አሉ። ከዝቃጮቹ መቼም መልካምን ነገር አንጠብቅም። ዝቃጮች ራሳቸውን ደብቃው ይሳደባሉ፣ ይዋሻሉ፣ ስም ያጠፋሉ። በአርቲስትዋ ላይ በብዙ የተሞከረው ጥላሸት መቀባት አባዜ አሁን መልኩን ቀይሮ መጥቷል። ዘመቻ ዩትዩብ።
“አርቲስት መሰረት መብራቴ እና ንብረት ገላው (እከ) ፍቅራቸውን ይፋ አደረጉት”፣
“አርቲስት መሰረት መብራቴ ባለቤቷን ይፋ አደረገች”፣
“አርቲስት መሰረት መብራቴ ድምፃዊውን ልታገባ ነው” ወዘተ ከተሰኙ ተረት-ተረቶች ጀርባ ባለስልጣናት እና ልማታዊ ባለሃብቶች አሉ።
ለእንደዚህ አይነቱ የፈጠራ ዘመቻ ሁለት ምክንያቶች እንዳሉ ለሹክሹክታ የደረሰው ማስረጃ ያረጋግጠል። አርቲስትዋ ታዋቂ ናት፣ አርቲስትዋ መልከ-መልካም ናት፣ አርቲስትዋ መልካም ስነ-ምግባር የታነጸች እና ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረባት ናት።
ይህችን ሴት ለትዳር መመኘት አንድ ነገር ነው። ወግና ማእረግን ይዞ ለትዳር ጓደኝነት ማጨትም ምንም ክፋት የለውም።
ግን ልማታዊ ባለሃብት ስለሆነ ብቻ ለመኝታ ሲጋብዛት እንቢ ማለትዋ ነው ያስወነጀላት። ለአዳር የሚፈልጓት ሁሉ መሲ ላይ በብዙ መንገድ ይመጡባታል። የገንዘብ እና የጉልበት ሃይላቸው እየተማመኑ ይጠይቃሉ፣ ያስጠይቃሉ።
የመሰረት መብራቴ ምላሽ ያለስደሰታቸው የግዜው ጉልበተኞች ሁሉ እንዲህ አይነት የወረደ ተግባር ቢፈጽሙ ላይደንቀን ይችላል። ስካር፣ ዝሙት፣ ስግብግብነት፣ ዘራፊነት፣ ተሳዳቢነት፣ ጥጋብ… የነገሰበት ሃገር አንድ ጨዋ ቢገኝ ጥፋተኛው ጨዋው ይሆን?
እርግጥ ዘመኑ ክፉ ነው ልንል እንችላለን። ይህንን የሚያደርጉት የየዘመኑ ትውልድ እንጂ ግዜው አይደለም። ይህች አርቲስት በእምነትዋ እና በወግዋ መጽናትዋ የዚህ በዝሙት የናወዘ ቡድን ሰለባ አድርጓታል። በቃናት መካከል የተሰኘው ተከታታይ ድራማ እንዲቋረጥ የተደረገው ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ነው። መሲ ልማታዊ አርቲስት አልሆንም በማለትዋ ምክንያት ከማስታወቂያው ቢዝነስም እንዳትሳተፍ ተደርጋለች።
ይህ ነገር ሁሉ ተፈጽሞባት እስዋ ግን አልተበገረችም። በቅርብ በሰጠችው ቃለ-መጠይቅ ተስፋዋን በፈጣሪ ያደረገች ነው የምትመስለው። “ጸሎት ከምንም በላይ ሃይል አለው። ከሩጫም ከምንም በላይ ፤ ጉልበት አቅም ያለው በሙሉ ባለው አቅም ያድርግ …ስለቤተክርስትያን ስለሃገራችን ስለእያንዳንዱ ሰው እንጸልይ” ትለናለች።
እኛም ጽናቱን ይስጥሽ ብለን እንሰናበት።

3 Responses to አርቲስት መሠረት መብራቴን እንዲህ ጥምድ አድረው የያዟት እነማን ናቸው? (በጽሑፍ እና በቪዲዮ የቀረበ)

 1. How much do you get paid to write this commentary?
  Because, you haven’t told us anyone who could be responsible for this yet.

  Batti
  January 12, 2018 at 9:54 am
  Reply

 2. ስንት የሚያስጨንቅ የሀገር ጉዳይ እያለ እንቶ ፈንቶ የቡና ላይ ወሬ እዲያ

  ራሄል
  January 12, 2018 at 10:12 am
  Reply

 3. እግዚዓብሔር ከፈተና ይጠብቅሽ፣ጽናቱን ይስጥሽ፣ድንግል ማርያም ልጄ አይዞሽ ትበልሽ.;

  NARDI
  January 12, 2018 at 11:38 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<