ሮቤል ኪሮስ የቀድሞው ዋናተኛ የአሁኑ ስደተኛ | በቪዲዮና በጽሑፍ የቀረበ

Filed under: News Feature,ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች |

        በሪዮ አሎምፒክ ኢትዮጵያን መሳለቂያ ያደረገው ሮቤል ኪሮስ በአሜሪካ ስደት ጠይቋል። ልጁ ወደ አሜሪካ ከመሄዱ በፊት በኤፍ ኤም ፣ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አንድ የአሜሪካ “ፕሮፌሽናል ክለብ” በኮንትራት እንደወሰደው ተናግሮ ነበር።

        የሹክሹክታ ምንጮች እንደሚሉት፣ ልጁ የውሃ ዋና ክለብ አላገኘም። በአሜሪካ የስራ ኮንትራትም አልተፈራረመም። እንደማንኛውም የህወሃት ባለስልጣናት ልጅ ወደ አሜሪካ ተልኳል። ለግሪን ካርዱ ሲል፣ ስደት በመጠየቅ ኑሮውን እዚያው መስርቷል።

        ግን “ፕሮፌሽናል ክለብ እና ኮንትራት” እያሉ መዋሸቱ ለምን አስፈለገ?  ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ከመስጠታችን በፊት ስለ ሮቤል ኪሮስ የ2016 ኦሎምፒክ ክስተት በወፍ በረር እይታ እንቃኝ።

        ብራዚል 2016፣ 31ኛው የሪዮ ኦሊምፒክ ሲነሳ፣  ሶስት ትላልቅ ጉዳዮች ይነሳሉ። በአንደኛ ደረጃ፣ የጀግናው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጀብድ ይነሳል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በውድድሩ እንዳይሳተፍ የመደረጉ ጉዳይም ሌላው ክስተት ነው። ከሁሉም በላይ ግን ኢትዮጵያዊው የኦሎምፒክ ዋናተኛ ሮቤል ኪሮስ ሁሌ ይታወሳል።

        ሮቤል ኪሮስ ኢትዮጵያን ወክሎ በ100 ሜትር ነጻ ቀዘፋ (ፍሪ ስታየል) የውሃ ዋና  ለመወዳደር ብራዚል ሄዶ፣  ከ59 ተወዳዳሪዎች 59ኛ መውጣቱ ብቻ አልነበረም አለምን የስገረመው። እርግጥ  ነው በዚህ ውጤቱ ኢትዮጵያን “የመጨረሻው ቀርፋፋ ዋናተኛ” በማስባል አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። ከዚያ በላይ ግን የሰውነት ቅርጹን እጅግ ያሳፍር ነበር። ቦርጩን ለመቀነስ እንኳን ትንሽ ሳይጨነቅ በመቅረቡ፣ ተንቀሳቃሽ የሲሚንቶ ማቡኪያ መስሎ የመገናኛ ብዙሃን ትኩረትን ስቦ ነበር።  

        ይህ ክስተት ኢትዮጵያን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋና የስፖርት ዘርፍ በማይጠበቅ የሰውነት ቅርፅ ተወዳደሪ ያቀረበች ሀገር አርድጓታል።

        የሮቤል ነገር መነሳት የጀመረው ልጁ ገና ወደ ዋና መወዳደሪያ ገንዳ ለመግባት ዝግጅት ሲያደርግ ነበር።  ኢትዮጵያ ለ2016ቱ የኦሎምፒክ ውድድር መቀለጃ እና መሳለቂያ መሆን የጀመረችው ያኔ ነው። የዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃን እና ማኅበራዊ ገፆች ላይ ሚሊዮኖችን ሲያነጋግር ቆይቷል። ክስተቱ ለውጭ ዜጎች መሳለቂያ፣ ለእኛ ደግሞ መሳቀቅያ ነበር። በዓለም መድረክ አንገታችን ያስደፋ ክስተት።

        የዋና አሰልጣኙ አበበ የውሃ ዋና ቡድኑን ይዞ ወደ ሪዮ ኦሊምፒክ እንደሚሄድ ሲነገር ቆይቶ በመጨረሻ ግን ከቡድኑ ጋር ሳይጓዝ ቀርቷል። በአሰልጣኙ ምትክ የዋና ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና  የሮቤል አባት የሆኑት አቶ ኪሮስ ሃብቴ እንዲጓዙ ነበር የተደረገው። የሮቤል አባት አስቀድመው ሲናገሩ፤ “ለአንዲት ደቂቃ ውድድር አሰልጣኙ መጣ አልመጣ አዲስ ነገር አይፈጠርም። በውጤቱ ላይ የሚጨምረው ነገርም የለም።” ብለው ነበር።

        ሌላ ግዜ ጋዜጠኞች ሲያፋጥጧቸው አሰልጣኙ፣  “ችሎታ ስለሌለው ነው ያላመጣነው!” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ኢትዮጵያን በአለም መድረክ  ያስጠሩ አትሌቶች ባሉባት አገር፤  ሮቤል በመክፈቻው የሃገሪቱን ባንዲራ ይዞ ለመሰለፍ የተመረጠበት ሁኔታም ይነሳል። ሮቤል ኪሮስ በተሳተፈበት የ100 ሜትር ነፃ ቀዘፋ የውሃ ዋና ውድድር የተሟላ ብቃት (ሚኒሞ) አላሳየም። ከሱ የተሻለ ውጤት የነበራቸው ዋናተኞች ነበሩ። ሮቤል ለሪዮ ኦሎምፒክ ብቁ አልነበረም። ኪዚያም በላይ ቦርጫም በመሆኑ “አሳነባሪው ዋናተኛ” የሚል ስም ወጥቶለታል። ሮቤል ኪሮስ ወደ ሪዮ ኦሎምፒክ ሊሄድ የቻለው በአባቱ ተመርጦ መሆኑ በመጨረሻ ይፋ ሆኗል። የስፖርት ፌዴሬሽኑ በዘር ፖለቲካ ውስጥ ገብቶ መዋኘቱም በዚህ ተረጋገጠ። ሚኒማውን ማሟላት ማለት በዝምድና ወይም የፖለቲካ ትስስር እንጂ በችሎታ ያለመሆኑ በዚሁ ተመሰከረ።

        ሮቤል ኪሮስ ከኦሎምፒክ ጉዞው ቀደም ብሎ ለጋዜጠኞች “ጥሩ ልምምድ አድርጊያለሁ፣ በክፍተኛ ብቃት ላይ እገኛለሁ” ብሎ ነበር የተናገረው። እናቱ ፣  “ሮቤል ልጄ በኦሎምፒክ ወርቅ እንደሚያመጣ እተማመናለሁ” ሲሉ ተናግረው ነበር። ከውድድሩ በኋላ ግን ውድድሩ እንደ ተሳትፎ መታየት ይኖርበታል እንጂ ውጤት የሚገኝበት ተደርጎ መወሰድ የለበትም። ብለውናል አባቱ።

        ሮቤል በሰጠው አስተያየትም በኦሎምፒክ መሳተፉ በራሱ ትልቅ እድል መሆኑን እና ከተሳትፎ በላይ የጠበቀው ውጤት እንዳልነበረ ተናግሯል።  ይህ ደግሞ የህዝብ ገንዘብ በነዚህ ሃላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች ምን ያህል መጫዎቻ እንደሆነ ያሳየናል።

        እነሱ በመሳተፋቸው እና ውራ በመውጣታቸው ብቻ ሊደሰቱ ይችላሉ። ለዚህ ቀልድ ስራ የሚወጣውም የውጭ ምንዛሪም ደንታ ላይሰጣቸው ይችላል። ክስተቱ ሃገርን መሳለቅያ እና መቀለጃ ማድረጉን እንዲያውም የኢትዮጵያውያንን አንገት ማስደፋቱን ዘንግተውታል።    

        በነሱም ብሶ መገናኛ ብዙሃኑን እና ማህበራዊ ሚዲያውን ማውገዙን ተያያዙት። በጉዳዩ የሚተቹት ጋዜጠኞችም “ስለ ዋና ስፓርት እውቀቱ የሌላቸው” ተብለው ተብጠለጠሉ። ፀረ ሰላም ዲያስፖራ ሃይሎች ደግሞ በተለመደው “የተጀመረው የልማት ጉዞ እንቅፋቶች” መባላቸው አዲስ ነገር አይደለም።

        ችግሩ በዚህ የሙስና አሰራር አላበቃም። ችግሩ የህዝብ ገንዘብ በማባከን አላበቃም። ችግሩ በስድብ አላበቃም። ራሳቸው የፈጠሩትን ችግር በይቅርታ አልፎ ወደፊት ከመጓዝ ይልቅ፣ እነዚህ ሰዎች ችግራቸውን ለመሸፈን ደርዘን ምክንያቶች መደርደር ያዙ። ጥፋታቸውን ከማረም ይልቅ፣ ጥፋትን በየጥፋ መደራረብ ስራቸው ሆነ።

         የልጁን ስብእና በውሸት መገንባት መፍትሄ ነው ብለው ያዙት። በስሙ ድርጅት አቋቋሙ። የአንድ ሚሊዮን ዶላር ፈንድ ለመሰብሰብ ቢሞክሩም፣ የተሰበሰበው ግን ከ50 ዶላር አላለፈም።  

        ቀጥለውም ሮቤል ካናዳ ለአለምቃቀፍ ውድድር ተጠራ ስሉ ዋሹ።

        በመጨረሻም ሮቤል በአሜሪካን ሃገር ፕሮፌሽናል ክለብ ማግኘቱን በሰይፉ ፋንታሁን በኩል እንዲነገር ተደረገ።  ክለቡ የሮቤልን ውጤት አይቶ በደስታ ተቀበለው ተባለ። ከክለብ ውድድሩ ልምድ በኋላም ሃገሩ ገብቶ ለብሄራዊ ቡድን እንደሚሰለፍ ተገለጸ።

        ሮቤል አሜሪካ ገባ። እንደገባ ቀዘቀዘ። አሁን እንደማንኛውም የባለስልጣን ልጅ እዚያ ይኖራል። በቨርጂንያ ስካይ ላይን አካባቢ አይጠፋም። የባለስልጣን ልጅ ስለሆነ ስራ ባይሰራም እንዲሁ ይኖራል።

        በነገራችን ላይ፤ የኢትዮጵያኖች መገበያያ ስፍራ፣  ስካይ ላይን መንደር አሁን በህወሃት ሰዎች ሙሉ በሙሉ እየተያዘ ይገኛል።

        “ፕሮፌሽናል” ብለው ኢትዮጵያ ላይ መሳለቂያ ያደረጉት ዋናተኛ እርግጥም ፕሮፌሽናል ለማስመሰል ብዙ ጣሩ። ሮቤል በዘር መስፈርት ሳይሆን በችሎታ የደተመረጠ አትሌት ለማስመሰል ያደረጉት ጥረታቸው በሙሉ አልተሳካም።  

        ሮቤል ኪሮስ፣ የቀድሞው ዋናተኛ .. የቀድሞው በላተኛ… የአሁኑ ስደተኛ!

        ይህ ሹክሹክታ ነው!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.