በትግሪኛ ቋንቋ የሹመት ደብዳቤዋን የምታቀርበው የኢትዮጵያ (የሕወሃት) አምባሳደር (አባይ ወልዱና ባለቤቱ ትርፉ ኪ/ማርያም)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |


ከቅዱስ ሃብት በላቸው (አውስትራሊያ)

ከትግራይ ክልል አስተዳዳሪነት በብቃት ማነስ የተባረሩት አቶ አባይ ወልዱ “የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር” ተብለው መሾማቸው ያስገረማቸው በርካታ ሰዎች የሰጡትን አስተያየት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ አንብቤአለሁ። ይህ አካሄድ ካሁን ቀደምም ሲሰራበት የኖረ የተለመደ ህወሃታዊ ስልት ነው። እንዲያውም በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቤተክሕነትም በብቃት ሳይሆን ከሕወሃት ጋር ባላቸው የስጋ ዝምድና በሃላፊነት የተሾሙ ካድሬዎች ከአንዱ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ዘርፈው፣ ወይንም ሌላ ጥፋት አጥፍተው ሲታወቅባቸው ወደ ሌላ ቦታ እንዲዘዋወሩ ይደረጋሉ እንጅ በጥፋታቸው ሲጠየቁ ታይቶም! ተሰምቶም አይታወቅም! … የሰሞኑ የአባይ ወልዱ የአምባሳደርነት ሹመትም የዚሁ አንድ አካል ነው። ለምሳሌ በአውስትራሊያ፣ ኒዊዚላንድ እና ፉጂ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተብላ የተሾመችው ሚስቱ ትርፉ ኪ/ማርያም ለዚያ የሚያበቃ የትምህርት ደርጃም ሆነ የስራ ልምድ የሌላት የወያኔ ታጋይ ናት። ለዚህ ሹመት ከመብቃቷ በፊት የትግራይ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሃላፊና የክልሉ ዳኞች ሰብሳቢ የነበረች ሲሆን ለዚህም ሹመት የበቃቸው ለቦታው የምትመጥን ስለሆነች ሳይሆን የክልሉ ፕሬዚዳንትና የህወሃት ሊቀመንበር የነበረው የአባይ ወልዱ ሚስት በመሆኗ ነበር። ምንም እንኳን ተጋዳላይ ትርፉ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በቢዝነስ ማኔጅመንት የሁለተኛ ዲግሪዋን ደግሞ በገጠር ልማት ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እንዳገኘች ቢነገርላትም የርሷም የትምህርት ማስረጃ እንደመሰሎቿ የህወሃት ራሶች በሽልማት መልክ የተበረከተ (የተገዛ) እንደሆነ በስራ ላይ ሳለች ባስመዘገበችው ውጤት ማረጋገጥ ይቻላል።


ግለሰቧ የትግራይ ክልል ባለስልጣን ሆና በምትሰራበት ወቅት በትግራይ ፍትህ ቢሮ በተደረገ ግምገማ በከባድ ሙስናና የሀገርና የህዝብ ሃብት በማጥፋት ተገምግማ በህወሓት ጉባኤ ከሃላፊነቷ እንድትወርድ ተወሰነ። ይህንን በመቃወምም ለጥቂት ጊዜያት በስራዋ ላይ ከቆየች በኋላ ውስጥ ለውስጥ በተደረገ ድርድር የአውስትራሊያ፣ የኒዊዚላንድና የፉጂ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆና ተሾማለች። የቀድሞ የስራ ባልደረባዬና ጓደኛዬ አርአያ ተስፋ ማርያምም ከዓመታት በፊት ስለርሷና ባለቤቷ በከተበው ፅሁፍ የሚከተለውን አካፍሎን ነበር።


“የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አባይ ወልዱ ካስገነቧቸው ሁለት ቪላ ቤቶች አንዱን መሸጣቸውን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። የሕወሐት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አባይ ወልዱ በክልሉ ካስገነቧቸው ሁለት ቪላ ቤቶች አንዱ የሆነውና በመቀሌ – ዓዲ ሃውሲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን ይህን ቪላ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ወጪ ካስገነቡት በኋላ እንደሸጡት ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አባይ ወልዱ በባለቤታቸው ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያም ስም በአዲግራት ከተማ ባለሶስት ፎቅ ዘመናዊና በውድ ዋጋ የተገነባ ቪላ እንዳላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል። የአባይ ወልዱ ባለቤትና የክልሉ ባለስልጣን የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪ/ማርያም በትግራይ ክልል ከመንገድና ኮንስትራክሽን ስራዎችና በተለያየ ንግድ በክልሉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር በሙስና ተግባር መሰማራታቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።”


ከጫካ ከወጣች ጀምሮ ስለሌላው ዓለም አይደለም ከትግራይ ተሻግራ ስለቀሪው ኢትዮጵያ ምንም አይነት እውቀት ሳይኖራት በሹመት የተንበሸበሸችው ትርፉ ምንም እንኳን ስልጣኑ የርሷ ቢሆንም ስራውን የሚሰሩት ግን ሌሎች በስም የማይታወቁ ሙያተኞች እንደሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ሴትዮዋ ለአምባሳደርነት አይደለም ለመንደር የሴቶች ማሕበር ሊቀመንበርነት የማትበቃ ተራ ባልቴት መሆኗን ለማወቅ የፈለገ ደጋግማ ከምትመላለስበት የአውስትራሊያው ኤስ.ቢ.ኤስ ራድዮ ጋር ያደረገቻቸውን ቃለምልልሶች ማድመጡ በቂ ነው። በተከፈተ አፍ አይደል ባዶ ራስ የሚታየው?

እንዲያውም ሴትዮዋ ከአገር ከወጣች በኋላም ከዚሁ የአምባሳደርነት ስራዋ ይልቅ ከደሃው ወገናችን የዘረፈችውን ሃብት ለማደላደል እንደምትተጋ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይናገራሉ። የሌላውን ባላውቅም አንድ ልጇም እዚሁ አውስትራሊያ እንዳለ አውቃለሁ። እንዲያውም እነደብረፅዪን በስልጣን የሚገዳደራቸውን ባለቤቷ አባይ ወልዱን የአምባሳደርነት ሹመት ሰጥተው ገለል እንዲልላቸው ያደረጉት ቀሪ ሕይወቱን ከባለቤቱና ቤተሰቡ ጋር ዘና ብሎ መኖር የሚችልበትን መንገድ ለማመቻቸት ጭምር ሳይሆን ይቀራል ብላችሁ ነው? … ስለዚህም በቀጣይ፦ መጀመሪያ የአውስትራሊያና የኒዊዚላንድ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ደግሞ የፉጂ አምባሳደርነት ከተጨመረላት ባለቤቱ እነደብረፅዮን አንዱን አገር ቀንሰው ለርሱ መጦሪያ አበርክተውለት ከጫካ ባለቤቱ ጋር ያገናኙት ይሆናል! ለማንኛውም ሁሉንም በቅርቡ እናየዋለን! እስከዚያው ግለሰቧ ለፉጂ ፕሬዚዳንት የሹመት ደብዳቤዋን ስታቀርብ የሚያሳየውን ቪድዮ አይታችሁ ትፈርዱኝ ዘንድ አያይዤላችኋለሁ! …Dear excellence .letter …. Federal Democratic Republic of Ethiopia ከሚሉት የእንግሊዝኛ ቃላት ውጭ በትግሪኛው ነው የምትሄድበት!

11 Responses to በትግሪኛ ቋንቋ የሹመት ደብዳቤዋን የምታቀርበው የኢትዮጵያ (የሕወሃት) አምባሳደር (አባይ ወልዱና ባለቤቱ ትርፉ ኪ/ማርያም)

 1. ante begleh setyewan tetelat endehone lela neger newe,ENGLISH maweke ye alem mederesha behone noro FRANCE , GERMANY,ISRAEL—- ezehe balderesu neber.ante fereteteh AMERICA OR LONDON setegeba kenefesebelawe derge yaterefute agerachin Ethiopian kechaka yemetute gjegnoch nachewe. englisejama eweqet behone noro America taxi driver ,parking zebejaa mechee yeja sewe yehone neber. WAKE UP MAN

  moshe
  January 19, 2018 at 2:58 am
  Reply

 2. እና ምን ይጠበስ ?
  ፌደራሊዝሙ እኮ ስልጣንን ከፊውዳል ገዥ መደብ እጅ ከተፈለቀቀ ቆየ ፡፡
  ቢፈልግ በትግርኛ ቢፈልግ በቅማንትኛ ቢፈልግ በሽናሻኛ ወይም በስልጥኛ ያቅርብ ፡፡ ሁሉም ቋንቋ እኩል ነው ፡፡የቤተመንግስት ቋንቋ እኮ የሚባል ከቀረ ሠነባበተ ፡፡

  ሌላው

  ኢሀአዲግ እንደ ደርግ ጅብ አይደለም የቆሠለ አባሉን አይበላም ፡፡
  አብዮት ልጆችዋን ትስማለች !!!!!

  ነቄ
  January 19, 2018 at 4:15 am
  Reply

 3. ‘moshe’ and ‘ነቄ’ is one (same) person, obviously a banda from Adwa/Adi Abun.

  you smell a typical Banda from Adwa.

  death to Adwa bandas.

  gedamu
  January 19, 2018 at 3:07 pm
  Reply

  • ጀልጋጋ ዘረኛ

   ነቄ
   January 21, 2018 at 3:04 am
   Reply

 4. የሜዳዋን ጣጣ ያየ ብዙ አይቀባጥርም!!! ዓባይ ወልዱ ሜዳ የፈተነው ሜዳ የወለደው ነው!!! በትግል የተፈተኑ ልጆች አሉን!!

  Mulugeta Andargie
  January 19, 2018 at 4:20 pm
  Reply

 5. ግማታም ትግሬ ሁሉ ኢትዮጲያን ለቃቹ ወደ ሀገራቹ ሂዱ እባካቹ እንላለን።

  ethiopia tikdem
  January 20, 2018 at 12:04 am
  Reply

 6. What can be expected from these scum of humanity?. They are a disgrace to the very Tigre race which the half-beast Woyanes hail from.

  Their frantic attempt to buy time, is futile. In the minds of 95% of Ethiopians, the TPLF men and women are condemned to painful death.

  Whether they are made ambassadors who are engaged in merchandise involving historical and religious artifacts looted from Ethiopia’s holy places, their days are numbered.

  S.D. N. Liben
  January 20, 2018 at 1:42 am
  Reply

 7. በትግርኛ ማቅረቧ ምን ያስደንቃል ? ኢትዮጵያ በትግሬ አፓርታይዳው አገዛዝ ሥር ከወደቀች ከ፪፮ ዓመታት በላይ ሆኖዋታል
  አይደል አንዴ ? በመጀመሪያ ሴትዮዋ ለዚህ ሹመት የምትበቃም አይደለችም ! ህወሓት ትግሬ መሆንን አንጂ ዕውቀትን አይጠይቅም ! አገሪቱ ማንበብና መጻፍ በማይችሉ ጉዑዛን የትግራይ አራዊቶች አየተገዛች አይደል ! ሞት ለትግራይ ሞሶሎንዎች
  አና ተከታዮቻቸው ይሁን !

  አደባይ
  January 20, 2018 at 3:45 am
  Reply

 8. Denqoro hule hayl align yilal. Tibeb gin me-yet yimetal? Yechka aEmuro.

  Ethiopiawi
  January 20, 2018 at 4:19 am
  Reply

 9. Tigrigna is a language spoken by kings and queens. Before Amharic took over as the dominant language in Ethiopia, Tigrigna was the official language of the country under his excellency emperor Yohannes IV’s first democratic government in Ethiopia. All the important people who came to seek favors from emperor Yohannes IV had to either learn to speak the kings language of Tigrigna, or bring along a translator to his court. Therefore, we the proud sons and daughters of emperor Yohannes IV intend to make Tigrigna the official and working language in Ethiopia again. Her excellency Weyzero Tirfe’s presentation of her impeccable credentials to Fiji’s president in the Tigrigna language is a good start. Tigray is the center of gravity, and the Tigrigna language should reflect that undeniable reality. God bless Tigray, and Ethiopia.

  Awash
  January 20, 2018 at 9:20 pm
  Reply

 10. ትግርኛ ገና ስፔስ ላይ ይነገራል ፡፡ ጠላት አፍንጫህን ላስ !

  ነቄ
  January 21, 2018 at 3:05 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<