ቴዲ አፍሮ ለባህርዳሩ ኮንሰርት ስንት እንደተከፈለው ያውቁ ኖሯል? | ተጨማሪ መረጃዎችንም ይዘናል

Filed under: News Feature,ኪነ-ጥበባዊ ዜና,የዕለቱ ዜናዎች |

ቴዲ አፍሮ የፊታችን እሁድ በባህርዳር የሚያደርገው የሙዚቃ ኮንሰርት በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል:: ለመሆኑ በዚህ ኮንሰርት ቴዲ አፍሮ ስንት ያገኛል? ኮንሰርቱስ እንዴት ፈቃድ አገኘ የሚሉ መረጃዎችን የያዘ ዘገባ ይዘናል ይመልከቱት::

ሳልሳዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
(ቬሮኒካ መላኩ)
ጥር ፲፫ በባህር ዳር ፈለገ ግዮን በአስራት ወልደየስ ስታዲየም(ስታዲየሙ በፕሮፌሰር አስራት ስም ብንጠራው መልካም ነው ) በዳግማዊ ቴዎድሮስ ሁለት መቶኛ አመት የልደት በአል ላይ ቴዲ አፍሮ ሳልሳዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ተብሎ በአንድ መቶ ሺህ ህዝብ ፊት ይነግሳል። የአማራ ህዝብ አዳኝ መሲህ ይመጣል ይወለዳል ኢትዮጵያን በፍቅር አንድ ያደርጋል እየተባለ ለዘመናት ትንቢት የተነገረለት ቴዎድሮስ የተባለው ንጉስ እነሆ መጥቷል። አንቺ የባህር ዳር ምድር ሆይ ምንኛ ታድለሻል። ቴዎድሮስን ልታነግሽ በኢትዮጵያው ካሉ ከተሞች ሁሉ አንቺ ተመርጠሻል።

አይሁዶች ክርስቶስ የተባለ አዳኝ ከዳዊት ወገን እንደሚወለድ ተነግሯቸው በተስፋ ይጠባበቁ ነበር። እነሱ ይጠብቁ የነበረው ጦር ሰራዊት አሰልፍ የሚመጣ ጦረኛ ነበር። የዛሬ ሁለት ሺህ አመት ገደማ ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ሁኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ጥቂት ህፃናት እና የከተማይቱ ነዋሪዎች ብቻ ነበሩ ሆሳእና በአርያም በዳዊት ስም የምትመጣ የአባታችን መንግስት የተባረከች ናት እያሉ አቀባበል ያደረጉለት። እነሆ ዛሬ ለሺህ ዘመናት ሲነገርለት እና ትንቢት ሲተነበይለት የነበረው የኢትዮጵያን ህዝብ በፍቅር አንድ አድርጎ የሚገዛው ቴዎድሮስ የተባለው ንጉስ መጥቷል። እኛም በአማራ እምብርት በፈለገ ግዮን ንጉስ ቴዎድሮስ ልንል ተዘጋጅተናል። በዳግማዊ ቴዎድሮስ ሁለት መቶኛ የልደት በአል ላይ ሳልሳዊ ቴዎድሮስ ንጉስ ሁኖ በኢትዮጵያውያን ልብ ላይ ይነግሳል። መይሳው ካሳ በቴዲ አፍሮ ካሳ ካሳ የቋራው አንበሳ ሙዚቃ መቃብሩን ፈነቃቅሎ ይነሳል። የአባ ታጠቅ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ህልም በአባ ኮስትር ሀገር ባህር ዳር ላይ በሳልሳዊ ቴዎድሮስ ይዘመራል።

ቴዎድሮስን ለማንገስ ኢትዮጵያውያን ከመላ ሀገሪቱ ወደ ጎንደር እና ባህር ዳር እየተመሙ ነው። ከውጭ ሀገራትም ብዛት ያለው ህዝብ ጥምቀትን ጎንደር ላይ አክብሮ ባህር ዳር ላይ ሳልሳዊ ቴዎድሮስን ለማንገስ ወደ ኢትዮጰያ እየገባ ነው። ደጆች ይከፈቱ! ንጉሱ ይግባ። እግሮች ሁሉ ወደ ባህር ዳር አስራት ወልደየስ ስታዲየም ያመራሉ።

5 Responses to ቴዲ አፍሮ ለባህርዳሩ ኮንሰርት ስንት እንደተከፈለው ያውቁ ኖሯል? | ተጨማሪ መረጃዎችንም ይዘናል

 1. አዳኝ መሲ ይወለዳል ይመጣል ብላ የተናገረቸው ቤተክርስቲያን ናት? ገና ዛሬ ስማሁ ዘፋኝ ነው መሲቡ? ሆሆሆ ተናግሮ አናጋሪን ያዝልን ጌታ ሆይ ጉድ ሳይስማ መስከረም አይጠባም ል ክክክክክክ አመት ያሳቃል!!!

  ራሄል
  January 20, 2018 at 1:01 am
  Reply

 2. Wonderful that the brilliant and courage-incarnate Tewedros Kasahun, is gracing Bahr Dar where Amaras and Oromos affirmed their eternal unity only a month or two ago.

  This young man’s concert heralds Ethiopia’s resurrection. Mercifully, our country’s occupation by an inferior breed of men who are innately corrupt, vicious,venal and have neither moral scruple nor a shame culture, is coming to an end. The day Tigres will rue the day they were born into this suicidal entity, is written on the wall.

  Death and destruction to Ethiopia’s internal enemies. Long live our motherland.

  kibret Tesemma
  January 20, 2018 at 2:00 am
  Reply

 3. ቸር ተመኝ ቸር አንድታገኝ ይላል የሃገሬ ሰው ! ምኞት አይከለከልም ! ያውም ጥሩ ምኞት ማለቴ ነው ! ሃዳ አንደምኞታችሁ ይሆናል ትላላችሁ ? ለሁሉም መድህን ዓለም ክርስቶስ በቃችሁ ይበለን – አሜን !

  አደባይ
  January 20, 2018 at 3:19 am
  Reply

 4. Personal cult is detrimental to a society. Praise him as a single person! Elougizing long dead tyrants contributes little to solving current mountainous problems of the country. What else did Tedy contribute??

  ABBA Caala
  January 20, 2018 at 5:12 am
  Reply

 5. Shame on you for stating this “ሳልሳዊ ቴዎድሮስ ንጉስ ሁኖ በኢትዮጵያውያን ልብ ላይ ይነግሳል”. Even “ዳግማዊ ቴዎድሮስ” did not reign on all Ethipians unless you are re-defining what you mean by “Ethiopia” and “Ethiopians”.

  Zeraf
  January 21, 2018 at 9:37 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.