‹‹አለማረፍ የተርብ ቤት መቆስቆስ!!!›› – ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም (በጥቁር ገበያ አንድ ዶላር በ33 ብር በመመንዘር ላይ ይገኛል!!!)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ኢት-ኢኮኖሚ     ET-ECONOMY

‹‹አለማረፍ የተርብ ቤት መቆስቆስ!!!››        ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም

‹‹የልጄን ገዳይ ትናንት አገኘሁት፣

አይቼው ቢደነግጥ ውሃ ቢሆን ተውኩት!!!››

ወልድያ ለተረሸኑ ሰማዕታት መታሰቢያ ትሁን ገዳዮቹ ለፍርድ ይቅረቡ!!!  የአጋዚ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ፣ የወቅቱ ጥያቄ ነው!!!  የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የጋምቤላ፣ ወዘተ ወጣቶች እየተገደሉ ሠላም የለም! የልጆቻችንን ገዳይ እንፋረድ! የወያኔ አንባገነን መንግሥት በህዝብ አመፅ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡

‹‹ህዝቡን መመገብ ያልቻለ መንግሥት፣ መግዛት አይችልም!!!›› በጥቁር ገበያ አንድ ዶላር በ33 ብር በመመንዘር ላይ ይገኛል!!! የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን ከአመት ወደ አመት እየረከሰ መሄድ ማለትም፣ የአንድ ዶላር የብር ተመን በ1991 እኤአ 2.05 ብር የነበረ ሲሆን፣ ከ1992 እስከ 1994 እኤአ ወደ 5 ብር፣ ከ1995 እስከ 1999 እኤአ 5.88 ብር፣ ከ2000 እስከ 2004 እኤአ 8.15ብር፣ ከ2005 እስከ 2008 እኤአ 8.65 እስከ 9.67 ብር አንድ አሃዝ እየረከሰ ሄድ፡፡  ከ2009 እስከ 2015 እኤአ የአንድ ዶላር የብር ተመን ወደ ሁለት አሃዝ እየረከሰ ከ12.39 ብር ወደ 21.83 ብር፣ በ2017 እኤአ የአንድ ዶላር የብር ተመን 27.97 የብራችን የመርከስና የብር የመግዛት አቅም መውደቅ ዋና ምክንት የተደላደለና የረጋ የውጭ ምንዛሪ ተመን አለመኖሩን በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል፡፡ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በጥቁር ገበያ 33 ብር ገብቶል፡፡ መቶ የአሜሪካ ዶላር በ3300 ብር በመመንዘር ላይ ይገኛል፡፡ ባንክ ከሚመነዝረው በ500 ብር ልዩነት በመመንዘር ላይ ይገኛል፡፡ የወያኔ ሹማምንቶች ዶላር ና ወርቅ በማሸሽ ላይ ይገኛሉ፡፡ አዲስ አበባ ባሉ ወርቅ ቤቶች የወያኔ ሚስቶች አንድ ሚሊዮን ብር ሚያወጣ ወርቅ መሸመት የተለመደ ሆኖል፡፡ ንብረታቸውን እየሸጡ ገንዘብ በማስወጣት ሥራ ተጠምደዋል፡፡ የኦሮሞ ቆሮዎችና የአማራ ፋኖዎች ህዝባዊው አመፅ በደቡብ ህዝቦች፣ በአፋር፣ በሱማሌ፣ በሃረሪ፣ በቤኒሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባና በትግራይ ወጣቶች በይነ መረቡን ዘርግቶል፣ ውጤቱ በወራቶች ውስጥ ይታያል፡፡ መከላከያ ሠራዊቱም ህዝባዊውን አመፅ ይቀላቀላል፡፡ በውጭ ምንዛሪ እጦት ብዙ ፋብሪካዎች ሥራ አቁመዋል፡፡ የተጀመሩ ብዙ ፕሮጀክቶች ታጥፈዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ፤የውጭ ምንዛሪ ምጣኔን መወሰንና መቆጣጠር፣ኃላፊነቱን መወጣት ባለመቻሉ ሥራቸውን መልቀቅ አለባቸው፡፡ በኢትዩጵያ ውስጥ የምርት ገበያው፣ የሠራተኛ ገበያው፣ የካፒታል ገበያው፣የመሬት ገበያውም ተዛብተዋል፡፡ የሃገሪቱ የጥሬ ገንዘብ ስታቲስቲክስ መረጃ መልክ ተተምኖ የቀረበው በ1983 ዓ/ም አሥር ቢሊዩን ብር ገደማ የነበረው ብሄራዊ አማካይ የአገር ውስጥ ምርት፣ በ2008ዓ/ም አንድ መቶ ሃምሳ ዕጥፍ አድጎ አንድ ተኩል ትሪሊየን መድረሱ ከገበያው ፍላጎትና አቅርቦት መጣጣም መረጃ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ የህዝብ አመኔታን አጥቶል፡፡

 


በ1991እኤአ (1983ዓ/ም) ብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት (Real GDP) 10,535 ቢሊዩን ብር የነበረ ሲሆን በግዜው (አንድ ዶላር በ2.07 ብር እኩሌታ ይመነዘር ነበር) በ2015 እኤአ (2008 አ/ም) ብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት 1,300,000 ትሪሊየን ብር ሲሆን (አንድ ዶላር በ21.83 ብር እኩሌታ ይመነዘር ነበር) የሃገሪቱ ጂዲፒ እድገቱ በ123 እጅ ማለትም አስራ ሁለት ዕጥፍ እንዲደርስ አንዳደረገው ይስተዋላል፡፡ (አንድ ዶላር በ2.07 ብር እኩሌታ ወደ 21.83 ማደግ በ9.5 በመቶ አምስት እጥፍ በላይ የውጪ ምንዛሪው በማደጉ የብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ስሌት እንዲጨምር አደረገው፡፡) የብር መንዛሪ መርከስ ሁኔታ ማለትም በዓለም አቀፍ ንግድ ገበያ የኢትዩጵያ ብር የመሸጥና የመግዛት አቅም እንደተሸመደመደ ያሳያል፡፡ አገሪቱ በውጪ ንግድ የምትልካቸው ምርቶች ዋጋ መቀነስን አስመዝግቦል፡፡ እንዲሁም አገሪቱ በገቢ ንግድ የምታስገባቸው ካፒታል ጉድስ እቃዎች ዋጋ በመጨመሩ የዶላር  የመግዛት አቅም በ9.5 በመቶ ማለትም አምስት እጥፍ በላይ በመጨመሩ ሃገሪቱ በገቢ ንግድ ተጎጂ ሆናለች ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት (Real GDP) ከቢሊዩን ብር ወደ ትሪሊዩን ብር እምርታ ማሳየቱ የኢኮኖሚ እድገትን አያመላክትም፣ የብር መርከስንና የመግዛት አቅም መቀነስን ነው የሚያሳየው፡፡ የብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት (Real GDP) እድገት መገለጫዎች በሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች፣በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች መረጋገጥ አለበት፡፡  የመግዛት አቅም የሌለው ገንዘብና የሚዋዥቅ የውጭ ምንዛሪ ተመን( weak or volatile currency)መረጃ መሠረት፣ ከ1980 እኤአ እስከ 2014እኤአ አንድ ዩኤስ ዶላር ወደ ስንት የኢትዩጵያ ብር እየተተመነ፤ማለትም የብር የመግዛት አቅም ቅነሳ (devaluation) እያደረገ እንደመጣና ቅናሹ በመቶኛ ተሰልቶም በሰንጠረዡ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

“Annual inflation rates in Ethiopia from 2005 to 2013, respectively, were 9.95%, 12.20%, 17.25%, 43.80%, 10.57%, 8.12%, 33.00%, 23.33% and 8.07%. The reader can observe from this that the exchange rate has not been coping with the country’s inflation rates.“The Devaluation of the Birr: A Layman’s Guide, Part 2: By Seid Hassan, Murray State University; August 1, 2014

የአለም ባንክና አይኤም ኤፍ የኢትዩጵያ ብር እንዲቀንስ፤ማለትም የብር የመግዛት አቅም ቅነሳ (devaluation) እንዲያደርግ አሁንም አሳስበዋል የወደፊት እጣ ፈንታችን ምን ይሆን; የኢትዩጵያ ብር የውጭ ምንዛሪ ተመኑ እንዲቀንስና በውጭ ንግድ ገቢ በብዛት በመላክ የውጪ ምንዛሪ ማግኘት እንደሚቻል ምክረ ሃሳባቸው ነው፡፡ የአገር ውስጥ ምንዛሪ (currency) ከሌላ አገር ምንዛሪ ጋር በመገበያያ ዋጋ የሚለካው በእርግጠኛ መመነዛዘሪያ መጣኝ፣ የአንድ አገር ምንዛሪ ሸቀጦችን በመግዛት አቅሙ ከሌላ ተገበያይ አገር ምንዛሪ ሸቀጦችን በመግዛት አቅም ጋር ሲወዳደር፣ወይም ከጊዜ ወደ ጊዜ በተመናዛሪዎቹ አገሮች ውስጥ ያለውን የዋጋ ንረት ልዩነት ከግምት ባስገባ የመመነዛዘሪያ መጣኝ ሲሆን የሃገር ውስጥ ምርት በርካሽዋጋ መሸጡና የባህር ሞዶ ሸቀጣ ሸቀጥ በከፍተኛ ዋጋ መገዛቱ ገሃድ የሆነ ሃቅ ነው፡፡ በሃገር ቤት የዋጋ ንረቱ ከ12 እስከ 15 በመቶ ደርሶል፡፡ የዕዳ ጫናው የትየለሌ ሆኖል፡፡ የበጀት እጥረት ተከስቶል፡፡ ህዝቡ ለዳቦ፣ ለዘይት፣ ለዱቄት፣ ለስኮር፣ ለታክሲ፣ ወዘተ ሰልፍ የተለመደ ክስተት ሆኖል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ንዋየ-ኩብለላ ከሃገረ ኢትዩጵያ ወደ ባህር ማዶ ሃገራት (Illegal Ethiopian Capital Flight)

በአለፉት 40 አመታት ውስጥ፣ከኢትዬጵያ የውጭ ምንዛሪ ንዋየ-ኩብለላ በብዙ ቢሊዬን ዶላር በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሃገራቶች እንደወጣ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ ኢትዬጵያ ከአለማችን ከሚገኙ ደሃ አገራቶች ውስጥ ከመጨረሻዎቹ ጠርዝ ላይ የምትገኝ ስትሆን ይሄን የሚያህል የውጭ ምንዛሪ ከሃገር ውስጥ ወደ ውጭ ሲኮበልል የሃገሪቶን እድገት በማቀጨጭ ስርዐቱ ምን ያህል በሙስና የተጨማለቀ፣ግልፅነት የጎደለው መንግስታዊ አደረጃጀትና አሰራር በሃገሪቱ እንደሰፈነ ያሳያል እንዲሁም ተጠያቂነት የሌለበት የሽፍቶች፤ የነዱር ቤቴ ዘመን በከተሞች የሰፈነ ይመስላል፡፡ ሰባ ከመቶ የሚሆነው የኢትዬጵያ ህዝቡ በቀን ከአንድና ሁለት ዶለር ገቢ እያገኘ በሚኖርባት የድሆች፣ የርሃብተኛች፣የበሽተኞች ሃገር ይሄን የሚያህል የገንዘብ ነጠቃ ምን ይባላል፡፡ ጅቦች የሚያስተዳድሮት ሃገር ከማለት በስተቀር፡፡በኦክቶበር 2012 እኤአ ፕሮፊሰር ሊዎንስ ኤንዲኩማንና ፕሮፊሰር ጅምስ ኬ ቦይስ በማሳቹሴት  ዩኒቨርሲቲ አመህርስት፤ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትውት፤ ባቀረቡት የጥናት ርዕስ ‹የንዋይ ኩብለላ በስብ ሳህራ አፍሪካ አገሮች ከ1970 እስከ 2010› ጥናታዊ ሪፖርት መሠረት ከኢትዬጵያ ወደ ውጭ አገሮች የኮበለለ የውጭ ምንዛሪ ከ1970 እስከ 2010 ድረስ ምን ያህል  በየአመቱ እንደአደገና በየአስር አመቱም እምርታውን እየጨመረ መሄዱን ከጥናቱ ለመቃኘት ይቻላል፡፡

የብር ምንዛሪ ማርከስ( Devaluation of currency) የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ከሃገረ ሱዳን የኢትዮጵያን ብር እሳተመ ብሩን ወረቀት ደረጃ አድርሶታል፡፡ ባንኩ የሃገር ውስጥ ምርቱ ሳይኖር ጥሬ ገንዘቡን በማተም በሃገር ውስጥ ገበያ ገንዘብ በማሰራጨቱ የምርቱን ዋጋ መጨመር አስከተሎል፡፡ የሃገሪቱም የብር የመግዛት አቅም በመውደቁ ምክንያት የሃገር ውስጥ ምርቶችን የመግዛት አቅሙ ተዳክሞል፡፡ ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ ብሔራዊ ባንክ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦቱን  ከልኩ በላይ በሃገሪቱ ገበያ ውስጥ በማሰራጨቱ ተጠያቂ ነው፡፡

በኢትዬጵያ ከውጭ የተላከ ገንዘብ/ የውጭ ሐዋላ ከ2000 እስከ 2015እኤአ በ2000 እኤአ 53 ሚሊዩን ዶለር  የነበረው እያደገ መሄዱን  የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይፋ አድርረው ነበር፡፡ በግምት አንድ ሚሊዩን ከሚሆኑት ባህር ማዶ ሃገራት ከሚኖሩ ኢትዬጵያዊያን ሰደተኛች በ2012 እኤአ 2.4 ቢሊዩን ዶለር ከውጭ ሐዋላ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገባ የብሄራዊ ባንክ ገልፆል፡፡ በዚህም  መሠረት ከባህር ማዶ ከሚኖሩ ኢትዬጵያውያን ወደ ሃገር ውስጥ የተላከ ገንዘብ የዓለም ባንክ ባወጣው መረጃ፣ ከሠንጠረዡ ላይ መመልከት እንደሚቻለው ዝቅተኛ ከውጭ ሐዋላ የተገኘው ገቢ በ2001 እኤአ 18 ሚሊዩን ዶለር የነበረ ሲሆን ከፍተኛ 3 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር በ2013እኤአ እድረት እንዳሳየ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲሁም በ2015 እኤአ 4 ቢሊዩን ዶላር ወደ ሃገር ቤት ገንዘብ ልከዋል፡፡ በዚህም መሠረት በውጭ የሚኖሩ ኢትዬጵያውያን ወገናቸውን በመርዳትና በማስተዳደር የሲሶ መንግስትነት ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛሉ ሰለዚህም በሀገራቸው ጉዳይ ከማንም በላይ ሊያገባቸውና ድምፃቸውም ሊሰማ ይገባቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዬጵያ ከውጭ የሚላከው ገንዘብ/ የውጭ ሐዋላ ከመጠን በላይ ቀንሶል፡፡ በባህር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህወሓት የግፍ አገዛዝ በመቃወም የሃዋላ እቀባ በተሳካ መልክ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡

 

በአሁኑ ግዜ፤በዚህ የውጭ ምንዛሪ ንዋየ-ኩብለላ ከሃገረ ኢትዩጵያ ወደ ባህር ማዶ ሃገራት የሚደረግ ዘረፋና ስርቆት ዋና ተዋናይ በመሆን የህወሃት/ኢህአዲግ ቱባ ባለስልጣኖች፣  የጦር አበጋዞች ጀነራል መኮንኖች፣ አንባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፤ ኢፈርትና ሜድሮክ ቢዝነስ ኩባንያዎች (የወርቅና የውጭ ምንዛሪ ንዋየ-ኩብለላ) በማከናወን የአንበሳውን ድርሻ ሲቀራመቱ የቻይና ባለሃብቶችም ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከአስር በላይ የሚሆኑ የቻይና ባለሃብቶች ከ50 ሽህ እስከ 500000 ዩኤስ ዶለር  ወደ ሃገራቸው ለማስወጣት ሲሞክሩ አዲስ አበባ ኤርፖርት ተይዘው ወህኒቤት ተፈርዶባቸው ይገኛሉ፡፡ የቻይና ባለሃብቶች ሦስት ቢሊዩን የኢትዩጵያ ብር በማከማቸት የእራሳቸው ስውር ካዝና የገንዘብ ዝውውር በማድረግ ከባንክ የውጭ ምንዛሪ ተመን በላይ በጥቁር ገበያውን በመቆጣጠር ብርን ወደ ዩኤስ ዶለር በመቀየር ወደ ቻይና በመላክ የሞቀ ንግድ ያከናውናሉ፡፡ እንዲሁም የክልል መንግስታት በተለይም ከኢትዩጵያ አጎራባች  ሃገራት ጋር የሚዋሰኑ ክልሎች የአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ቢኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሱማሊያ ክልላዊ መንግስታት ድንበር በኩል  የወርቅ፣ ቆዳ፣ ነዳጅና፣ የቁም ከብት፣ የግብርና ምርቶች በተለይ ቡና፣ ጫት፣ ሰሊጥ፣ ጤፍ  የውጭ ምንዛሪና የንዋየ-ቅዱሳን ኩብለላ ወደ ጂቡቲ፣ ሱዳን ፣ኬንያ፣ ሱማሊያ በኩል በስፋት ይከናወናል፡፡

የቻይና መንግሥት ለኢትዩጵያ መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶችን በሰጠው ከፍተኛ ብድር የተነሳና ዕዳቸውን መክፈል ስለተሳናቸው የፕራይቬታይዜሽን መርሃ-ግብር ነድፎ  የኢትዩጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት፣ ኢትዮቴሌኮም፣ የኢትዩጵያ ምድር ባቡር ድርጅትን ለመቆጣጠር አሰፍስፎል፡፡ የኢትዩጵያ መንግሥት  ያለበትን  ዕዳ መክፈል የሚችለው በውጪ ንግድ ዘርፍ ሃገሪቱ ወደ ባህር ማዶ አገራቶች ምርቶቾን ልካ የውጪ ምንዛሪ በማግኘት ያለባትን ብድር በዶላር የመክፈል ግዴታ አለባት፡፡ አንድ ሃገር የውጪ እዳዋን የመክፈል ዓለም ዓቀፋዊ ስምምነት አለ፡፡  ሃገሪቱ ለተበደረችባቸው ፕሮጀክቶች፣ እዳ መክፈል ካልቻለች፣ ሃገሪቱ የገነባችውን መሠረተ,ልማቶች የዓየር ማረፍያ፣ ወደብ፣ ባቡር፣ ቴሌ፣ መብርት ኃይል፣ ውኃ ወዘተ  በፕራይቬታይዜሽን መርሃ-ግብር ለአበዳሪው ሃገር ወይም በዓለም አቀፍ ጨረታ ይቸበቸባሉ ፡፡

ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት መጨረሻው ይሄው ነው፡፡

የህሊና እስረኞች ይፈቱ!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<