ሰበር ዜና: በቴዲ አፍሮ የባህርዳር ኮንሰርት የተከሰተው….. | ከስፍራው የደረሰንን መረጃ በጽሁፍና በቪዲዮ ይዘናል

Filed under: News Feature,ኪነ-ጥበባዊ ዜና,የዕለቱ ዜናዎች |


(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ማምሻውን በባህርዳር ስታዲየም በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ የተገኘበት የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት በሰላም ተጠናቀቀ:: ዘ-ሐበሻ ኮንሰርቱ ላይ የታደሙ ወገኖችን በማነጋገር የተለያዩ መረጃዎችን አሰባስባለች::

እጅግ ያማረ የነበረው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት የባህርዳር ከተማን ማነቃነቅ የጀመረው ገና ከጠዋቱ እንደነበር የሚናገሩት ወገኖች ኮንሰርቱ የሚደረግበት ስታዲየም በር ላይ መሰለፍ የጀመረው ሕዝብ በሞንታርቦ የቴዲ አፍሮ ዘፈኖች ተከፍቶለት ዘና ፈታ እያለ ነበር:: የቴዲ ኮንሰርት ከታሰበለት ሰዓት ትንሽ ዘግየት ብሎ እንደጀመረ የሚናገሩት እነዚሁ ወገኖች ቴዲ አፍሮ ሕዝቡን ባይቆጣጠረው ኖሮ የሕዝቡ ስሜት አስፈሪ ነበር ብለዋል::

ከተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ወደ ባህርዳር የተመሙት አድናቂዎቹ “አማራው አይፈራም” “ኢትዮጵያ ኬኛ” “ወልዲያ” “ወያኔ ሌባ” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች ሲያሰሙ እንደነበር የገለጹት የአይን እማኞች ቴዲ ሕዝቡን “ፍቅር ያሸንፋል” ፍቅር ያሸንፋል እያለ እንዳረጋገው ገልጸዋል::

ኢትዮጵያዊነት የነገሰበት ይኸው የባህርዳሩ ኮንሰርት ሕዝቡ ብሶቱን ያሰማበት እንደነበር የሚገልጹት የአይን እማኞች ስታዲየሙ በአረንጓዲ ቢጫ ቀይ ባንዲራና የቴዲ አፍሮ ምስል ባለበት ነጭ ባንዲራ ተሞልቶ ነበር ብለዋል::

ቴዲ አፍሮ በመድረክ ላይ ያሳየው ብቃት የሚደነቅ እንደነበር እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች ገልጸው ሕዝቡ ቴዲ አፍሮ የሚለውን ባይሰማ ኖሮ በሰላም ላይጠናቀቅ ይችል ነበር ብለዋል::

በዚህ ኮንሰርት ላይ የአማራ ክልል ባለስልጣናት የታደሙ ሲሆን ሕዝቡም በአደባባይ ተቃውሞውን “አማራ አይፈራም” “ኦሮሞ የኛ” “ኢትዮጵያ የኛ” ‘ወያኔ ሌባ’ እያለ በአደባባይ ሲያወግዝ ተመልክተዋል::

በዚሁ ኮንሰርት ላይም በትናንትናው ዕለት በወልዲያ ከተማ የጥምቀትን በዓል ለማክበር ወጥጠው በትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች የተገደሉት ወገኖቻችንን ሕዝቡ “ወልዲያ” “ወልዲያ” እያለ አስቧቸዋል::

የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በሰላም ከተጠናቀቀ በኋላም በባህር ዳር አደባባይ ሕዝቡ በመውጣት ለወያኔ ስርዓት ያለውን ጥላቻ በመግለጽ ብ አዴን ከተላላኪነት እንዲወጣ የሚጠይቅ ድምጽ ተሰምቷል::

የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በቅርቡ በአዳማ; በአዋሳ; በመቀሌ; በጋምቤላ እና በድሬደዋ ከተሞች ለማካሄድ እቅድ እንደተያዘ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል::

6 Responses to ሰበር ዜና: በቴዲ አፍሮ የባህርዳር ኮንሰርት የተከሰተው….. | ከስፍራው የደረሰንን መረጃ በጽሁፍና በቪዲዮ ይዘናል

 1. It is good to hear success story about the event! Yes,
  Love wines even if it is not a newly invented word or phrase or concept .
  The question is what does love wins mean ? What does Ethiopia toward love mean ? Who is the enemy of peace and love? The people or the ruling gangs? whose love wins? How and where tis love comes from? By defeating the gangs of hatred and disunity or just by singing and preaching ? Are you saying that the people calmed down because Tewodros preached them not to confront the killing machine but to love it (the killing machine)?? If that is the meaning, it is not real love but fake love. What is the brutal ruling gangs including those who were honorably seated at the event are doing in many parts of the Amhara and Oromia regional states ? How many innocent citizens terribly suffered and killed while we were talking and singing about love and peace and patriotism ?I do not know how it makes sense for the people to enjoy musical concert in that kind horribly disturbing situation .

  To my understanding and belief, Tewodros would have been much more honored if he had canceled the event for the sake of the comfort of mourning families and the people general, especially of Woldians as well as for the sake of comforting those who were badly bitten up and all other badly traumatized young and all other innocent citizens . I do not know how the musical concert can be said colorful and wonderful where as the people are in a very disturbed state of the situation and extremely frustrated minds.

  I watched Teodros’s interview with the Amhara National Democratic Movement/Beaden Television for about 40′ . He is a very ‘smart’ guy . His words are very selective or purposely very general as he does not want give an impression that he is critical of TPLF/EPRDF. His words are very general or common that don’t open any chance of catching him with specific and concrete terms, and he articulates it very carefully.

  T. Goshu
  January 21, 2018 at 8:47 pm
  Reply

 2. poor politicianz .their silly attempt to turn every gathering into chaos is invain .
  አወገዘ ፡ተሣደበ ፡ፎከረ ፡አቅራራ ፡ ምናምን አይሠልችም ??

  nana
  January 21, 2018 at 9:20 pm
  Reply

 3. Tedy don’t go to that country Tigray. You can’t earn any love from that Land and people. You better go to Eritirea or Sudan.

  nabil
  January 21, 2018 at 9:39 pm
  Reply

 4. The Tigray militia that have murdered the young in Weldia belong to the special forces the TPLF leaders have trained and armed. This militia will unleashed in every part of Ethiopia where protests against the fascist rule of the TPLF can happen. According to crdible sources, the Tigray militia are trained like the Sudanese Janjaween that went into rampage in Darfur. The Tigray militia or paramilitary force are the Janjaween of the TPLF and are brainwashed with hate and have the mission to kill the Oromos and Amharas. The Oromia leadership under Lema Megersa should do all it can to stop the deployment of this murderous Tigray militia in the region.

  Mezmur
  January 22, 2018 at 4:41 am
  Reply

 5. አንዳንድ ታዳሚ ፡፡
  በጠጅ አሟሙቁ ፡በረቂ ደቆ ፡ በጫት ፈጦ አስር ብር ከፍሎ ይገባና
  ሠማይን የነካ አለምን የገዛ ይመስለዋል

  ነቄ
  January 22, 2018 at 8:00 am
  Reply

 6. ሀገርን መውደድ ወንጀል የሆነበት ሀገር በምድር ላይ ኢትዮጵያ ብቻ ነው። ይቺ ወቅት ታልፋለች። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ለማለት የማንፈራበት ቀን ቅርብ ነች!!!

  ጀማል
  January 24, 2018 at 10:41 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.